موعــظة مــؤثّرة من إمــــام الشَّــيخُ العلّامــة/
محــمّّد بنُِ صِالِــح العُثــيمين-رحِــمُه الله- :
ተፅዕኖ አሳዳሪ ግሳፄ ከሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊህ
አልዑሰይሚን ረሂመሁላህ
≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅
«የሰው ልጅ ህይወቱ በአካሉ ውስጥ እስካለች ድረስ ለፈተና የተጋረጠ ነው። ስለሆነም ራሴንም ሆነ እናንተን የምመክረው ጉዳይ በእምነታችን ላይ ፅናት እንዲኖረን ዘወትር አላህን መጠየቅ እንዳለብን ነው። ምክንያቱም ከእግሮቻችሁ ስር አንሸራታች ነገር ኣለና ልትሰጉት ይገባል። ሃያሉ አላህ እንድትፀኑ ካላደረጋችሁ በስተቀርም ለጥፋት ትዳረጋላችሁ።
ከእንከን ሁሉ የጠራው ሃያሉ አላህ ለመልእክተኛው አለይሂ አሰላቱ ወሰላም
{وَلَوْلَا أَن ثَبَّتْنَاكَ لَقَدْ كِدتَّ تَرْكَنُ إِلَيْهِمْ شَيْئًا قَلِيلًا } الإسراء (74)
“በአቋምህ ላይ እንድትፀና ባናደርግህ ኖሮ (ወደ ቅኑ ሀይማኖት እንዲገቡልህ ከመጓጓትህ የተነሳ የሚሉህን ሰምተህ) በትንሹም ቢሆን ወደነሱ ልትዘነበል በተቃረብክ ነበር።” በማለት የሱ ጥበቃ ባይታከልበት ኖሮ ከአቋም ዝንፍ ማለት ከፍጡራን ሁሉ የበለጠ ፅናት ላላቸው መልእክተኛው እንኳን እንደማይቀር ገልፇል።
ታዲያ መልእክተኛው ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ይህ ሁኔታ ይደርስባቸው ነበር ተብሎ የሚፈራላቸው ከሆነ እኛስ ምን ይውጠን ይሆን? በኢማናችን ሆነ በየቂናችን ደካማ የሆንን ውዥንብሮችና ስሜታዊነት የሚያጠቃን ከመሆናችን አንፃር ምንኛ ለመንሸራተት የቀረብን ነን!
ስለዚህ ሀይለኛ በሆነ አደጋ ውስጥ ነው ያለነውና በሀቅ ላይ እንዲያፀናን አላህን ልንለምነው ይገባል። ልባችን በወንጀል ቆሽሾ ለዝገት እንዳይዳረግብንም
{رَبَّنَا لَا تُزِغْ قُلُوبَنَا بَعْدَ إِذْ هَدَيْتَنَا …} آل عمران(8)
“ጌታችን ሆይ ቅኑን መንገድ ከመራኸን በኋላ ልቦናችንን አታዝግብን።” እያልን በዚያ የባለ ልቦናዎች ልመና በሆነው ዱዓእ አላህን መለመን አለብን።»
📕 [الشرح الممتع (5\388)]
[ሸርሁል ሙምቲዕ 5/388]
≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅
Abufewzan
ሻዕባን 28/1439
14/05/2018
0 Comments