ለተራዊሕ ኢማሞች (በተለይ ለወጣቶቹ)
ስለ ስራችሁ መልካምነት ላወራ አልፈልግም፡፡ እሱን “አገር” ያውቀዋልና፡፡ እናም የሚታወቀውን ለማሳወቅ በከንቱ
መድከም አልፈልግም፡፡ ይልቁንስ ፅሁፌ እርማት የሚሻ ነገር አለና አትዘንጉት ለማለት ነው፡፡ ነብያችን ሰለላሁ
ዐለይሂ ወሰለም እንደሚሉት “ዲን መመካከር ነው፡፡” ስለሆነም ከተራዊሕ ኢማሞች በስፋት ይታያሉ የምላቸውን ነጥቦች
እንደሚከተለው አስፍሪያለሁ፡፡
1. የኹሹዕ መቅለል፡- ኢማሞቻችን ላይ ጎልተው ከሚታዩ ድክመቶች በሰላት ላይ ኹሹዕ አለመኖር ነው፡፡ እንደሚታወቀው የሰላት ሩሑ ኹሹዕ ነው፡፡ ኹሹዕ ከሌለ የሰላቱ ህልውና እራሱ ጥያቄ ላይ ወድቋል፡፡ ዛሬ ግን ይሄ ወሳኝ ነገር አደጋ ላይ ነው፡፡ ሰላቱ ሩጫ ሆነ፡፡ ወላሂ በረመዳን መግባት ተደስተን ሳንጨርስ፣ የተራዊሕን ጥዑም ድባብ ሳናጣጥም ውስጣችን ወከባ በበዛበት የአሰጋገድ ስርኣት እየደፈረሰ ነው፡፡ ወላሂ ከስንት መስጂድ ውስጥ ነው ተሸሁድ (አተሒያቱን) ሳንጨርስ የሚሰላመትብን፡፡ እንዴት ተደርጎ እንደሚቀራ አላውቅም፡፡ ሩጠን እንኳን መድረስ አልቻልንም፡፡ እስኪ እራሳችንን ከዚህ ሐዲሥ አንፃር እንገምግመው፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መስጂድ ውስጥ ተቀምጠው ሳለ አንድ ሰው ገባና ሰገደ፡፡ ሰላቱን እንደ ጨረሰ ለአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰላምታ አቀረበ፡፡ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ተመለስና ስገድ፡፡ ምክኒያቱም አልሰገድክምና!” አሉት፡፡ ተመልሶ ሰገደና መጥቶ ሰላምታ አቀረበ፡፡ “ወዐለይከሰላም፡፡ ተመለስ ስገድ አልሰገድክም!” አሉት፡፡ ሶስት ጊዜ ከፈፀመ በኋላ “በሐቅ በላከህ እምላለሁ! ከዚህ የበለጠ አላሳምርም፡፡ አስተምረኝ” አላቸው፡፡ ይህን ጊዜ መልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉት፡- “ለሰላት ስትቆም “አላሁ አክበር” በል፡፡ ከዚያም የተገራልህን ያክል ቁርኣን ቅራ፡፡ ከዚያም ሩኩዕ አድርግ፡፡ ሩኩዕ ላይ እስከምትረጋጋ ድረስ፡፡ ከዚያም ቀና በል፡፡ ተስተካክለህ እስከምትቆም ድረስ፡፡ ከዚያም ሱጁድ አድርግ፡፡ በሱጁድ እስከምትረጋጋ ድረስ፡፡ ከዚያም (ከሱጁድ) ቀና በል፡፡ ተስተካክለህ እስከምትቀመጥ ድረስ፡፡ ከዚያም በሰላትህ ባጠቃላይ እንዲሁ ፈፅም፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት ነው፡፡) እስኪ አሁን የኛን የተራዊሕ ሰላት በዐይነ-ህሊና እንቃኘው፡፡ ጤነኛ የሚባል ነው? ከሆነ እሰየው!!
2. ቁርኣን ሲሳሳቱ የሚስተዋሉ ችግሮች፡- ወንድሞቼ እውነት ለመናገር ምግባራችሁ ያማረ ምግባር ነው፡፡ ነገረ ግን ኢኽላስ ከጎደለው፣ በማልቀስ “አላህን ፈሪ” መባል ከታሰበ፣ “ጎበዝ ሐፊዝ” ለመባል፣ ወይም “ድምፁ ያምራል” ለመባል የሚሰራ ከሆነ ምንኛ አስቀያሚ ተግባር ነው?! አንዳንዶቹን ኢማሞች ቁርኣን ሲሳሳቱ ማረም ከባድ ነገር ነው፡፡ ከኋላ ያለ ሰው የሚያርማቸውን ጥለው በራሳቸው ችክ ብለው የሚታገሉ አሉ፡፡ (አራሚው ላይ ያለው ችግር በራሱ እንዳለ ሆኖ፡፡) አንዳንዶቹ የጠፋባቸውን ለማግኘት ሲሉ ሰው የሚነግራቸውን ጥለው በጣም ወደ ኋላ ርቀው ይመለሳሉ፡፡ አንዳንዶቹ የሚነገራቸውን ትተው እንደፈለጉ አድርገው ይቀጥላሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ መጀመሪያ ረከዐ ላይ የጠፋባቸውን ቦታ ለማረም ቀጣዩ ረከዐ ላይ ተመልሰው የሚታገሉ አሉ፡፡ ይሄ ከሐፊዝ የማይጠበቅ አሳፋሪ ባህሪ ነው፡፡ የተሸከሙት ቁርኣን በቀዳሚነት የሚያጠነጥነው ስለኢኽላስ ነው፡፡ ስህተታችንን ብዙሃን ስለሰማው የምንሸማቀቅ ከሆነ ነፍስያችንን ማሸነፍ አቅቶናል ማለት ነው፡፡ መሳሳቱ እኮ ምንም ክብርን ዝቅ አያደርግም፡፡ አይደለም ሌላ ቀርቶ ቁርኣኑ የወረደባቸውን ነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንኳን ያጋጥም አልነበር እንዴ፡፡ ለምሳሌ በአንድ ወቅት ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እያሰገዱ ሳለ ቂራኣታቸው ተቀላቀለባቸው፡፡ ሲጨርሱ ኡበይን ረዲየላሁ ዐንሁ “ከኛ ጋር ሰግደሃል?” አሉት፡፡ “አዎ” አላቸው፡፡ “ታዲያ እንዳታስታወስኝ የከለከለህ ምንድን ነው?” በማለት ሊያስታውሳቸው ይገባ እንደነበር ተናገሩ፡፡
3. መሰረታዊ የሰላት ድንጋጌዎችን አለመለየት፡- እያሰገዱ ቢሳሳቱ ምን ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው የሚያውቁት ስንቶች ይሆኑ? የማካካሻ ሱጁድ እንደተፈፀመው ስህተት ከማሰላመት በፊት ወይም በኋላ ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ጠንቅቀው የሚለዩት ምን ያክሉ ናቸው? በአጭሩ አንድ ሰው አንድ ሀላፊነት ላይ እስካለ ድረስ ሀላፊነቱን ባግባቡ እንዲወጣ የሚያስችሉትን መሰረታዊ ተግባራት ጠንቅቆ ሊያውቅ ይገባል፡፡ ያለበለዚያ ኢማምነት ሀላፊነት ነው፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ኢማም ሀላፊ ነው” ማለታቸው ከግምት ይግባ፡፡ እሱ ባግባቡ ሲሰግድ ነው ተከታዮቹ ባግባቡ ሊሰግዱ የሚችሉት፡፡ ኢማሙ አሳስቶ የሚፈፅማቸው ተግባራት በተከታዮቹ (መእሙሞቹ) ይበልጥ የበላሸት እድል አላቸው፡፡ ይሄ ነገር በደንታ ቢስነት ከተፈጸመ ደግሞ ከራሱ አልፎ በሌሎች ስህተት የሚጠየቅበት ሁኔታ ሊኖር ይችላልና መጠንቀቅ የግድ ይላል፡፡
4. ሱናው ላይ ከማነጣጠር ይልቅ ታዋቂ ኢማሞችን ለመምሰል መጣር፡- የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የረመዳን ሰላት እጅግ ያማረ እንደነበር እናታችን ዓኢሻ ተናግራለች፡፡ “ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መመሪያ ነው፡፡” ሩኩዕና ሱጁድ አልፎም ተሸሁድ ላይ አሯሩጣችሁ ቁኑት ላይ 20 ደቂቃ፣ 30 ደቂቃ መገተሩ የጤና ነው? ይህን ልክ ያለፈ ማስረዘም በርካታ ዐሊሞች እንደሚኮንኑት ልናውቅ ይገባል፡፡ እንዳውም አንዳንዶቹ “ቢድዐ ነው” እስከማለትም ደርሰዋልና ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡ ደግሞስ ምነው ይሄን ያህል የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የቁኑት ዱዐ ተዘነጋ? ስንቶች ናቸው ዛሬ በዱዐ አጉል ፀጉር ስንጠቃ ውስጥ የሚገቡት? ስንቶችስ ናቸው የዱዐቸው እያንዳንዱ ዐረፍተነገር አንድ አይነት ምት (ሪትም) እንዲኖረው የሚጨናነቁት? ስንቶችስ ናቸው ድምፃቸውን ከፍ ዝቅ እያደረጉ አላስፈላጊ ዜማ የሚያዜሙት? ስንቶችስ ናቸው ሳይመጣባቸው የግድ ለማልቀስ የሚታገሉት? ስንቶችስ ናቸው ገደብ ያለፈ ጩኸት የሚጮሁት? ስንቶችስ ናቸው በዱዐቸው ላይ ልክ ባለፈ መልኩ ዝርዝር የሆነ ነገር የሚተነትኑት? ሰሐባው ዐብዱላህ ኢብኑ ሙገፈል ረዲየላሁ ዐንሁ ልጁን “ጌታየ ሆይ! ጀነት እንደገባሁ በቀኝ በኩል የሚገኝ ነጩን ህንፃ እለምንሃለሁ” እያለ ዱዐ ሲያደርግ ሰማው፡፡ ይህኔ አባት እንዲህ አለው፡፡ “ልጄ ሆይ! አላህን ጀንትን ጠይቀው፡፡ በሱም ከእሳት ተጠበቅ፡፡ እኔ የአላህ መልእክተኛን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ከዚህ ህዝብ ውስጥ በጡሃራ እና በዱዐ ድንበር የሚያልፉ ሰዎች ይመጣሉ” ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ” አለው፡፡ ሐዲሡን ሸይኹል አልባኒ “ሰሒሕ” ብለውታል፡፡ ሱብሓነላህ!! ኪታብ ላይ ያለውን ጥለን ሰዎች ላይ ያየነውን ለምን እናስቀድማለን? “እከሌ ቦታ እየተሰራ አይደለም ወይ?” የሚል የየዋህ ደሊል ከአስተዋይ ሰው አይጠበቅም፡፡ የትም ቦታ፣ በየትኛውም ሸይኽና ኢማም ከሚሰራው ይልቅ መልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሰሩት በላጭ እንደሆነ ለማንም አይሰወርም፡፡ ታዲያ ምን ሲባል በላጩን ጥለን ዝቅ ያለው ላይ ይህን ያክል ሙጭጭ እንላለን? ምናለ ለቁኑት የሚሰጠው ረጂም ጊዜ መሰረታዊ ለሆኑት የሰላቱ ክፍሎች ተሰጥቶ ተረጋግተን ብንሰግድ?
በጥቅሉ በርካታ ችግሮች አሉ፡፡ አቅማችን በፈቀደ ግን ዘወትር ልናርምና ልናሻሽል ይገባል፡፡ በዙሪያችን ያሉ ዐሊሞችንም ምክርና ሀሳብ መስማት ደግ ነው፡፡ መግቢያየ ላይ እንዳልኩት ደካማ ጎን የመሰለኝን ለመጠቆም ይህን አልኩ እንጂ በጎ ስራዎቻችሁን ዘንግቼ አይደለም፡፡ ከዚያ ባለፈ እንዲሁ ችግሩ እኔንም ሌላውን በብዛት ስለሚያጋጥም እንጂ ሁሉንም በጅምላ ልፈርጅም አይደለም፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡ በሀሳቤ የምትስማሙ ካላችሁ እባካችሁን ችግሩ ላለባቸው አድርሱልኝ፡፡