ሱሑርን የሚመከቱ ጥቂት ማስታወሻዎች
በተለምዶ ማሰሪያ እያልን የምንጠራው በፆም ወቅት ሊሊት ላይ የምንመገበው ምግብ በዐረብኛው “ሰሑር” ሲባል ድርጊቱ ማለትም በዚያ ሰዐት መመገቡ ደግሞ “ሱሑር” ይባላል፡፡ ልዩነቱን በጥንቃቄ ሲያነቡ ያገኙታል፡፡ ሱሑር የሙስሊሞች ሱና ነው፣ እጅጉን የተወደደ ምግባር፡፡ ይህን የሚያመላክቱ የተለያዩ ነብያዊ ሐዲሦች አሉ፡፡ ለምሳሌም የሚከተሉትን የነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሐዲሦች ማውሳት ይቻላል፡፡
1. “ሰሑርን ተመገቡ፡፡ በሰሑር ላይ በረካ አለና፡፡” [ቡኻሪና ሙስሊም]
2. “በኛ ፆም እና በመፅሀፉ ሰዎች ፆም መካከል መለያው የሱሑር ምግብ ነው፡፡” [ሙስሊም]
3. “እሷ (ሱሑር) አላህ የሰጣችሁ በረከት ነች፡፡ ስለሆነም አትተዋት፡፡” [ነሳኢይ]
ስለዚህ ሱሑር የተለያዩ ጥቅሞች አሉት ማለት ነው፡፡ ከነዚህም ውስጥ
1. በረከት አለበት
2. ከመፅሀፉ ሰዎች (ከአይሁድና ከክርስቲያኖች) መለያ ነው
3. ማንም በግልፅ እንደሚረዳው ቀን ላይ የተሻለ ብርታትና መቋቋም እንዲኖር ያደርጋል፡፡
ከነዚህም ውጭ እኛ የማናውቃቸው ሌሎች ጥቅሞች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ አዋቂው አላህ ነው፡፡
ሱሑር የተወደደ ለመሆኑ ምን ጥርጥር የለውም፡፡ ታዋቂው ዐሊም ኢብኑ ቁዳማህ ረሒመሁላህ “(ሱሑር) የተወደደ ለመሆኑ በዑለማዎች መካከል ውዝግብ አናውቅም” ይላሉ፡፡ የተወደደ እንጂ ግዴታ አለመሆኑን የሚጠቁመው የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያለ ሱሑር ቀናቶችን አከታትለው መፆማቸው ነው፡፡
ታዲያ በላጩ ነገር ሰሑርን አዘግይቶ መመገብ ነው፡፡ ለዚህም “ፊጥራን አፋጥኑ፡፡ ሱሐርን ግን አዘግዩ” የሚለው የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ንግግር ምን ያማረ ማስረጃ ነው፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 1773] የሱብሒ ሶላት ወቅት እስከሚገባ ድረስ መመገብ ይቻላል፡፡ በነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘመን ፈጅር ከመግባቱ ቀደም ብሎ ቢላል ረዲየላሁ ዐንሁ አዛን ያደርግ ነበር፡፡ የሌሊት ሰጋጆች ሶላታቸውን እንዲያገባድዱ ጥቆማ ለመስጠትና በእንቅልፍ ላይ ያሉ አማኞችን ደግሞ ተነስተው እንዲዘጋጁ ለማድረግ፡፡ የፈጅር ወቅት መግባቱን ለማወጅ ደግሞ ዐብዱላህ ኢብኒ ኡሚ መክቱም ነበር አዛን የሚያደርገው ረዲየላሁ ዐንሁ፡፡ ታዲያ መልእክተኛው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የቢላል አዛን እንዳይሸውዳችሁ” በማለት በዚያ ሰዐት ሰሑር መመገብ እንደሚቻል ይጠቁማሉ፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም] በተጨማሪም “ቢላል በሌሊት ነው የሚጣራው፡፡ ኢብኑ ኡሚ መክቱም እስከሚጣራ ድረስ ብሉ ጠጡ” ይላሉ፡፡ [ቡኻሪ፡ 617]
በነገራችን ላይ በሱሑር ወቅትና በፈጅር ሶላት ወቅት መካከል መጠባበቂያ የሚሆን የተወሰነ ሰዐት በመተው ካላንደር ማዘጋጀት ከሱና ጋር የሚፃረር እንደሆነ ዑለማዎች ይገልፃሉ፡፡ የአዲስ አበባ መጅሊስ በያመቱ የሚያዘጋጀውና በየመሳጂዱ የሚበትነው ካላንደር ይሄ ችግር ይስተዋልበታል፣ የዘንድሮዉን ባላውቅም፡፡ ሶሐቦች ከነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር ሰሑር ከተመገቡ በኋላ ቀጥታ ወደ ፈጅር ሶላት ይወጡ እንደነበር የሚያመላክቱ መረጃዎች የፈጅር ሶላት ወቅት እስከሚገባ ድረስ መመገብ እንደሚቻል ያስረዳሉ፡፡ እንዳውም የፈጅሩ መውጣት ግልፅ እስከሚሆን ድረስ መመገብ እንደሚቻል ጌታችን በቁርኣን ተናግሯል፡፡ [አልበቀራህ፡ 187] እነዚህ ማስረጃዎች ይሄ በሱሑርና በፈጅር ሶላት መካከል መጠባበቂያ ሰዐት መመደብ አግባብ እንዳልሆነ ግልፅ ማስረጃ ናቸው፡፡ ከዚህም ባለፈ አዘግይቶ መመገቡ ፈጅርን በወቅቱ ለመስገድ፣ በዚህም ላይ ላለመዘናጋት ጠቃሚ ነው፡፡ በጣም ቀደም ብሎ የሚመገብ ሰው ግን ፈጅርን በወቅቱ የመስገድ እድሉ እጅጉን አናሳ ነው፡፡ ባይሆን አንዳንዶች ጋር እንደሚስተዋለው ምንም በማያጠራጥር መልኩ ወቅቱ በግልፅ ፍንትው ብሎ ከለየ በኋላም ጭምር እየተመገቡ ሊዘናጉ አይገባም፡፡ ይሄ እጅግ አደገኛ ነገር ነው፡፡
አንዳንድ ሰው ሱሑር ሰዐት ላይ መመገብ በጣም ይከብደዋልና ምን ያድርግ? በመጀመሪያ ጉዳዩ ግዴታ ስላልሆነ ችግር የለበትም፡፡ ባይሆን ሱናው እንዳይቀርበት በረካው እንዳያልፈው ያክል ቀለል ያለ ነገር እንኳን ቢፈፅም መልካም ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ተምር ቢመገብ፡፡ መልእክተኛው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ተምር ምንኛ ያማረ የሙእሚን ሰሑር ነው!!” ይላሉ፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 562] ይህንንም ካልቻልን ቢያንስ ውሃ እንኳን እንቅመስ፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡- “ሰሑር በረከት ያለበት ምግብ ነው፡፡ አንዳችሁ የውሃ መጎንጨት እንኳን ቢሆን ይጎንጭ እንጂ እንዳትተዉት፡፡ ምክንያቱም አላህ እና መላእክቱ ሰሑር በሚመገቡ ላይ ሶለዋት ያወርዳሉና፡፡” [ሶሒሑልጃሚዕ፡ 3683]
በዚህ አጋጣሚ ረመዳን ላይ ሰዎችን ለሱሑር ለመቀስቀስ በሚል እሳቤ ድቤ እየደበደቡ ሌሊቱን መዞር፣ “ተሰሐሩ” እያሉ ከመስጂድ በእስፒከር ማወጅ ያለ ሸሪአዊ ማስረጃ ሊገባበት የማይገባ አላስፈላጊ ምግባር ነውና “አበጀሁ” ብለው ከማጥፋት ይጠንቀቁ፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡