Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢኽዋን የISIS የጡት አባት ነው !

ኢኽዋን የISIS የጡት አባት ነው !
ዛሬ የአረቡ አለም ላይ ለመቶ ሺዎች የሚቆጠር የሙስሊሞች ሞት ተጠያቂው ማንም ሳይሆን ኢኽዋን ነው ። ይህንን አይክዱም ።
ቱኑዚያ፣ ሊቢያ፣ ሚስር፣ ሶሪያ ወዘተ የተበጠበጠው በኢኽዋን ስውር እጆች አማካኝነት ነው። ሙስሊም መሪ ላይ ማመፅን የሚከለክሉ አሐዲሶች ወደጎን ወርውሮ ለሙስሊሞች እልቂትና የጠላት የበላይ መሆን አሁንም እየሰራ ይገኛል። ሶሪያ ላይ የተወለደው የIS ቡድን አባትም ማንም ሳይሆን ኢኽዋን ነው። ዛሬ ሊቢያን ያለመሪ አስቀርቶ ሰው ለሰው እንደ አውሬ እንዲባላ ደም የጠማው IS በሊቢያ ምድር አላፊ አግዳሚውን እንዲቀላ ያመቻቸለት ማንም ሳይሆን ኢኽዋን ነው።
የሊቢያው መሪ ሙሐመድ ቃዛፊ ተገድሎ ሕዝቡ ያለ መሪ እንዲቀርና እርስ በርሱ እንዲባላ የቃዛፊን ስህተቶች እያነሳ “ግደሉት! ግደሉት! ” ሲል የነበረው ማንም የሱና ዑለማ ሳይሆን ፈላስፋው የኢኽዋን መሪ ዩሱፍ አል ቀረዷዊ ነበር።
ይሀው ከታች ያለውን ተስፈንጣሪ ተጭናቹ ስሙት
https://www.youtube.com/watch…

በተመሳሳይ ለዛሬዎቹ የ IS ወሮበላዎች ንድፈ ሓሳባዊ ሰው የሆነው ማንም ሳይሆን ሰይድ ቁጥብ የተባለ ራፊዲ፣ ኸዋሪጅ ኢኽዋኒ ነው ። ኦሳማ ቢን ላዲን የምን አባል ነበር? የኢኽዋን ። አይመን አልዘዋሂሪ የተባለው የዘመናችን ዙል ኹወይሲራ የምን ቡድን የቅርብ ሰው ነበር? የኢኽዋን። የዛሬዎቹም ኸዋሪጆች እንደድሮዎቹ በኢኽዋን ጓዳ በኩል የወጡ ጭራቆች እንጂ ሌላ አይደሉም ። እስኪ ከታች ያለውን ምስል ተመልከት! የኸዋሪጁ ቡድን አባል የማንን ኪታብ ያነባል? የሰይድ ቁጥብን ፊዚላሊ ሸይጧን የተሰኘውን ኪታብ ነው። ይሄ ኪታብ ነው ከሰውነት ወደ አውሬነት የሚቀይራቸውም።
ቀረዷዊ ለኛም ኢትዮጵያውያን ፈታዋ ሰጠ አሉንና የኛዎቹ የፌስቡክ ጂሐዲስቶች ቪዲዮ ለቀቁልን ። ጭራሽ?
ቆይ ደሞ ምን ፈለገ ከኛ? ሙስሊሙ እንዲጨፈጨፍ? ከዚህም በላይ አንገቱን አቀርቅሮ እንዲኖር?
ይሀው ስሙት
https://www.youtube.com/watch…
ለዚያም ነው ዑለማዎች ከጥንት ጀምሮ ኢኽዋንን እየተከታተሉ የሚያጋልጡት ። አንተም IS ማጋለጥና መቃወም ስትሻ ግንዱን ትተህ ቅርንጫፉን አትቁረጥ ። ኢኽዋንን ተቃወም አጋልጥ ያኔ መሠረቱን ንደሀል። ያለበለዚያ ግን «አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ..» ይሆንብሃል ።

Post a Comment

0 Comments