Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለው ጂሐድን (ተውሒድና ሱናን የበላይ ለማድረግ በአላህ መንገድ ላይ መታገል)'ን ከነፍሶቻችን ከቤተሰቦቻችን ከሚስቶቻችን ከልጆቻችን ከንብረታችን .... የበለጠ እንወዳለን!

Abubeker Siraj's photo.
ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለው
ጂሐድን (ተውሒድና ሱናን የበላይ ለማድረግ በአላህ መንገድ ላይ መታገል)'ን
ከነፍሶቻችን
ከቤተሰቦቻችን
ከሚስቶቻችን
ከልጆቻችን
ከንብረታችን .... የበለጠ እንወዳለን!
ነገር ግን ለሰላት ሸርጥ (ማዕዘናትና ቅድመ ዝግጅቶች) እንዳሉት ሁሉ ለጂሐድም አሉት!
ዘወትር በዱዓችን የማንረሳቸው በየትኛውም የአለማችን ክፍል ያሉት ሙስሊም ወንድሞቻችን እና እሕቶቻችን በኩፋሮች በሚደርስባቸው ግፍና በደል ልባችን ክፉኛ ቢያዝንም የጂሐድ አንዱና ዋነኛው ሸርጥ የሆነው «አቅም» ስለሌለን ከዚህ ጭንቅና መከራ አውጥቷቸው በጠላቶቻቸው ላይ የበላይነትን እንዲያጎናፅፋቸው እያለቀስን ለአላህ ዱዓ እናደርጋለን ። አዎን «ዱዓ የሙዕሚን መሳሪያ ነው» ዛሬ ግን የዱዓን ክብደት ያልተረዱ ሰዎች በንቀት ይመለከቱታል። አላህ እኛንም እነሱንም ይምራን።
በተመሳሳይ ይሄ የጠላት በኛ ላይ የበላይነት የመጣበትን መንስዔ ከስሩ ነቅለን ለመጣል ቀን ከሌት እንጥራለን ። እሱም ተውሒድና ሱናን ማስተማር ነው ። አዎን! ጠላት እኛ ላይ የበላይ ሊሆብን የቻለው በታንክና በሚሳዒል ብሎም በጠንካራ ወታደራዊ ስልትና በኒውክለር ቦምብ ሳይሆን በኛው በራሳችን ድክመት ነው። ድክመታችንም ከሽርክ ጀምሮ ቢድዓ እያለ ወደታች የሚዘልቀው ከባባድ ወንጀሎች ውስጥ ስለተዘፈቅን ነው ።
{{ ﻭَﻣَﺎ ﺃَﺻَﺎﺑَﻜُﻢْ ﻣِﻦْ ﻣُﺼِﻴﺒَﺔٍ ﻓَﺒِﻤَﺎ ﻛَﺴَﺒَﺖْ ﺃَﻳْﺪِﻳﻜُﻢْ ﻭَﻳَﻌْﻔُﻮ ﻋَﻦْ ﻛَﺜِﻴﺮٍ}} [ ﺍﻟﺸﻮﺭﻯ : 30]
(( ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር፣ እጆቻችሁ በሰሩት (ኀጢያት) ምክንያት ነው፤ ከብዙውም ይቅር ይላል።)) [አልሹራ 30]
አላህ እንደነገረን መልዕክተኛው በብዙ አሐዲሶች እንዳስገነዘቡን ጠላት ከእኛ የበላይ መሆኑ ወይንም የአላህ ቁጣ በኛ ላይ የማየሉ ምክንያት እኛው በሰራነው ሃጢዓት ነው። ከሃጢዓቶች ሁሉ የከፋው ድግሞ ሽርክ ነው ። ከጂሐዶች ሁሉ በላጩ ጂሐድ ደግሞ ሺርክን መቃወም ተውሒድን ማስተማር ነው። :: ለዛም ነው የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዓለይሒ ወሰለም ለትጥቅ የጂሐድ ጦርነት ዝግጁ ባልነበሩበት ወቅት (ማለትም አቅማቸውን ባላጎለበቱበት ሰዓት) ምንም እንኳን የመካ ሙሽሪኮች አካበዋቸው እየጨቆኗቸው ቢሆንም አላህ ግን ትልቁን ጂሐድ እንዲያደርጉ ነገራቸው ። ይህ ትልቁ ጂሐድ ምን ነበር?
{{ﻓﻼ ﺗﻄﻊ ﺍﻟﻜﺎﻓﺮﻳﻦ ﻭﺟﺎﻫﺪﻫﻢ ﺑﻪ ﺟﻬﺎﺩًﺍ ﻛﺒﻴﺮًﺍ}} [ﺍﻟﻔﺮﻗﺎﻥ 52]
(( ከሐዲዎችንም፣ አትታዘዛቸው፤ በርሱም ታላቅን ትግል (ጂሐድን) ታገላቸው)) [አልፉርቃን 52]
የኢስላም ሊቃውንት እንደሚሉት ይህ አንቀፅ የወረደው ነቢዩ ሙሐመድ መካህ በነበሩበት ጊዜ ነው (ከሒጅራ በፊት) ። መካህ በነበሩበት ሰዓት ለትጥቅ ትግል የሚሆን አቅምና ጉልበት አልነበራቸውም ። ግን አንድ መሳሪያ ብቻ ነበራቸው እሱም አንደበታቸው ነበር ። እናም ሰውን ወደ ተውሒድ ይጣሩ ሽርክን ደግሞ ከነቤተሰቦቿ ያወግዙ ነበር ። ለዚህም አላህ የተውሒድን ጥሪ «ትልቁ ጂሐድ» ሲል ጠራው።
ቀድሞውኑ የየትኛውን ጂሐድ (የትጥቅ ትግልም ይሁን የአንደበት ትግል) አላማው እና ኢላማው ተውሒድን ለማንገስ እና ሱናን የበላይ ለማድረግ ነው ። ይህ ደግሞ ትልቅ ወደ አላህ መቃረቢያ መንገድ ነው። በአላህ መንገድ ላይ እንሰዋለን ። ከሞትንም ጀነትን እንከጅላለን ። ከሱ ካፈገፈግንም አሳማሚውን የአላህ ቅጣት (ጀሃነምን) እንፈራለን ።
ግን ... ከላይ እንደጠቀስኩት ሽንት ቤት አጠቃቀም እንኳን ያስተማሩን ነቢይ ጂሐድን ግን እንደፈለጋቹ ተግብሩት አላሉንም! ሸርጦቹን አይነቶቹን በደንብ አስተምረውናል ።
ወደ አላህ መቃረቢያ የሆኑ ተግባራት ሁለት መስፈርቶችን ሟሟላት የግድ ይላቸዋል ። እነሱም
1) የአላህን ፊት ብቻ ከጅለን መስራት ሲሆን
2) የመልዕክተኛውን ፈለግ (ሱና) የተከተለ መሆን አለበት
ይህ በጥቅሉ የላኢላሃ ኢለላህ ሙሐመዱን ረሱሉላህ ትንታኔ ነው ።
ላኢላሃ ኢለላህ ያለ ሰው ሙሐመዱን ረሱሉላህ እስካላለ ድረስ አይድንም ። የአላህን ፊት ብቻ ከጅሎ ቢሰራ የነቢዩን ፈለግ እስካልተከተለ ድረስ ስራው ዋጋ የለውም ። የነቢዩን ፈለግ ተከትሎ የሰራው መልካም ተግባር ቢኖርም የአላህን ፊት ብቻ ከጅሎበት እስካልሰራው ድረስ ስራው ወደራሱ ተመላሽ ይሆናል እንጂ አላህ አይቀበለውም ።
ይህን መንደርደሪያ ካደረግኩ ዛሬ ላይ አንዳንድ ሰዎች ጂሐድን በፈለጉት መልኩ ይተረጉሙታል። አንዳንዶቹ እንደ አይ ኤስ ያሉ የኸዋሪጅ ቡድኖች ጂሐድን ንፁሃንን በመግደል ብሎም ሙስሊሞችን ጭምር በማክፈር መቅላት ፣ ኢስላም ነፍስን ማጥፋት በፅኑ እየተቃወመ እነሱ ግን አጥፍቶ ማጥፋትን አንድ የጅሐድ መንገድ አድርገው ይስሉታል ።
ይህ ምንም የአላህ ፊት ተከጅሎበት የተሰራ ስራ ቢሆንም እንኳን የነቢዩና የባልደረቦቻቸውን ፈለግ ያልተከተለ ዘግናኝና አስነዋሪ ተግባር በመሆኑ ውድቅ ተግባር መሆኑ አያጠራጥርም ። በመሠረቱ እነኚህኞቹም ሆኑ አብዛኛው የዛሬው “የጂሐዲስት ቡድን” ብለው የሚሰይሙት እንደ አልቃዒዳ፣ አልሸባብ፣ በሮኮሃራም የመሳሰሉት የኸዋሪጅ ቡድኖች አላማቸው ተውሒድን የበላይ ማድረግ ሳይሆን ስልጣንን መቆናጠጥ ነው ።
ሌሎቹ ደግሞ እንደ ሐማስ ፣ ሒዝቡ ተህሪር ፣ ኢኽዋን ያሉ ቡድኖች ከላይኛዎቹ ጋር የአይዲዮሎጂ ቁርኝት ቢኖራቸውም መዳረሻቸውን ግን እንደየሁኔታው እየቀያየሩ እንደ አስፈላጊነቱ መልክና ይዘታቸውን ቀይረው ይንቀሳቀሳሉ ። ለምሳሌ አስፈላጊ ከሆነ ዲሞክራሲያዊ (በብዙ ዑለማዎች ስምምነት ዲሞክራሲ ኩፍር ነው) ምርጫ ላይ በመሳተፍ ፣ ከጠላት ጋር በመወገን ጥቅማ ጥቅሞችን በመቀበል ፣ አቅም እና ጉልበት ሳይኖራቸው ጠላትን በመተናኮስ ሙስሊሙን በማስጨረስ (ለራሳቸው ፕሮፓጋንዳ ለማዋል) ፣ የአይሁዶችን ባሕል ሙስሊሙ ዘንድ በመሰግሰግ ( ለምሳሌ በነሺዳና ድራማ ሕዝቡን ማነሳሳት፣ የፊኛ መልቀቅ ሰልፍ፣ አፍ ላይ ፕላስተር የማድረግ ሰልፍ፣ ከfree mason የአይሁድ ቡድን በወሰዱት መርሆ መሠረት ተውሒድ የያዘውንም ያልያዘውንም ሙሽሪክ አንድ ነን ፣ ወንድሞቻችን እያሉ ድጋፍና ድምፅ በመሰብሰብ በመሳሰሉት) ይህን አካሄዳቸውን «ትግል» ወይንም «ጂሐድ» ብለው ይጠሩታል።
ይህም ለሥልጣን ተብሎ ከመሰራቱ ባሻገር ፍፁም የመልዕክተኛውን ፈለግ ያልተከተለ በመሆኑ ውድቅ መሆኑ አያጠራጥርም ።
ከጥንት ጀምሮ ፈር የለቀቁ የቢድዓ ቡድኖችን የኢስላም ሊቃውንት ያርሟቸዋል ። አካሄዳቸው ልክ እንዳልሆነና በአንደበታቸው እንደሚደሰኩሩት «ለሙስሊሙ የቆሙ» ከሆኑ አላማቸውን ማድረግ ያለባቸው ተውሒድ ላይ እና ሱና ላይ ለሱም መታገል እንዳለባቸው ይገስፇቸዋል። ሆኖም ከጥንት ጀምሮ እንደሚሰማው ከነዚህ ቡድኖች አንደበት ለዚህ ተግሳፅ የሚሰጡ መልሶች ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ናቸው ። እሱም ..
« የሴት ልጅ የወርሃዊ ዑደት (የወር አባባ) ዑለማ ናቹ እንጂ ተጨባጭ ክስተቱን አያውቁም» ፤ « የቤተ መንግስት ፍርፋሪ ለቃቃሚዎች» (ይህ ክስ እነዚህ ቡድኖች ምን ያህል ከሥልጣን ዓላማ እንደተነሱ ያሳያል) ፤ « ቅጥረኞች፣ ካድሬዎች» የመሳሰሉት ናቸው ። ብዙውን ጊዜ ሕዝቡ እንደ አንደበታቸው ለሱ የቆሙ መስሎ ስለሚሰማው ስለነዚህ ሰዎች ማንነት ሲነገረው በእሺታ አይቀበልም ።
ነገር ግን የረሱልን ሱና ጥሶ የጂሐድን ትርጉም አዛብቶ ለኢስላም የበላይነት ሳይሆን በተቃራኒው ለኢስላም የበታችነት የሚታትር ቡድን ምን ኸይር አለው ። እስኪ ይህን ጥያቄ መልሱልኝ?
አላህ ቅኑን መንገድ ይምራን

Post a Comment

0 Comments