Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዙሕድን ከሰለፊ ዑለማዎች እንማራለን! ሸኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊህ አል ዑሰይሚን (رحمه الله)

ዙሕድን ከሰለፊ ዑለማዎች እንማራለን!
ሸኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊህ አል ዑሰይሚን (رحمه الله) ከተወሰኑ ተማሪዋቻቸው ጋር መስጂድ በራፍ ላይ ቆመው ከተማሪዋቻቸው የሚመጣን ጥያቄ እየመለሱና ስለዲን ጉዳዮች እየተወያዩ ባሉበት አጋጣሚ አንድ በጣም ውድ የሆነ የቅንጦት መኪና አጠገባቸው መጥቶ ቆመ ። ከዚያም ሹፌሩ ከመኪናው ላይ ወርዶ የመኪናውን ቁልፍ ለሸኽ ዑሰይሚን ሰጥቶ ከእከሌ እከሌ የተባለ ግለሰብ የተላከላቸው ስጦታ መሆኑን ነገራቸው። ሸኹ ግን መቀበል እንደማይፈልጉ ነገሩት ነገር ግን ሹፌሩ እንደምንም አግባብቶ ቁልፉን ለሸኹ ሰጣቸው ። ሸኹም ተቀብለው ቁልፉን እያሽከረከሩ ከተማሪዎቻቸው ጋር ውይይታቸውን ቀጠሉ ። ወደመኪናው ዞርም ብለው አላዩም ። በዚህ አጋጣሚ አንድ ወጣት ወደ ሸኹ መጣና ሰላምታ ካቀረበ በህዋላ “ያ ሸኽ! ሰርጌ ዛሬ ማታ ነው። በዝግጅቱ እንደሚገኙልኝ ተስፋ አደርጋለው” አላቸው ። ሸኹ ግን ከሱ በፊት ሌላ ቀጠሮ እንዳለባቸውና መገኘት እንደማይችሉ ነገሩት። ወጣቱ ግን ሸኹ እንዲገኙለት ጎተጎታቸው ። ሸኹም በትሕትና መገኘት እንደማይችሉ ካስረዱት በህዋላ ..
“ለዚህ መኪና ይህም ቁልፍ ተቀበለኝ። ለሰርግህ ስጦታ ሰጥቼሃለው።” አሉት ። ወጣቱም ቁልፉን ተቀብሏቸው መኪናውን ይዞ ሄደ ።
ሸኹ ምንም እንዳልተፈጠረ ነገር ከተማሪዋቻቸው ጋር ውይይታቸውን ቀጠሉ ።

[ሽይኽ ፈላህ አስ–ሱነይድ : አድ–ዱር አስ–ሰሚን ፊ ተርጀማቲ ፊቕሁል ዑማ አል ዓላማ ኢብኑ ዑሰይሚን ገፅ 218]

Post a Comment

0 Comments