Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የፊረቅ አመጣጥና ቅደም ተከተሉ

بسم الله الرحمن الرحيم
الحمدلله والصلاة والسلام على رسول الله
ውድ ወንድሞችና እህቶች የፊረቅ አመጣጥና ቅደም ተከተሉ በእስልምና ያደረሰው ከባድ ጉዳት በነብዪ ሱና ተከታዪች ሙብተዲዓ ያደረሱት ግፍና በደል ሰለፎች እስልምናን በፍልስፍና ይሁን በአስተያየት እንዳይበከል ለመከላከል ያደረጉት ከፍተኛ ጥረትና ለደረሳቸው ከፍተኛ በደል ምን ያህል እንደታገሱ የሚያሳይ በታላቁ ዐሊም ሸይኽ መሐመድ አማን አልጃሚ
رحمه الله
العقيدة الاسلامية وتاريخها
በሚል ኪታባቸው ስለ ፊረቅ አመጣጥ እና ቅደም ተከተል አጠር ባለ መልኩ ለማየት እንሞክራለን የመጀመሪያው ፊርቃ እንግዲህ ኸዋሪጅ ሲሆኑ በዓሊ ኢብን አቢ ጣሊብ
رضي الله عنه
ዘመን የወጡ ሆነው ሸይኹ رحمه الله
እንደሚገልፁት ዓቂዳቸው ማንኛዉም ( الكبائر) ታላለቅ ማዕስያ አለመስራት የእምነት መሰረታዊ እንደሆነ በመቁጠር በዚህ መሰረት ምክንያት ማንኛውም ከባኢር የሰራ ሁሉ እንደከፈረና ከእስልምና ጠቅልሎ እንደወጣ አድርገው ያዩት ነበር ይህን ብቻም አይደለም በሙስሊም መሪ ላይ መውጣት እንደሚቻልና እንዲያውም በጥሩ ነገር ከማዘዝና ከመጥፎ ነገር እንደመከልከል አድርገው ይቆጥሩታል ሸይኹ ቀጥለው አንዳንድ ዑለማዎች እንደሚያመለክቱት ኸዋርጆቹ በ ሐሩራእ በተባለ ቦታ ስድስት ሺ የሚሆኑ ተሰባስበው ለጦርነት እንደተዘጓጁ ዓብደላህ እብን ዓባስ رضي الله عنه ያለውን ጥሩ ልብስ ለብሶ ኸሊፍው ዐሊይ እብን አቢይ ጣልብን رضي الله عنه አስፈቅዶ እነሱ ጋር ከሄደ ቦሃላ ሰላምታውን አቅርበላቸው እነሱም መርሐበን እብን ዐባስ ካሉ በሃላ
١ ለምንድ ነው ይህን ልብስ የለበስከው ብለው ጠየቁኝ አለ እሱም ምን ችግር አለበት ነብዩ صلى الله عليه وسلم
ከዚህ የበለጠ ልብስ ይለብስ ነበር الله ም በቁርአኑ በሱረት አል አዕራፍ ላይ አያ 32 እስቲ በላቸው ማን ነው الله በምድር የፈጠረውን ቆንጆ የሚያምር ነገርና ጥሩ የሆነ ምግብ ሐራም ያደረገው ቀጥለው ምንድ ነው ያመጣህ ብለው ጠየቁኝ አለ እሱም ከነብዪ صلى الله عليه وسلم ሰሐቦች ከሙሃጅሪንና ከአንሷር እነሱ ስለናንተ ምን እንዳሉ ልነግራቹህ ምክንያቱ ይህ ቁርአን በነሱ ላይ ወረደ ከናንተ የበለጠ ደሞ ትርጉሙ ያውቁታል ከነሱም አንድ እንኳን ከናንተ ጋር የለም ከዛ አለ ቀጥሎ ከነሱ ግማሽ ከቁረይሺይ ጋር አትከራከሩ ምክንያቱ الله እንደነሱ የሚከራከር የለም ብለዋል አሉ ፊታቸው ሳይ አለ እንደነሱ በብዛት ዒባዳ የሚያደርግ እንደሌለ ያስታውቃል ቀጠሎ ከነሱ ግማሽ እስቲ የሚለውን እንስማ ሲሉ እኔም በነብዪ የአጎት ልጅ የሆነው ዓሊና በሙሃጅሪንና በአንሷር ምንድ ነው ቅሬታቹህ እነሱን ሶስት ነገሮች አሉ ምንና ምን ናቸው አንዱ አሉና በዲኑ ላይ ሰዎች ፍርድ እንዲሰጡ አደረገ الله ግን የሚለው ፍርድ ለ الله ብቻ ነው ይላል በሱራ አንዓም አያ 57 ሰዎች ፍርድ መስጠት አይገባቸውም
እኔም ይህች አንድ አልኩኝ አለ ቀጥሎ ሌላ ሁለተኘሰውስ ምንድ ነው ስል ከውጊያ በሃላ( ከጂሀድ ) የሚወሰደውን (ቐናኢም ), አልወሰደም የተዋጋቸው ኩፋር ከሆኑ መውሰድ ነበረበት ሙስሊሞች ከሆኑም መዋጋት አልነበረበትም
( ይህ እንግዲህ እኛን የማይመለከት ከዑስማን እብን ዓፍን رضي الله عنه ግድያ በሃላ በሶሐቦች ለተፈጠረው አለመስማማት አስመልክተው ነው)
3ኛው አሉ ራሱን ከአሚር አልሙእሚኒን አገለለ አሉ
እብን ዓባስ رضي الله عنه ታድያ እኔ ከቁርአንና ከሱና መልስ ብሰጣቹህ ምን ትላላቹህ አለ እነሱም እሺ አሉት
ለመጀመሪያው ጥያቄአቹህ መልሱ አለና الله በብዙ ነገሮች ሰዎች ፍርድ እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው ምሳሌዎች ከጠቀሰ በሃላ ከነሱም ባልና ሚስት ሲጣሉ በማሃከላቸው ከባልና ከሚስቲቱ ዘመዶች ተመርጠው እንዲያስታርቁ አዘዋል ካለ በሃላ ስለዚህ ይህ ደሞ ልክ እንደዛው ነው ብሎ አስረዳቸውና የመጀመሪያው ጥያቄ ተመለሰ አላቸው እነሱም አዎ ካሉ በሃላ ሁለተኛው ደሞ አላቸው ለመሆኑ እናንተ የምትሉት እናታቹህ ዓኢሻን ልትማረክና በሌላ ምርኮኛ ሴት ላይ የሚደረገውን እሷ ላይ ሊደረግ ትፈልጋላቹህ አዎ ካላቹህ እንግዲህ ከፍራቹሃል አይ እናታችን አይደለችም ካላችሁም ከፍራቹሀል ስለዚህ በሁለት ጥመቶች መሃል እየዋለላቹህ ነው ካላቸው በሃላ እርስ በርሳቸው ተያዩና አለ እሱም ቀጥሎ ተመለሰላቹህ ወይ ሲላቸው አዎ አሉት ሰዎስተኛው ደሞ አላቸው ነብዪ صلى الله عليه وسلم
ከ ዐሊይ ይበልጣል ነገር ግን ከሙሸሪኮች ስምምነት እያደረጉ በነበረበት ግዜ ዓሊይን رضي الله عنه
ይህ በ رسول الله እና ብለው ስምምነቱ እንዲፅፍ ሊያዙት ሲጀምሩ ሙሽሪኮች አንተ መልእክተኛ መሆነክን አናምንምና በስምህ ብቻ ይፃፍ ሲሉ ነብዩም
صلى الله عليه وسلم
اللهم إنك تعلم أني رسول الله
ካሉ በሃላ ያ ዐሊ አሉት ይህ ሙሐመድ እብን ዓብዱላህና በለህ ፃፍ ያሉት ግዜ ነብዪ صلى الله عليه وسلم ከነብይነታቸውም አላወጣቸውም ብሎ አስደናቂ በሆነ መልኩ መለሰላቸው ከዛ፣በሃላ ሁለት ሺ የሚሆኑ ሲመለሱ ቀሪዎቹ ኸሊፉው ዐሊ በከፈተባቸው ጦርነት እንዳሉ ተገድለዋል ከዚህ የምንወስደው ትምህርት ካለ እንግዲህ እነዚህ ሰዎች የተጣመሙበት ዋናው ምክንያት እስልምናን ከዋናው ምንጭ ከነብዪ ባልደረቦች አለመውሰዳቸው ነው እነዚህ ሰዎች ነብዪ صلى الله عليه وسلم
ስለ ኸዋሪጅ ምንነት በተለያዩ ሐዲሶቻቸው እንደገለፁልንና እብኒ ዓባስም رضي الله عنه ሁኔታቸው አይቶ እንደነገረን ሶላትና ቁርአንም ቢያበዙም ከቀጠተኛው የሱና መስመር በመውጣታቸው ምንም ሊጠቅማቸው አልቻለም ስለዚህ ስለ አንድ ሰው ላይ ፍረድ ከመስጠታችን በፊት ከዒባዳው ይልቅ የእምነቱ መስተካከሉ የግድ ማስተዋል
አለብን ይህን አስመልክተው የሰለፉ ዑለማዎች ብዙ ብለዋል ለምሳሌ አጁሪ رحمه الله )እንደሚለው የአንድ ኻሪጂ ዒባዳ ማብዛት ወይም ቁርአን በብዛት መቅራት አይድነቃቹህ )ዓቂዳው የተጣመመ ከሆነ ምንም ዋጋ የለውምና እንጠንቀቅ እኛም ዲናችን ከነዛ ከነብዩ
صلى الله عليه وسلم
ተወርሶ ከትውልድ ወደ ትውል የተላለፈውን ንፁህ እስልምና ከሚያስተምሩት ታማኝና አዋቂ ከሆኑ ዓሊሞች ብቻ እንውሰድ የተከታይ ወይም የአንጨብጫቢ ብዛት ዋጋ የለውም ዳዒ ነው ተብሎ ብዙ ሰዎች ቢያወድሱትም በእጁ ብዙ ቢያሰልሙም ትክክለኛውና ቀጥተኛው እምነት የማያስተምር ከሆነ ምን ዋጋ አለበት ተመልከቱ ሸይኹ رحمه الله ቀጠል አድርገው
هكذا يفعل سؤ الفهم وعدم التزيث وقلت البصيرة بأهله
አዎ ችኮላ ረጋ ብሎ አለማስተዋልና በትክክል አለመረዳት መጨረሻው እንዲህ ነው ካሉ በሃላ
وقد ظن الخوارج أنهم على شيئ فيما ذهبو إليه عندما خرجو على أمير المؤمنين علي بن أبي طالب وقاطعو المهاجرين والأنصار الذين نطق بهم القرآن وبه نطقو وقام بهم القرآن وبه قامو وهم خير هذه الأمة ن
١ ከዚች ኡማ በደረጃቸው ከፍ ያሉ ቁርአን በነሱ ተናግሮ እነሱም በቁርአን የተናገሩት እነዛ ቁርአን በነሱ ቁሞ እነሱም በቁርአን የቆሙት ከነብዩ ባልደረቦች ሙሃጅሪንና አንሷርን ተነጥለው እኛ በጥሩ ሁኔታ ነን ብለው ገምተው ነበር ነገር እነሱ በጥመት ነበር የነበሩት
ከነሱ الله ነጃ እንዲወጡ የፈለገላቸው በሶሐቢው ዓብደሏህ እብኒ ዓባስ رضي الله عنه ምክር ተቀብለው ተመለሱ ከዚህ አይነት ጥመት الله ይጠብቀን
ቀጥለው የመጡት ሺዓ ሆነው አጀማመራቸው ደሞ ዓሊ እብን አቢ ጣሊብን
رضي الله عنه
ላይ ቕሉው በማድረግ አሱን እስከመገዛትና ከዛም አልፈው ኢላህ ነው እስከማለት ስለደረሱ ኸሊፍወረ ዓሊ رضي الله عنه በተደጋጋሚ ቢያስጠነቅቃቸውም እንቢ ስላሉት ግማሾቹን በእሳት እስከማቃጠል ደርሰዋል ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በሙስሊሞች መሀል ፊትና ለመፍጠር ቆርጦ የተነሳ ዐብደሏህ እብን ሰባእ የተባለ የሁዲ እስልምና እንደተቀበለ በማስመሰል የዓሊ ወዳጆች ነን ከሚሉት ጎን በመሆን ነብዪ
صلى الله عليه وسلم
ዓሊ እብን አቢ ጣልብን رضي الله عنه ከኔ ቀጥሎ ኢማም መሆን አለበት ብለው ወሲያ ትተዋል እሱ ብቻ ሳይሆን እንዲያውም ዓሊ رضي الله عنه ከፊሉ ኢላህ ስለሆነ እንደማይሞትና ተመልሶም እንደሚመጣ ይናገር ጀመር የሱ ንግግርም የራፊዳ የሁሉም እምነታቸው መሰረት አድተርገው ወስደውታል
ከዛ በሃላ ቀደርያ መጡ የነሱ የጥመት መስራች ደሞ መዕበድ አል ጅሃኒ ይባላል ይህ ጠማማ ሰውየ በበስራ ከተማ በሙስሊሞች የማይታወቅ አዲስ እምነት ይዞ መጣ እሱም ማንም ባርያ የሚሰራው በ الله ዘንድ ከመስራቱ በፊት አይታወቅም የተፃፈም የለም ነገር ግን ይላል ይህ ጠማማ الله የኛ ስራ الله የሚያውቀው ከሰራነው በሃላ ነው ማለት ጀመር የዚህ ጠማማ እምነት መስራች የሆነው መዐበድ አል ጅሃኒ ይህን ጥመት የወሰደው ከአንድ ዩንስ አሷውሪ የሚባል ክርስቲያን ነው ተመልከቱ የሺዓ መስራች የሁዲ ነው የቀደርያ ደሞ ክርስቲያን ነው ለዚህም ምክንያት ነው ነብዪ صلى الله عليه وسلم የሁድና ክርስቲያንን እንዳንከተል ያስጠነቀቁን
ስለዚህ አኛም በዚህ ዘመን ካሉት ዘመናዊ ፍልስፍናዎች ርቀን ንፁህ ዲናችን ብቻ መያዝ ይኖርብናል
ይህ ጥመት በበስራና ባከባቢዋ ብዙ ፊትና ስለፈጠረ በዛ ግዜ የነበረው ኸሊፍ ዓብደላህ እብን መርዋን ለሐጆጅ ይሱፍ አሰቀፊ ትእዛዝ በማስተላለፍ የፊትና ባለቤቱ ይዞ የሚገባው ቅጣት ሰጥቶታል በዘመኑ የነበሩ የሰሐባና የታብዒን ዑለማዎች ቢድዓውን በሃይል አወገዙት ለምሳሌ ዓብደሏህ እብን ዑመር رضي الله عنه ይህን ጥመት ሲሰማ ከጥመቱና ከጥመቱ ባለቤት እሱ ( በሪእ) መሆኑን አመለከተ እንዲሁም ዓብደሏህ እብን ዓባስ
رضي الله عنه
ይህን ጥመት ሲሰማ ሰዎቹን በአካል ቢያገኛቸውና ገሮሮአቸው ይዞ ቢያንቃቸውና ቢገድላቸው ተመኘ ተመልከቱ ለዲኑ እንደኛ ጥመት እየተሰራ ወይም አዲስ ቢድዓ እያየን ችግር የለውም ብለን እንደምናልፈው ሳይሆን ለዲናቸው ምን ያህል እንደሚቆረቆሩ በግልፅ ያሳያል በሌላ በኩል ደሞ በጀብሪያ የሚሉም ተገኙ እሱም ቀደሪያ ከሚሉት በተቃራኒ ማንም ሰው የሚሰራው الله የፃፈለትን ብቻ ነው ማንኛውም ኸይር ይሁን ሸር የሰው ልጅ ምንም ምርጫ ሳይኖረው ነው የሚሰራው ይላሉ የ አህሉ ሱና አቋም ግን የነዚህ ሁለቱ ጥመቶች መካከል ነው አሱም ከ الله በስተቀር ፈጣሪ የለም ባሪያና ስራው የሚፈጥረው አንድ الله ብቻ ነው ሆኖም አንድ ባርያ ጥሩ ይሁን መጥፎ ለመስራትና ላለ መስራት ውሳኔ ማድረግ ይችላ : ከቀደሪያ ቀጥሎ ጃህሚያ ሌላ አስደንገጭ ጥመት ይዞ መጣ እሱም አንድ ጀዐድ ብን ድርሀም የተባለ ጠማማ الله ኢብራሂምን ኸሊል አላደረገውም ሙሳንም አላናገረም የሚል ከዛ በፊት የማይታወቅ ጥመት ይዞ መጣ ሆኖም በዛን ዘመን የነበሩ ዑለማዎችና መሪዎቻቸው ለዲናቸው የቆሙ ስለነበሩ ሰውየው ተይዞ በአንድ ጀግና ኻልድ አልቀስሪ የተባለ የዒራቅ አሚር በዒድ አድሐ ቀን የዒድ ሶላት ተሰግዶ ኹጥባ ካደረገ በሃላ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ለሱ የሚገባ ቅጣት አወረደበት ከኹጥባው በሃላ ኻልድ رحمه الله
أيها الناس ضحو تقبل الله ضحايكم ካለ ባሃላ
فإني مضح بالجعد بن درهم لأنه زعم أن الله لم يتخذ إبراهم خليلآ ولم يكلم موسى تكليمآ
ከዒድ ኹጥባ በሃላ እናንተ ሙስሊሞች ሆይ ኡድሒያችሁን እረዱ እኔ ጀዓድን በኡድሒያ ምትክ አርደዋሎህ ምክንያቱ ብሎ ያመጣውን ጥመት ገለፀላቸው ተመልከቱ ይህ የመሰለ አቋም ከመንግስቶች እንኳን በዘመናችን ባናገኝም በተቃራኒ ለሙብተዲዕ ጥብቅና የሚቆሙ ስታይ በጣም ያሳዝናል ለምሳሌ ጣርግ ስዌዳን የተባለው የኩዌት ጠማማ የሃይማኖት ነፃነት አስመልክቶ በእስልምናና በ الله ቅሬታህን ማሰማት ችግር የለውም ሲል ቢያንስ የኛ አቋም ምን መሆን ነበረበት የሚያሳዝነው ስንት ዳዒ ወይም ኡስታዝ የሚባሉ ሰዎች ለንደዚህ አይነቱ ጠማማዎች ጥብቅና ሲቆሙ ማይቱ ይገርመሰል ተመልከቱ የሱ ንግግርና የዑለማዎች መልስ
http://m.youtube.com/watch?v=JYm8RapbKnE:
አሳዛኙ ነገር ግን ጀዐድ ከመሞቱ በፊት መርዙን አሰራጭቶ ስለነበር የመርዙ ተለካፊ የሆነው ጀሀም ብን ሰፍዋን ይህን ጥመት በሱ ምትክ ለማስፉፉት ወደ ጥመቱ ጥሪ በማድረግ ከፉተኛ ጥረት አደረገ በዚህ ምክንያት ጀማሪው ጀዐድ ቢሆንም በጃሀም ስም ጃህሚያ የሚል ቅጥል ስም ወጣበት የዚህ ጥመት ሰነድ ወይም መሰረቱ ማወቅ ከፈለግን አንዳንድ ዑለማዎች እንደሚሉት ከአንድ የሁዲ አባን ብን ሰምዓን ጣሎት የተባለ ለነብዪ
صلى الله عليه وسلم
ስሕር ያደረገላቸው በይድ አዕሰም የተባለ የሁዲ የእህቱ ልጅ ነው ሆኖም ጀሃም የጥመት ጥሪውን ቀጠለ ሙስሊሞችን በ الله ስሞችና ባህሪዎች ላይ ጥርጣሬ ይጥልባቸው ጀመር ምክንያቱ የ الله ባህሪዎችን ለዲኑ ተቆርቋሪ በመምሰልና የ الله ን ባህሪና ስም በጭራሽ ይክድ ነበር: ይህ የጃህሚያ ፊትና በአስማእ ወሱፉት በእስልምና ታሪክ የመጀመሪያው ነው ይህ ቅጥል ስም ደሞ የ الله ስሞችና ባህሪዎች ሙሉውን ወይም ግማሹን የሚክድ ዑለማዎች ዘንድ ጃህሚ ተብሎ ይጠራ ጀመር የጃህሚያ ፊትና ሳያልቅ የሙዕተዚላ ፊትና ደሞ ብቅ አለ እሱም በአስማእ ወሲፋት ነው ተመልከቱ ሙስሊሞች እሰከዛ ድረስ እምነታቸው ከቁርአንና ሐዲስ ቀጥታ ይወስዱ ነበር ስለ الله ስምና ባህሪም በቁርአን ያገኙትን ያለ ምንም መፈላሰፍ ወይም መጠራጠር ይቀበሉት ነበር ነገር ግን የነዚህ ፈላስፋዎች መምጣት ለሙስሊሞች በእምነታቸው ጭቅጭቅና ጥርጣሬ እንዲመጣ ዋናው በር ከፈተ የዚህ ጥመት አጀማመር አስመልክተው ሸይኹ ሲናገሩ በታቢዒው በኢማም ሐሰን አልበስሪ ዘመን ዋስል እብን ዓጣእ የተባለ የሙዕተዚላ መስራች የሐሰን አልበስሪ ዒልም ተከታታይ ነበር ከሐሰን አልበስሪ ጋር በዓቂዳ ልዩነት ፈጥሮ ከመስጂዱ ሳይወጣ ከደርሱ በመራቁ ሙዕተዚል ተባለ የዚህ ፊርቃ ጥመት ልክ እንደ ጃህሚያ በዓቂዳ ጉዳይ በተለይም በአስማእ ወሲፉት ሆኖ ከጃህሚያ ለየት የሚያደርገው ግን ጃህሚያ አስማእና ሲፉት ሲክዱ ሙዕተዚላ ግን አስማእን ሳይክዱ ሲፍት ብቻ ይክዳሉ ስሞችም ቢሆን አምነናል ቢሉም ነገር ትርጉም እንደሌለው አድርገው ይወስዱ ነበር ምክንያቱም እነሱና ጃህሚያ የሚሉት የተለያዩ ስሞችን ባህሪዎችን ለ الله ማፅደቅ አንችልም ምክንያቱ እሱ አንድ ነው በሚል አጉል አባባል ነው ይህ የሚያመለክተው ደሞ ማንም ሰው ከ الله የተላከውን ቁርአን ትቶ የራሱ ፍልስፍና ሲከተል በጥመት ይወድቃል በአሁኑ ዘመን የአሽዓሪያና የአሕባሽ ፊትና መሰረቱም ከዚህ ከጃህሚያና ከሙዕተዚላ ነው ማለት ነው ሌላው ሙዕተዚላን ከ ጃህሚያና ከሌሎች ፊረቆች ለየት የሚያደርጋቸው ደግሞ ከጥመታቸው ጋር የተያያዘ አምስት ህግጋት አውጥተዋል እነሱም የመጀመሪያም ተውሒድ ብለው የጠሩት ልክ በአሁኑ ሰአት አሕባሽ እንደሚሉት የ الله ባህሪዎች ከ ዓርሽ በላይ መሆኑንና ሌላላም ባጠቃላይ ለ الله ጥራት ለማድረግ በሚል ስም
ሙዕተዚላ እንግዲህ እንደልብ ጥሪያቸው ማስፉፉት ስለቻሉ ከሌሎች ይበልጥ የከበደ ፊትና እየፈጠሩ መጡ የ الله ሲፍቶች በግልፅ በመካድ በተለይም ቁርአን መኽሉቅ ነው በማለት የሚለው ቢድዓቸው ብዙ ፊትና መፍጠር ጀመሩ ይህም የሆነበት ምክነወያት የዘመኑ ኸሊፍ ከነበረው ማእሙን ብን ሃሩን ረሺድ በሙዕተዚላዊች ምክንያት ከሱ በፊት የነበሩበት የሰለፎች ዐቂዳ ትቶ የነሱ ፍልስፍና በመቀበል በ ሁለት መቶ አስራ ስምንት አመት ህጅሪ አከባቢ ወደ ምክትሉ ኢስሐቅ እብን ኢብራሂም ሰዎች ቁርአን መኽሉቅ ነው እንዲሉ ጥሪ እንዲያስተላልፍ አዘዘው እሱም በበኩሉ የኸሊፍውን ትእዛዝ ለመፈፀም ዑለማዎቹን አሰባስቦ የኸሊፉው ትእዛዝ ነገራቸው እነሱም በፍፁም አይሆንም አሉ ነገር ግን ከብዙ ማስፈራራት በሃላ ግማሾቹ ውስጣቸው እንኳን ባይቀበለውም ህይወታቸውን ለማዳን ሱሉ በቃላቸው ተስማሙ ይህን የኩፍር ቃል አንቀበልም ብለው በቃላቸው ከፀኑት ዑለማዎች እንግዲህ ኢማም አህል ሱና ተብሎ የተሰየመው ኢማም አሕመድ ብን ሐምበል ነው ለዲኑ ሲል ብዙ ስቃይ አሳለፈ ብዙም ተገረፈ ነገር ግን ከአቋሙ ምንም ፈንክች አላለም ይህን ፊትና ከነበረው መንግስት እንኳን ቢሆንም እሱ በመታሰሩ በመሰቃየቱ በመገረፍ ሰዎች እንዲሰባሰቡ ጥሪ አላደረገም እንዲያውም ከእስር ከወጣ በሃላ የነበሩት ፉቀሃዎች ወደሱ ተሰባስበው በመሄድ ይህን መንግስት ምን እንዳደረገን እያየህ ነው ከዚህ የከፍ ፊትናም የለምና ስለዚ አንፈልገውም ሲሉት እሱም ምንም እንካን የደረሰበት በደል ከባድ ቢሆንም ከሸሪዓው ትእዛዝ መውጣት ስላልፈለገ አይ አይሆንም የናንተና የሙስሊሞችን ደም ጠብቁ እኔ በዚህ ነገር አልተባበራችሁም ብሎ ትእግስት እንዲያደርጉ አፀናናቸው ተመልከቱ በእምነቱ ፀና ለራሱ ቂም ለመበቀል ብሎም ፊትና እንዲቀሰቀስ አልፈቀደም ተመልከቱ እንግዲህ ሁኔታዎች እንዴት እንደተቀያየሩ ትናንት ጀዐድ ብን ድርሃም የዚህ ፊትና ቀስቃሽ በዒድ ቀን እንደ በግ ታረደ ሆኖም በመርዙ የተለከፍት ሰዎች ግን እንደምንም ብለው ከግዜ በሃላ ነገሩን በተገላቢጦሽ እንዲሆን አደረጉት ይህ በኡማው ታሪክ እጅግ ከባድ የሆነ ። ፊትና የወረደበት ግዜ ነበር ማእሙን ሰባተኛው ኸሊፉ ነበር እሱ ከሞተ በሃላ ከሱ ቀጥሎ የመጣው ስምንተኛው ኸሊፍ ሙዕተስምም ፊትናው እንዲቀጥል አዘዘ ቀጥሎም ዘጠነኛው ዋስቕ ቢሏህ ቀጥሎ እሱ ከሞተ በሃላ ፊትናው አለቀ አስረኛው አልሙተወክል ከመጣ በሃላ ፊትናው እንዲነሳ አዘዘ ተመልከቱ የቢድዓና የሙብተዲዖች መዘዝ ይህን አስመልክተው ስለ ኸልቅ አልቁርአን ፊትናና ኢማም አሕመድ የደረሰው ድብደባ የፊትና አነሳስ እጅግ ልብ የሚነካ ሙሐደራ በሸይኽ ረስላን አብረን እናዳምጥ http://m.youtube.com/watch?v=_eKkbhmm0zw

Post a Comment

0 Comments