Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አመድ በዱቄት ይስቃል

“አመድ በዱቄት ይስቃል”
በቅርቡ “አልወለደም አልተወለደም” የሚለውን የቁርኣን አንቀፅ አንዱ ክርስቲያን “ይህን ለጆሮ የማይጥም መፈክር…” እያለ ሲቃወም አይቼ ተገረምኩኝ፡፡ እውን ይሄ ከስላሴ ይደብራል? እስኪ እባካችሁ ለአፍታ እራሳችሁን ገለልተኛ አድርጉና አወዳድሩ፡፡
1. “ፈጣሪ አልወለደም አልተወለደም” ከሚለውና
2. “ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው” ከሚለው የትኛው ነው ለጆሮ የማይጥመው? ኧረ እባካችሁ በህሊናችን ላይ አንዝመት፡፡ ዘላለማዊ ህይወትን የሚያልም ሰው ህሊናው የማይቀበለውን እንቆቅልሽ እያስተጋባ ፅድቅን ያልማል እንዴ?
“እንደ እግዚያብሄር ያለ ማንም የለም” እያላችሁ አይደል? ታዲያ እኮ “ወለደ ተወለደ” ስትሉ እግዚአብሄራችሁን ከፍጡር ጋር እያመሳሰላችሁት ነው::
ብቻ “ፈጣሪ አንድም ነው ሶስትም ነው” የሚለውን የስላሴ እንቆቅልሽ ለመቀበል በራስ ህሊና ላይ ማመፅ የግድ ይላል፡፡ አእምሮን “እስዊች ኦፍ” ማድረግ፡፡ ያለበለዚያማ እንኳን የአዋቂ የህፃንም ጭንቅላት አይቀበለውም፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ አንዴ በእንቁላል፣ ሌላ ጊዜ በፀሀይ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በዛፍ፣… እያመሳሰሉ የራሳቸውን ህሊና ለመሸወድ የሞት ሽረት ትግል ያደርጋሉ፡፡ ለአእምሯቸው ረጋ ብሎ የሚያስብበት ፋታ አይሰጡትም፡፡ “እንዴት ብሎ” ከተባሉ አንዱ የሚሰጠውን ማብራሪያ ሌላው አይደግመውም፡፡ ምክኒያቱም በመረጃ ሳይሆን በደመ ነፍስ ነውና የሚጓዙት፡፡ አስር ክርስቲያኖች በዚህ ጉዳይ ቢናገሩ አስራ አንድ አይነት አቋም ያንፀባርቃሉ፡፡ እስኪ ይታያችሁ ሰው ህሊናው እያለ እንዴት ብሎ አንድ ከሶስት ጋር እኩል ነው ብሎ ያምናል? ደግሞ ማሳመን ሲያቅታቸው “መንፈስ ስላላደረብህ ነው፡፡ ብታምን ይገባሃል” ይላሉ፡፡ ምነውና ቀድሞ ሳይገባኝ አይኔን ጨፍኜ የማምነው?!! ደግሞስ እሱ ምን የሚሉት መንፈስ ነው? የት ነበር “መንፈስ ያለው ሁሉ አብዷል” የሚል ያነበብኩት? እውነት ብሏል፡፡ የሆነ የቡሎን መላላትማ አለ፡፡ እርግጠኛ ነኝ በእንዲህ ያለ ተልካሻ ምክኒያት ተናጋሪው ብቻ ነው የሚሸወደው፡፡ እሱ እራሱ አንድ ከሶስት ጋር እኩል ሆኖለት ሳይሆን እንዲሁ ከወረሰው ከንቱ እምነት መሸሽ ሽንፈት ስለሆነበት ነው፡፡ “ወደው የዋጡት ቅልጥም ከብርንዶ ይጥም”
https://www.facebook.com/IbnuMunewor