Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዑመሩል ፋሩቅ ሸይጧን የሚሸሸው ሶሐብይ!

ዑመሩል ፋሩቅ ሸይጧን የሚሸሸው ሶሐብይ!
ሶሐባው ሰዕድ ኢብን አቢል ወቃስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡፡ በአንድ ወቅት ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ከነቢዩ (ዐለይሂሰላም) ቤት ሊገባ ፍቃድ ጠየቀ፡፡ ከነቢዩ (ዐለይሂሰላም) ዘንድ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚያወሩ ሴቶች ነበሩ፡፡ የዑመርን ድምፅ ሲሰሙ ሒጃባቸውን አስተካክለው ሊለብሱ ተሯሯጡ፡፡ ረሱል (ዐለይሂሰላም) እየሳቁ ለዑመር እንዲገባ ፈቀዱለት፡፡ ዑመርም “አላህ ጥርስህን ያስቀው የአላህ መልእክተኛ ሆይ!” አላቸው፡፡ ነብዩም (ዐለይሂሰላም) “እነዚህ እኔ ጋር የነበሩ ሴቶች ገረሙኝ፡፡ ድምፅህን ሲሰሙኮ ወደ ሒጃባቸው ተሯሯጡ” አሉት፡፡ ዑመርም “አንተ ነህ ልትከበርና ልትፈራ የሚገባህ ያረሱለላህ” ካለ በኋላ “እናንተ የነፍሶቻችሁ ጠላቶች እኔን ትፈራላችሁ የአላህ መልእክተኛን አትፈሩምና?!” ሲላቸው “አዎ ከረሱል (ዐለይሂሰላም) ይልቅ አንተ ደረቅና አስፈሪ ነህ” አሉት፡፡ ከዚያም ረሱል (ዐለይሂሰላም) እንዲህ አሉ “ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ ይሁንብኝ ሸይጧን በአንድ መንገድ ላይ በጭራሽ አያገኝህም መንገድ ቀይሮ በሌላ መንገድ ቢሄድ እንጂ”
ቆይማ እዚች ጋ አንድ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ ሺዐዎች የዑመር ስም ሲነሳ በጥላቻ እብደታቸው እንደሚነሳ ይታወቃል፡፡ ዛሬ ድረስ ይሄ ነገር በግልፅ የሚታይ ነው፡፡ እ.ኢ.አ በ2005 ኢራቅ ውስጥ 15 ሰዎች ስማቸው ዑመር ስለሆነ ብቻ በሺዐዎች ተገድለዋል፡፡ በቅርቡም ኢራን ውስጥ በርካታ ዑመሮች በሌላ ሳይሆን በስማቸው ብቻ ከስራ ተባረዋል፡፡ ዑመርን ምን ያህል ቢጠሉት ነው በስም ብቻ እንዲህ የሚደረገው?
ሌላ ነገር፡፡ መዲና ውስጥ የሚገኘው የነብዩ (ዐለይሂሰላም) መስጂድ ካሉት በሮች ውስጥ አንዱ “የዑመር በር” ነው፡፡ ታዲያ ሺዐዎች ምን አሉ “ለዑመር ካለን ጥላቻ የተነሳ ወደ መስጂዱ ስንገባ በዑመር በር በኩል አንገባም” አሉ፡፡ አንዱ ዐሊም ምን አላቸው “ረዲየላሁ ዐንከ ያ ዑመር! ሸይጧን በህይወትህ ሳለህ ብቻ አይለም ሞተህም ይሸሸሃል!!!” አላሁ አክበር!!!