Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የገደለው ባልሽ የሞተው ወንድምሽ ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ! የIS ታጣቂዎች ማርከው በእጃቸው ያስገቡትን ዮርዳኖሳዊ ፓይለት ከነህይወቱ በእሳት አቃጥለው ሲገድሉት የሚያሳይ ቪዲዮ ለቀዋል። ይህን ስትሰማ ምን ትላለህ?

'የገደለው ባልሽ 
የሞተው ወንድምሽ
ሀዘንሽ ቅጥ አጣ
ከቤትሽ አልወጣ!

የIS ታጣቂዎች ማርከው በእጃቸው ያስገቡትን ዮርዳኖሳዊ ፓይለት ከነህይወቱ በእሳት አቃጥለው ሲገድሉት የሚያሳይ ቪዲዮ ለቀዋል። ይህን ስትሰማ ምን ትላለህ?

ጠላቶች ወንድሞቻችንን ቢገሉብን ተራግመንም፣ ተቃጥለንም፣ ቂም አዝለንም እንኖራለን፤ ከምንም በላይ ደግሞ አላህ እንደሚክሰን ተስፋ እናደርጋለን። ሙስሊም ሙስሊሙን ሲገድል ግን የት እንገባለን? ምን እንላለን? 

አንድ ካፊር ሲሞት አለም እንዴት እንደሚጮህለት አስተውለናል፤ ግና ነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) "አላህ ዘንድ የአንድ ሙስሊም ደም ከሚፈስ ዱኒያ ብትወገድ ይቀላል" ያሉለት ሙስሊም ደሙ ዛሬ በየአቅጣጫው ሲፈስ ዋይ ባይ አጥቷል። ግን ለምን?

ነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) "ሁለት ሙስሊሞች በሰይፋቸው ቢጋጠሙ ገዳዩም ተገዳዩም የእሳት ናቸው" እያሉ ዛሬ የስልጣን ጥመኞች በሚቀሰቅሱት አመፅ ሙስሊም ሀገራት እየታመሱ ሙስሊሞችም እየተጫረሱ ታያለህ። ግልብ ወጣቶች በአፈቀላጤዎች ተሸውደው የስልጣን መሸጋገሪያ ርብራብ ሲሆኑ ደካማ ህፃነትና አረጋውያን ደግሞ በወላፈኑ እየተገርፉ መርገፋቸውን ቀጥለዋል። 

ይኸው በሶርያ ብቻ ባለፉት አመታት በነበረው የእርስበርስ ግጭት ምክንያት ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) የሚልቅ ክቡር ሙስሊም ደም ፈሷል! 

ከሀድያን ግን ዛሬም  እየተጫወቱብን ነው። እኛም ከነሱው በወሰድነው ዜማ፣ በነሱው መዝሙር ተቃኝተን፣ ከነሱው በገዛነው መሳሪያ እያቀነቀንን የወንድማችንን ህይወት እንቀጥፋለን። ከዚያም ይህንን ግፍ፣ ጨካኝነትና እውርነት "ጂሀድ" ብለን ራሳችንን እናታላለን። 

መቼ ይሆን የምንነቃው? መቼ ይሆን ወደ ዲናችን የምንመለሰው? መቼ ይሆን የሚፍለቀለቀውን ስሜታችን ገዝተን ለዑለሞቻችን ምክር ጆሮ የምንሰጠው?

ያረቢ አንተ ለባሮችህ ቀልብ ስጠን! 
የሙስሊሙን ደም አንተ ጠብቅልን! 
አላዋቂዎች በሚሰሩትም አትያዘን!'

የገደለው ባልሽ

አላዋቂዎች በሚሰሩትም አትያዘን!

Post a Comment

0 Comments