Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አበሳኸም ጥዝጥዝ አትበር የሼኾች ቀልብ ይረግድኸ በግርድፉ (ሲበዛ አትዳፈር የሼኾቹ ቀልብ በመጥፎ ያገኘሀል) ማለት ነው።



አበሳኸም ጥዝጥዝ አትበር የሼኾች ቀልብ ይረግድኸ
።።።።።።።።።።።
በግርድፉ (ሲበዛ አትዳፈር የሼኾቹ ቀልብ በመጥፎ ያገኘሀል) ማለት ነው።
ይህ በብዛት በቤተ—ጉራጌ አካባቢ ተውሂድ በምታስተምርበትና ከሽርክ በምታስጠነቅቅበት ጊዜ ከአባቶችና ከእናቶች በኩል የሚሰነዘርብህ የማስፈራሪያ ዐረፍተ ነገር ነው። ታዲያ ሁድን ሕዝቦቹ እንዲህ ብለውት አልነበር
إِنْ نَقُولُ إِلا اعْتَرَاكَ بَعْضُ آلِهَتِنَا بِسُوءٍ
‘ከፊሎቹ አማልክቶቻችን በክፉ ነገር (በዕብደት) ለክፈውሀል እንጂ ሌላን አንልም ‘ ብለው ባስፈራሩት ጊዜ ይህንን ነበር ያላቸው
" قَالَ إِنِّي أُشْهِدُ اللَّهَ وَاشْهَدُوا أَنِّي بَرِيءٌ مِمَّا تُشْرِكُونَ (54) مِنْ دُونِهِ فَكِيدُونِي جَمِيعًا ثُمَّ لا تُنْظِرُونِ (55)
‘እኔ አላህን አስመሰክራለሁ፤ (በአላህ ላይ) ከምታጋሩትም እኔ ንጹሕ መሆኔን መስክሩ ። ከአላህ ውጭ የምታመልኳቸው አማልክቶች እናንተም አንድ ላይ አብራችሁ በኔ ላይ የቃጣችሁት(የፀነሰሳችሁት) ነገር ካለ ፋታ አትስጡኝ የምትችሉ ከሆነ አሁኑኑ አድርጉት ታደርሱብኛላቹ ብዬ አልሰጋም ምክንያቱም
إِنِّي تَوَكَّلْتُ عَلَى اللَّهِ رَبِّي وَرَبِّكُمْ
የነገሮች ሁሉ አስተናባሪ ፤በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ፤ ከፍላጎቱ ውጭ አንዳችም ነገር መሆን በማይችል ለኔም ለናነተም ጌታ በሆነው አላህ ተመክቻለው።" በማለት ነበር ያጣጣለባቸው ነብዩላህ ሁድ። የነገሮች ሁሉ አስተናባሪ በርሱ ላይ መንፈሳዊ ጉዳት ማድረስ የሚችለው ብቸኛው አላህ እንደሆነ በማወቁ ፤ ስለዚህ አትፍራ አብሬትዬም ሆኑ ሌላው በአንተ ላይ ሊያደርሱ የሚችሉት ጉዳት የለም ይልቁንም የአላህ እርዳታ ካንተ ጋር ነውና ቀጥ በል።

Post a Comment

0 Comments