Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የመጀመሪያው አረብ አሳሽ (The First Arab Explorer) በመባል ይታወቃል ኢብን ባቱታ


የመጀመሪያው አረብ አሳሽ (The First Arab Explorer) በመባል ይታወቃል ኢብን ባቱታ።እውነት እያደረ ይጠራል የሚለውን ብሂል አያውቀው ኖሯልና በታላቁ የኢስለም ሊቅ ኢብን ተይሚያህ ላይ እንዲህ በማለት ነበር የቀጠፈው " ወደ ደማስቆ በደረስኩ ጊዜ ኢብን ተይሚያህ በጃሚዕ ሚመበር ላይ ሆኖ ሰዎችን ሲገስፅ አገኘሁት ከአጠቃላይ ንግግሩ እንዲህ የሚል ነበር ’አላህ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ ልክ እኔ ከሚምበር እንደምወርደው ይወርዳል ካለ በኋላ ደረጃ በደረጃ ከሚንበር ላይ ወረደ’ " ይህንን ቅጥፈት አስመልክተው ሸይኽ አል ዐላማህ ሙሀመድ በይጧር እንደሚከተለው ምላሽ ሰጥተዋል
1ኛ) ኢብን ባቱታ በጭራሽ ምንም ዓይነት ንግግር ከኢብን ተይሚያህ አልሰማም ፤ አልተገናኙምም። ምክንያቱም ኢብን ባቱታ ደማስቆ የደረሰው በዕለተ_ሀሙስ ቀን 19 ወረሀ ረመዷን 726 ዓ·ሂ ሲሆን ሸይኸል ኢስላም የዚያን ዓመት ከሻዕባን ወር መጀመርያ ጀምሮ እስከ ዕለተ_ህልፈቱ (ሰኞ ዙልቂዳ 20/728 ዓ·ሂ) ድረስ አላህን የተገናኘበት እስር ቤት ውስጥ ነበር ።ታዲያ ሸይኸል ኢስላም እሰር ቤት ሆኖ ሳለ እንዴት ጃሚዕ ውስጥ ሰዎችን ሲገስፅ ሊያገኘው ቻለ?
2ኛ) በጃሚዕ ሚንበር ላይ ሆኖ በፍፁም ሰዎችን ገስፆ አያውቅም በወንበር ላይ ተቀምጦ ቢሆን እንጂ። ኢማም አዝዘሀብይም ወንበር ላይ ሆኖ ሰዎችን የቁርዐን ተፍሲር በቃሉ ያስተምር እንደነበር ነው ያተቱት።
3ኛ) የኢብን ባቱታ ቅጥፈት ሸይኸል ኢስላም በኪታቦቹ የአላህ ስሞችንና ባህርያቶችን አስመልክቶ "ፍፁም ከፍጡር ጋር ማመሳስል ሳይኖር ማፅደቅ እና ያለምንም ትርጉም ማራቆት ከፍጡራን ባህርይ ፍፁም ማጥራት" ከሚለው አስተምህሮው ፍፁም ተቃራኒ ነው።
4ኛ) ኑዙልን (አላህ የቅርቢቷን ሰማይ እንደሚገባው እንደሚወርድ ) አስመልክቶ ራሱ የቻለ ኪታብ አለውና ኪታቡ በራሱ በኢብን ባቱታ ላይ ምላሽ ነው "
[ምንጭ: ሚን አዕላሚ አልሙጀዲዲን ከሚለው የሸይኽ ፈውዛን (አላህ ይጠብቃቸው) ኪታብ ለቃላት አሰካክ በሚመች መልኩ የተቀነጨበ]

Post a Comment

0 Comments