Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ልብ ያለው ልብ ይበል ።።።።።።።።።።።።።። ሰሕል ኢብን አብደላህ አትስቱርይ እንዲህ ይላሉ "ሰዎች በመልካም ከመሆን አይወገዱም ባለስልጣኖቻቸውና (መሪዎቻቸው) ዑለማዎቻቸውን እስካላቁ ድረስ።





ልብ ያለው ልብ ይበል
።።።።።።።።።።።።።።
ሰሕል ኢብን አብደላህ አትስቱርይ እንዲህ ይላሉ "ሰዎች በመልካም ከመሆን አይወገዱም ባለስልጣኖቻቸውና (መሪዎቻቸው) ዑለማዎቻቸውን እስካላቁ ድረስ። ሁለቱን ያላቁ ጊዜ አላህ ዱንያቸውንም አኺራቸውንም ያሳምርላቸዋል። ሁለቱን ማሳነስ (ማቅለል) ሲጀመሩ ዱንያቸውንም አኼራቸውንም አበላሽተዋል።"
ሸይኽ ዑሰይሚን መሪና ተመሪን ሀቅ በተመለከተ እንዲህ ይላሉ " ከባለስልጣን በሚኖር ግኑኝነት በደጋግ ሰለፎች አካሄድ ላይ አደራ አደራ። የነሱን (የመሪዎች) ስህተት ሰዎችን ለማሳመፅ ፤ የሰዎችን ልቦና ከመሪዎች ለማራቅ መንገድ ተደርጎ መያዝ የለበትም (ምክንያቱም) ይህ የሁከት (turmoil) ምንጭ ፤ እንዲሁም በሰዎች መሀከል ብጥብጥ እንዲከት ዋናው መሠረት ነው። በተመሳሳይ የሰዎችን ልብ የዑለሞች ደረጃ እያሳነሱ መሙላት (ከራሴ : የወር አበባ እና የኒፋስ ደም ፈትዋ እንጂ ስለ ተጨባጩ ዐለም እውነታ አያውቁም እንደሚሉ ፊክረኞች) ። ከዚያም የተሸከሙትን የአላህ ሸሪዓን ማሳነስ ይከተላል (ከራሴ: ከኋላ የመጡ የንጉሱ ወንበር ጠባቂ ዑለሞች እንደሚሉ ፊክረኞች)" ካሉ በኃላ በመቀጠልም እንዲህም አሉ "ሰለፎቹ ባለስልጣን ክብርን በተመለከተ ያሳለፉትን በጥሞና ማየት ግድ ይላል (ከራሴ: ለምሳሌ ከሀጃጅ ጋር)። ሰዉ ስሜቱን ማገት እና ከኃላ ሊከሰት የሚችል ችግር ማገናዘብ መቻል አለበት። አማፂ የሆነ (በአጠቃላይ የሚያምፅም የሚያሳምፅም) የኢስላም ጠላቶችን እየካደመ እንደሆነ መታወቅ አለበት። ሀሳብ በአመፅ ወይም በውጭ አካላት በመረዳት አይደለም የሚገለፀው (በሂክማ) በጥበብ እንጂ ። ሂክማ ስል ግን ስህተትን እያዩ ዝም ማለት ነው እያልኩ አይደለም ባይሆን የተወከለው አካልን (መሪን) ስህተት ማረም እንጂ እሱን በሌላ ለመተካት መንቀሳቀስ አይደለም ። መካሪ ብሎ ማለት ተወካዩን የሚያስተካክል እንጂ የሚቀይር አይደለም"
(ከሸይኽ አብዱሰላም ቡርጁስ አላህ ይዘንላቸው ሙዐመለቱ አል ሁካም ፊ ደውኢ ኪታብ ወ ሱናህ ኪታብ የተወሰደ )

Post a Comment

0 Comments