Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሸሪዓዊ ጉዳዮችን አቅልሎ ማየት እና ሸሪዓውን መፃረር ያለው መዘዝ!!! ክፍል ሁለት


ክፍል ሁለት
።።።።።።።
ክፍል አንድ ላይ እንዳሳለፍነው አላህ ሱብሀነሆ ወተዐላ ተራ በሚመስል ቅርንጫፋዊ ጉዳይ በመልክተኛው ፍርድ ተሰጥቶት ያንን አንሳርይ ለውሳኔው እጅ ባለመስጠቱ ነበር ይህን አስፈሪ አንቀፅ (… ፍፁም መታዘዝን እስከሚታዘዙህ አያምኑም።" (አንኒሳእ 65)) አላህ ከሰማይ ያወረደው ። ታዲያ አላህ እና መልክተኛው ኢስላማዊ መሪዎችን መታዘዝ አፅንኦት ሰጥተውበታል። መልክተኛውም መሪዎችን መታዘዝ እርሳቸውን እንደመታዘዝ እንደሆነ ተናግረዋል እንዲህ በማለት
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنَّهُ قَالَ: ((مَنْ أَطَاعَنِي فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ وَمَنْ عَصَانِي فَقَدْ عَصَى اللَّهَ وَمَنْ أَطَاعَ أَمِيرِي فَقَدْ أَطَاعَنِي وَمَنْ عَصَى أَمِيرِي فَقَدْ عَصَانِي)).
ለዚህም ነው ከቀደምት ዑለሞች ጀምሮ አሁን እስካለንበት ዘመን ያሉ ዑለሞች ለጉዳዩ አፅንኦት የሚሰጡት። መሪን መታዘዝ የዲን መሠረታዊ መርህ ወይም ኡሱል እንደሆነም ይናገራሉ። በዚህ ላይ ጥሩ ምሳሌ ሊሆን የሚችለው
የአላህ ክልከላን በመዳፈር፣ በበደልና ብዙ ደም በማፍሰስ ሙስሊም ማ/ሰብ ዘንድ እውቅና ያተረፈው ሀጃጅ ኢብን ዩሱፍ ነው። ታዲያ ከስኬታማ ትውልዶች ለአብነት ሰዒድ ኢብኑ ጁበይርን ፤ ሀረም ውስጥ ደግሞ ምንም እንኳ ቃልኪዳኑን ባያፈርስም ኢብኑ ዙበይርን ገድሏል። ይህማ ከመሆኑ ጋር በርሱ ላይ ሰይፍ የመዘዘ አንድም ሰሀባ ወይም ታብዕይ የለም። ይልቁንም ከሰሀባ እነ አብደላህ ኢብኑ ዑመር ከታብዕይ እነ ኢብኑ ሙሰየብ፣ኢብኑ ሲሪን ሁሉም ሰምተው ታዘዋል አመፅ አስበውትም አያውቁም። እነዚያ ምርጥ ትውልዶች ሀጃጅ ይህ ሁላ እኩይ ተግባር ሲፈፅምባቸው አንገት ያስደፋቸው ጉዳይ ከቶ ምን ይሁን? ሽንፈትን ፈርተው እንዳንል ከመልክተኛው ጋር ብዙ ጦርነቶችን አድርገው ድል ተቀናጅተዋል።ከነብዩ ኸሊፋዎችም ጋር ተሰልፈው ብዙ አገራትን ከፍተዋል። ታዲያ ለአንድ ሀጃጅ የሚሆን አቅም ተክኒክና ስልት እንዴት ጠፋ ? ብለን በንፁህ አዕምሮ ራሳችንን ብንጠይቅ መልሱ ከወዲህ መሆኑን እንገነዘባለን። አዎ ሽንፈት ወይም ፍርሀት አሊያም መበደላቸው ሳያውቁት ቀርተው አይደለም ይልቁንስ አንገት ያስደፋቸው ከነብዩ አንደበት ቀጥታ (lively) የተማሩት ወህይ ብቻ እና ብቻ ነው።
ለምሳሌ…
……2b continued (ይቀጥላል)

Post a Comment

0 Comments