Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሸሪዓዊ ጉዳዮችን አቅልሎ ማየት እና ሸሪዓውን መፃረር ያለው መዘዝ!!! ክፍል አንድ


ሸሪዓዊ ጉዳዮችን አቅልሎ ማየት እና ሸሪዓውን መፃረር ያለው መዘዝ!!!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ክፍል አንድ
።።።።።።።
ይህ የሚያነቋቁረን ጉደይ መሠረታዊ ሳይሆን ቅርንጫፋዊ እና ተራ ጉዳይ ነው አትበል። የመልክተኛው አክስት ልጅ ዙበይር እና አንድ አንሳርይ ያጨቃጨቃቸው ርዕስ ቅርንጫፋዊ ጉዳይ ነበር። ለዚያውም የአትክልት ስፍራን ወራጅ ውሃ ቀድሞ ለማጠጣት ተገቢው ማን ነው? የሚል። ታዲያ መልክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በመሀከላቸው ፍርድ ሰጡ የላይኛው ተፋሰስ ባለቤት የነበረው ዙበይር ነበርና ቀድሞ እንዲያጠጣ ከዚያም (ዙበይር ሲጨርስ) ለታችኛው ተፋሰስ ባለቤት (አንሳርዩ) እንዲያጠጣ ውሳኔ አስተላለፉ። ሆኖም አንሳርዩ በመልክተኛው ውሳኔ ባለመደሰት "የአክስትህ ልጅ ስለሆነ ነው " የሚል ቃል ተነፈሰ ።በዚህ ንግግሩ አላህ ይህን አንቀፅ ነበር ያወረደው
( ﻓَﻼ ﻭَﺭَﺑِّﻚَ ﻻ ﻳُﺆْﻣِﻨُﻮﻥَ ﺣَﺘَّﻰ ﻳُﺤَﻜِّﻤُﻮﻙَ ﻓِﻴﻤَﺎ ﺷَﺠَﺮَ ﺑَﻴْﻨَﻬُﻢ ﺛُﻢَّ ﻻ ﻳَﺠِﺪُﻭﺍ ﻓِﻲ ﺃَﻧْﻔُﺴِﻬِﻢْ ﺣَﺮَﺟًﺎ ﻣِﻤَّﺎ ﻗَﻀَﻴْﺖَ ﻭَﻳُﺴَﻠِّﻤُﻮﺍ ﺗَﺴْﻠِﻴﻤًﺎ )
"በጌታህ ይሁንብኝ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስኪያስፈርዱህ ከዚያም በፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኛቸው ፍፁም መታዘዝን እስከሚታዘዙህ አያምኑም።" (አንኒሳእ 65)
ስማኝ እሰቲ ጎበዝ
" አንድነታችንን እናጠናክር
በተስማማንበት አንድ እንሁን በተለያየንበት ጉዳይ ላይ ኡዝር እንሰጣጥ። " ባትልስ?
ለምን እንደሆነ ታውቃለህ?
ያነቋቆረህ ጉዳይ መፍትሔ እንዳለው በማይሻረው የጌታህ ቃል እንዲህ ተብሎ ተነግሮሀል።
﴿ ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍْ ﺃَﻃِﻴﻌُﻮﺍْ ﺍﻟﻠّﻪَ ﻭَﺃَﻃِﻴﻌُﻮﺍْ ﺍﻟﺮَّﺳُﻮﻝَ ﻭَﺃُﻭْﻟِﻲ ﺍﻷَﻣْﺮِ ﻣِﻨﻜُﻢْ ﻓَﺈِﻥ ﺗَﻨَﺎﺯَﻋْﺘُﻢْ ﻓِﻲ ﺷَﻲْﺀٍ ﻓَﺮُﺩُّﻭﻩُ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﻠّﻪِ ﻭَﺍﻟﺮَّﺳُﻮﻝِ ﺇِﻥ ﻛُﻨﺘُﻢْ ﺗُﺆْﻣِﻨُﻮﻥَ ﺑِﺎﻟﻠّﻪِ ﻭَﺍﻟْﻴَﻮْﻡِ ﺍﻵﺧِﺮِ ﺫَﻟِﻚَ ﺧَﻴْﺮٌ ﻭَﺃَﺣْﺴَﻦُ ﺗَﺄْﻭِﻳﻼً )
"እናንተ ያመናችህ ሆይ አላህን ተገዙ። መልክተኛውንና ከናንተ የስልጣን ባልቤቶችን ታዘዙ። በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትሆኖ (የተከራከራችሁበት ነገር) ወደ አላህና (ቁርዐን) ወደ መልክተኛው (ሱናቸው) መልሱ።ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው።" (አንኒሳእ 59)
ኢንሻላህ ይቀጥላል…

Post a Comment

0 Comments