Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አፕሪልስ ፉል ።።።።።።።።። April Fool's Day


አፕሪልስ ፉል
።።።።።።።።።
April Fool's Day ብለህ ትዋሽ ይሆናል አላህ ግን እውነተኛና ከእውነቶኞች ጋር ብቻ እንድንሆን እንዲህ በማለት አዟል
{يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللهَ وَكُونُوا مَعَ الصَّادِقِينَ} [التوبة: 119]
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ፍሩ ፤ ከእውነቶኝችም ጋር ሁኑ።
መልክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የውሸት ክፋቱንና እንዲሁም መዳረሻው ጀሀነም እንደሆነ እንዲህ በማለት ነግረውናል
عن ابن مسعود رضي الله عنه عن النَّبيّ صلى الله عليه وسلم، قَالَ: ((إنَّ الصِّدقَ يَهْدِي إِلَى البرِّ، وإنَّ البِرَّ يَهدِي إِلَى الجَنَّةِ، وإنَّ الرَّجُلَ لَيَصدُقُ حَتَّى يُكْتَبَ عِنْدَ اللهِ صِدِّيقًا. وَإِنَّ الكَذِبَ يَهْدِي إِلَى الفُجُورِ، وَإِنَّ الفُجُورَ يَهدِي إِلَى النَّارِ، وَإِنَّ الرَّجُلَ لَيَكْذِبُ حَتَّى يُكتَبَ عِنْدَ الله كَذَّابًا)). مُتَّفَقٌ عَلَيهِ.
ከኢብን መስዑድ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ) እንዲህ ብለዋል " እውነት ወደ መልካም ነገር ይመራል ፤ መልካም ነገር ወደ ጀነት ይመራል ፤ አንድ ሰው እውነትን ይናገራል አላህ ዘንድ እውነተኛ ተብሎ እስኪመዘገብ ድረስ። ውሸት ወደ መጥፎ ነገር ይመራል ፤ መጥፎ ነገር ወደ ጀሀነም ይመራል ፤ አንድ ሰው ውሸትን ይናገራል አላህ ዘንድ ውሸተኛ ተብሎ እስኪመዘገብ ድረስ።"
በተለይ ሰዎችን ለማሳቅ ተብሎ የሚዋሽ ውሸት ሀራምና በተጨማሪም መዘዙ የከፋ መሆኑን በተረጋገጠ ዘገባ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ በማለት ተናግረዋል
« ﻭَﻳْﻞٌ ﻟِﻠَّﺬِﻱ ﻳُﺤَﺪِّﺙُ ﺑِﺎﻟﺤَﺪِﻳﺚِ ﻟِﻴُﻀْﺤِﻚَ ﺑِﻪِ ﺍﻟﻘَﻮْﻡَ ﻓَﻴَﻜْﺬِﺏ، ﻭَﻳْﻞٌُ ﻟَﻪُ، ﻭَﻳْﻞٌ ﻟَﻪُ » ﻭﺣﺴَّﻨﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ ﻓﻲ « ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺘﺮﻣﺬﻱ » (1885)
" ወሬን እያወራ ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ የሚዋሽ ሰው ወይል የሚባል ጀሀነም አለለት ወይም ወየውለት ወየውለት"
ሌላው የራስን ኢስላማዊ ባህል ችላ በማለት በአላህ መንገድ ላይ የካዱ ሰዎችን ፈለግ መከተል አደጋው የከፋ ነው መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በከሀዲያን የሚመሳሰል ከነርሱ ጋር እንደሆነም እንዲህ በማለት ተናግረዋል
( ﻣَﻦْ ﺗَﺸَﺒَّﻪَ ﺑِﻘَﻮْﻡٍ ﻓَﻬُﻮَ ﻣِﻨْﻬُﻢ )َ
"በሰዎች ላይ የተመሳሰለ እርሱ ከነርሱ ጋር ነው"