Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አሕባሽና ኢኽዋንን አንድ ከሚያደርጓቸው ዐበይት ነገራቶች (mutual identity) ውስጥ



አሕባሽና ኢኽዋንን አንድ ከሚያደርጓቸው ዐበይት ነገራቶች (mutual identity) ውስጥ የሁለቱም የጥመት ቡድን ተጣሪዎች ሕዝቡን ወደነርሱ እንዲመጣና ለነርሱም ዳዕዋ ጆሮውን እንዲሰጥ ዳዕዋቸውን የሚያተኩሩት በታሪክ ትረካ ላይ መሆኑ ነው!
እስኪ ተመልከቱ!
የኢኽዋን ዳዕዋ በእከሌ ዳዒ ይባልና
« የነቢዩላህ –— ታሪክ» ፣ «የሶሓባው — — ታሪክ» ፣ «የሙጃሒድ እከሌ ታሪክ» የመሳሰሉት
የአሕባሹም
«የሰይድና— — ታሪክ» ፣ «የነቢዩላህ— — ታሪክ» ፣ «የወሊይ እከሌ ታሪክ»
በመሰረቱ ታሪክን ማወቅ ማንንም ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም! ሆኖም ሕዝብን በትረካ ለመያዝና ለማባበል መሞከር የቢድዓ ሰዎች አንዱ መገለጫ ነው!
አቡ ቂላባህ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል: –
« ዕውቀትን የገደሉት ተራኪዎች (ቁሳሶች) ናቸው ። አንድ ሰው ለአመት ያክል እሱ ጋር የሚቀር አንድም ነገር ሳይማር (ሙሉ አመቱን) ትረካ በመስማት ያሳልፋል ። ከዓሊም ጋር አንዲትን ሰዓት የተቀመጠ ግን ከተቀመጠበት ከመነሳቱ በፊት እራሱ ጋር የሚቀር ጠቃሚ ዕውቀትን ይይዛል»
[ሒላየቱል አውሊያዕ 2:287]
ለዚህም ነው የቢድዓ ሰዎች የዓቂዳን ርዕስ ወደጎን ገሸሽ አድርገው ሕዝቡን በትረካ አፍ የሚያስከፍቱት ። ያኔ ሕዝቤ አፉን ከፍቶ ‘O’ ባለበት ሰዓት በማር የተለወሰች ቢድዓዋን ጉርስ ያደርጉታል!
እስኪ ከላይ ባለው የሰለፍ ንግግር እራሳችንን እንፈትሽ!
ስንቶቻችን ነን እስከዛሬ በሲዲና በመሳሰሉት የታሪክ መዓት አድምጠን ጠቃሚ የተውሒድና የሱና ዕውቀት ላይ ግን ከመሰረቱም የማናውቅ?
ዛሬ ደሞ ልክ እንደ ኢኽዋኖች አሕባሾችም የኢንተርኔት ራዲዮ ከፍተው «የእከሌ ታሪክ በመሳጭ ትረካ» ብለው ወደሽርካቸውና ወደቢድዓቸው መጣራት ተያይዘውታል!
አደራቹን አደራቹን አደራቹን ጠጋ እንኳን እንዳትሏቸው!
የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁዐለይሂወሰለም እንዲህ ብለዋል: –
« የኢስራኢል ልጆች የጠፉት ትረካ መተረክ ሲጀምሩ ነው»
[አል ሲልሲላ አሶሒሓ 4/246]

Post a Comment

0 Comments