Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ፦ በጀነት ውስጥ ለወንዶች ሁረልአይን እንዷላቸው ተወስቷል። ለሴቶችስ? (ሸኸ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን ረሒመሁላህ )

A user's photo.
ጥያቄ፦ በጀነት ውስጥ ለወንዶች ሁረልአይን እንዷላቸው ተወስቷል። ለሴቶችስ?
መልስ፦ አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) የጀነትን ሰዎች ድሎትና ፀጋን አስመልክቶ እንዲህ ይላል፦
ۖ وَلَكُمْ فِيهَا مَا تَشْتَهِىٓ أَنفُسُكُمْ وَلَكُمْ فِيهَا مَا تَدَّعُون(٣١) َ
نُزُلًۭا مِّنْ غَفُورٍۢ رَّحِيمٍ﴿٣٢ۢ

<<...ለናንተም በርሷ ውስጥ ነፍሶቻችሁ የሚሹት ሁሉ አላችሁ፤ ለናንተም በርሷ ውሰጥ የምትፈልጉት ሁሉ አላችሁ፤ መሐሪ አዛኝ በሆነው (አላህ) የተበረከተ! መስተንግዶ (ይባላሉ)። (ፉሲለት 41፥ 31-32)
وَفِيهَا مَا تَشْتَهِيهِ ٱلْأَنفُسُ وَتَلَذُّ ٱلْأَعْيُنُ ۖ وَأَنتُمْ فِيهَا خَٰلِدُونَ
<<... በእርሷም ውስጥ ነፍሶች የሚከጅሉት፣ ዓይኖችም የሚደሰቱበት ሁሉ አልለ፡፡ እናንተም በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናችሁ፡፡>>( አል- ዙኽሩፍ 43፥71)
ነፍሶች ከሚሹት ነገሮች ሁሉ ትዳር በጣም ትልቅ መሆኑ የሚታወቅ ነው። እናም ጀነት ውሰጥ ለጀነት ሰዎች ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች ትዳር አለ። ሴቷን አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) በአዱኒያ ላይ ባሏ የነበረውን ሰው ይድራታል።
አላህ እንዲህ ይላል፦
رَبَّنَا وَأَدْخِلْهُمْ جَنَّٰتِ عَدْنٍ ٱلَّتِى وَعَدتَّهُمْ وَمَن صَلَحَ مِنْ ءَابَآئِهِمْ وَأَزْوَٰجِهِمْ وَذُرِّيَّٰتِهِمْ ۚ إِنَّكَ أَنتَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيم
ُ
<<ጌታችን ሆይ! እነርሱንም፣ ከአባቶቻቸውና ከሚስቶቻቸውም፣ ከዝርዮቻቸውም፣ የበጀውን ሁሉ እነዚያን ቃል የገባህላቸውን የመኖሪያ ገነቶች አግባቸው፡፡ አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ነህና፡፡>> (ጋፊር 40፥8)
በዱኒያ ላይ ያላገባች ከሆነች ጀነት ውሰጥ የምትደሰትበትን ባል አላህ ይድራታል።
(ሸኸ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን ረሒመሁላህ )