Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጊዜን መሳደብ!

Haider khedir
📕 ጊዜን መሳደብ!
وعن أبي هريرة رضى الله عنه:
عن النبي صلى الله عليه وسلم قال،
قال الله تعالى:-

🚫«يؤذيني ابن آدم، يسب الدهر وأنا الدهر، أقلب الليل والنهار.»
📕[رواه البخاري ومسلم]

አቡ ሁረይራ እንደተናገሩት የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:–
የበላይ የሆነው አላህ እንዲህ ብሏል ፦

🚫«የአደም ልጅ ያስቸግረኛል (ያውከኛል) ፣ ጊዜን ይሰድባል! ጊዜ ራሱ እኔ ነኝ! ፣ ለሊትና ቀንን እገለባብጣለሁ (እለዋውጣለሁ)»
📕[አልቡኻሪይ እና ሙስሊም ዘግበውታል]
وفي رواية:-
🚫«لا تسبو الدهر فإن الله هو الدهر »
📕[رواه مسلم]

በሌላ ዘገባም፦
🚫«ጊዜን አትሳደቡ አላህ ራሱ ጊዜ ነውና»
📕[ሙስሊም ዘግበውታል]
📃ማስታወሻ ፦
"ጊዜ ራሱ አላህ ነው" ማለት በጊዜ ውስጥ የሚከናወኑ ክስተቶች ደስታም ይሁን ሀዘን ፣ ጭንቀትም ይሁን እርካታ ሁሉ በአላህ ውሳኔና እቅድ መሆኖኑ ለመግለፅ ነው።
"ባለቤቱን ካልደፈሩ አጥሩን አይነቀንቁ"
እንደሚባለው ብሂል ጊዜ በራሱ ምንም ማድረግ የማይችል ፍጡር በመሆኑ ጊዜን በምንሳደብበት ወቅት ምንሳደበው ጊዜውን ሳይሆን በጊዜ ላይ የፈለገውን እንዲከሰት ያደረገውን አላህን ነው።

🔇 ከተለመዱ አባባሎች
"ምን አይነት የተረገመ ቀን ነው!"

"የጊዜ ጎዶሎ!"

"ጊዜ ነው የጣለኝ!"

ሌላም ሌላም ይገኛሉ…
በማወቅን ሆነ በመዘናጋት ጊዜን የምንሳደብ ወንድምና እህቶች ሳይመሽ በጊዜ ጌታችንን ምህረት ልንጠይቅ ይገባል።
📌ጌታች እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ የሆነ ጌታ ነውና!
📜አላህን አዛ ከማድረግ እንቆጠብ!

Post a Comment

0 Comments