Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስልክ → የዘመናችን ጣዖት? የ12 አመቷ ልጅ እናቷ ስልኳን ስለደበቀችባት በመርዝ ልትገድላት ሞከረች!

A user's photo.
ስልክ → የዘመናችን ጣዖት?
የ12 አመቷ ልጅ እናቷ ስልኳን ስለደበቀችባት በመርዝ ልትገድላት ሞከረች!

በአሜሪካ ኮሎራዶ ግዛት ከ12 አመቷ ልጇ ጋር የምትኖረው እናት የልጇ የስልክ ሱሰኝነት አሳስቧት አይ ፎኗን (Iphone) ብትደብቅባት በአፀፋው ከልጇ ያገኘችው የመግደል ሙከራን ነበር ።
መርማሪ ፓሊሶች እንዳረጋገጡት የ12 አመቷ ልጅ በስልኳ መቀማት አማካኝነት እናቷን ከአንድም ሁለቴ በመርዝ ልትገድላት ሞክራ ሁለቱም ከሽፎባታል ።
እናቷ እንደምትናገረው በመጀመሪያ ልጇ እንድትጠጣው ካቀረበችላት መጠጥ ውስጥ ለየት ያለ ሽታ በማሽተቷና በማስተዋሏ ምንአልባት ልጄ ብርጭቆውን በደንብ ሳታጥበው ከዛ የመጣ ጠረን ይሆናል ብላ ሳትጠጣው እንደቀረች ታስታውሳለች ።
ሆኖም ከቀናት በህዋላ በድጋሚ በሁለተኛ ሙከራዋ እናት ልጇ ልትመርዛት እየሞከረች እንደሆነ ካቀረበችላት መጠጥ በኬሚካል የነጣና የተደባለቀ መሆኑን ማስተዋሏ ጥንቃቄ አድታደርግ አስገድዷታል ።
ፓሊስ ልጅቷን ባነጋገረበት ሰዓት የገዛ እናቷን ለመግደል ያነሳሳት ም/ት ምን እንደሆነ ሲጠይቃት ሲጠይቃት የልጅቱ መልስ የነበረው እናቷ ስልኳን ከሷ አርቃባት በመደበቋ ም/ት ብቻ መሆኑን ተናግራለች።
ፍርድቤት ልጅ እናቷን ለመግደል ባደረገችው ሙከራ የወጣት ጥፋተኞች ማዕከል ገብታ እንትቀጣ ውሳኔ አስተላልፎባታል።
[ምንጭ:– ፎክስ ኤይት የዜና ድረገፅ]
———
ኢናሊላሂ ወኢናኢለይሂ ራጂዑን