Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መርሀ ግብር ወዳጄ ሆይ! ይህ መርሀ ግብር የተቃውሞና የረብሻ አይደለሞ ...

መርሀ ግብር
ወዳጄ ሆይ! ይህ መርሀ ግብር
☞ የተቃውሞና የረብሻ አይደለሞ
☞ ለአንድ ጂመአ አልያም ለአንድ ወር ብቻ ቆይቶ የሚያበቃ ወይሞ የሚለወጥ ሣይሆን አንተ ይህችን አለም ለቀህ እስክትወጣ ድረስ አንተን ብቻ የሚመለከትህ ጉዳይ ሢያበቃ መርሀ ግብሩ ግን ይዘቱ ሣይቀንስ እና ምንም ሣይለወጥ ይህች አለም እስክትጠፋ ይቀጥላል
☞ ወዳጄ ሆይ! ይህ መርሀ ግብር የወጣው ዛሬ አልያም ትላንት አይደለም ይህ መርሀ ግብር የወጣው የሠው ልጆች አባት የሆኑት አደም አለይሒ ሠላት ወሠላም ከጠፈጠሩበት አንስቶ ነው
☞ ወዳጄ ሆይ! ይህን መርሆ ያወጣው ወደዚህች አለም መቼ እንደመጣና መቼ እንደሚሔድ ጠንቅቆ የማያውቀው ፍጡር ሣይሆን ፍጡራን በአጠቃላይ ከመኖራቸው በፊት ብቻውን የነበረው እንዲሁም ፍጡራን በአጠቃላይ ሢጠፋ ብቻውን ከሚቀረው አላሁ ሡብሀነሁ ወተአላ ነው
☞ ወዳጄ ሆይ! ይህ መርሀ እንዲሁ ምላስ ብቻ በሆኑ ፍጡራኖች አል ነበረም ወደ አላዋቂው ማህበረሠብ ሢደርስ የነበረው ለዚህ መርሆ የሚሞቱ ፣የሚታሠሩ ፣ በመጋዝ የሚዘገዘጉ ፣ ከቄያቸው ና ከሀገር በሚባረሩ … ጀግና ነብያቶች ነበር ይህ መርሆ ከአላህ መጥቶ ለሌላው ማህበረሠብ የሚደርስ የበረ
☞ ወዳጄ ሆይ! መርሀ ግብሩ የቃል ይዘቱ እጅጉኑ አጭር ሢሆን የሀሣቡ ይዘት ግን ስለሡ የሚያብራሩ ሠዎች አብራርተው ሣይጠግቡት የሚያልፋት እጅጉኑ ሠፊ ርዕስ ነው
መርሀ ግብሩ
✔ አላህን በብቸኝነት ማምለክ ከአላህ ውጪ የሚመለኩ አማልክቶችን በአጠቃላይ እርግፍ አድርጎ መተው
☞ አንድ የረሣሁት ነገር! ይህ መርሀ ግብር የሚያወርስህ የቤተ መንግስት ዙፋን ሣይሆን አይኖች አይተውት የማያውቁት ጆሮ ሠምቶት የማያውቀው በሠው ልጅ አእምሮ ውል ብሎ ወደማያውቀው የሠላም ሀገር ጀነትን ነው
★ወዳጄ ሆይ! ከዚህ ቡሀላ ደግሞ የምነግርህ ሊያስፈራህ ሣይሆን ሊያጠነክርህ ይገባል
☞ ይህን መርሆ ከሠማህበት እና ከተረዳህበት ሠአት አንስቶ ይህንን ህግ የማራገብ የማስተማር የማሣወቅ ግዴታ አለብህ!!! ይህን የማታደርግ ከሆነ ግን አላህ ከራህመቱ ያባርሀል እንዲሁም በታራጋሚዎች ምላስ ትረገማለህ!!
አስተውል!! ይህ ዛቻ ምንም ከማይፈጥረው ከደካማው የሠው ልጅ አይደለም የተሠነዘረው ከሀያሉ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ነው!!!
☞ ይህንን መርሆ ስታስተላልፍ ብዙ እንቅፋቶች ሊያገኙህ እንደሚችል እመንበት ምክንያቱም ጥሩ እና መልካም ነገር በመጥፎ እና በአስቸጋሪ ነገር የተከበቡ ናቸውና!!
☞ አደራህን ይሄንም ለማስተላለፍ ብለህ ቢሆን እንኳን ሁለተኛውን መርሆ እንዳትንደው ደሞ ሁለተኛው መርሆ ምንድን ነው!?
✔ መልዕክተኛውን ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም መከተል
ወደ ተውሒድ በምታደርገው ጥሪ መንገድህን መልዕክተኛው መንገድ ባደረጉት መንገድ አድርግ
 ጥንቃቄ!! "አተርፍ ባይ አጉዳይ" እንዳትሆን! የኢኽላሡን ጉዳይ አደራ!!!!!
አላህ በተውሒድ እና በሡና ላይ ኖረን በዛው ላይ የምንሞት ያድርገን

Post a Comment

0 Comments