Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሃቅን እወቃት የሃቅ ባለቤቶችን ታውቃለህ። ባጢልን እወቃት የባጢል ባለቤቶችን ታውቃለህ።

ሃቅን እወቃት የሃቅ ባለቤቶችን ታውቃለህ።
ባጢልን እወቃት የባጢል ባለቤቶችን ታውቃለህ።
=================
ከዚህ ውጭ መጀመሪያ ቀድመህ ሰዎችን ካወቅክ፣ ሰው ተከተይ ትሆናለህ። ያ ሰው ሲያወራ ታወራለህ፣ ሲቆጣ ትቆጣለህ፣ እሱ የወደደውን ትወዳለህ ሸሪአን ቢጋጭም፣ እሱ የጠላውን ትጠላለህ፣ ሸሪአን ቢገጥምም።
አገራችንም ላይ ይሁን ሌሎች ቦታዎች ላይ በግልፅ የሚታወቅ አባባል አለ። እሱም ሸሪአን የሚጋጭ ስራ ያ ሰዎች የሚከተሉት ሰው ሲሰራ እና በሸሪአ ሚዛን መልስ ሲሰጠው ስህተት ለመሆኑ፣ ሃቅን ሳይሆን ያን ሰው ሲከተሉ የኖሩት ጭፍራዎቹ "አንተ ከእገሌ የበለጠ ታውቃለህን?" ብለው። ሀቅን (የአላህን ቃል የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሱና) ለዛ ለሚከተሉት ሰው ሲሉ ይተውታል።
ይህም ታላቅ ጥመት ነው፣ ሀቅና ባጢልን በሰዎች መመዘን፣ ቁርአንን፣ ሀዲስን፣ የሰለፉነ ሳሊሁንን አስተምሮት ትቶ።
አላህ የሃቅ ተከታዮች ያድርገን። አላህ ሆይ! ሀቅን በሀቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፣ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን። አላሁመ አሚን።