Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሐላሉን ድፈረው‬ ግጥም


By Kiyya Muslimua Kiyya Muslimua
አሰላሙ አለይኩም
‪#‎ሐላሉን_ድፈረው‬
~~
~~እድሜህ ከደረሰ ከበረታ ጅስምህ
ከተመቻቸልህ ከፈቀደው አቅምህ
ለምን አታገባም አንተ ሙስሊም ወጣት
የፌስቡኳን ቆንጆ ባይንህ ከምትገምጣት
××××
በለስላሳ ድምፅዋ ኢማንህ ከሚተን
ምናል ብታገባ ሰርክ ከምትኳትን?
በሰዎች ሰርግ ላይ በተገኘህ ቁጥር
ምነው እኔስ በሚል ቅናት ከምትቋጥር
ምክኒያት እያበዛህ ለመሸሽ አትጣር
ብጤህን ፈልገው አንተም ኒካህ እሰር።
√√√√√√
ከአንዲት ሴት ጋራ መመስረት ጋብቻ
ምነው አስመሰልከው ጦርነት ዘመቻ
አብሽር ወንድምዬ በኣላህ ተመካ
ሐላል ሐላሉ ነው ያለበት በረካ
{{ ጣጣውን አታብዛው
ቀለል አርገህ ያዘው}}
~~እስከመቼ ድረስ በምኞት መዋተት
እውነታው ጋር ደርሶ ወደሁዋላ ማለት
ካልተፈቀደው ላይ አይንህን ስበረው
ከዚያም ጨክንና ሐላሉን ድፈረው !!!!
~~~~~~~~~~~~~
~~~~~~~~~~~~~
‪#‎ግልባጭ‬
ማግባት እየቻለ ወደሁዋላ ለሚለው፣ እንዲሁም ዛሬ ሰርግ ላለባቸው ላጤዎች……
ቻሉት እንግዲህ ወንዶች።
‪#‎ሴቶች_ጠብቁ‬
ሂሂሂ ከዛቻ አያልፍም ወይ ???
እኔ እፈራቸዋለሁዋ !!!! ሆሆ !!!