Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከእናቶችም አሉ……………

ከእናቶችም አሉ……………
☞ጀበናና ሲኒን የሚያመልኩ
☞ኮኮብ የሚቆጥሩ
☞በገድ የሚያምኑ
☞ጠንቋይ ስር ቀን ሌት የሚመላለሱ
☞ቀብርን የሚያመልኩ
☞ሙታንን የሚጣሩ
☞በዛፍ በድንጋይና መሰል ግኡዛን የሚባረኩ
☞ከአላህ ውጭ ላሉ የሚያርዱ
☞ከአላህ ውጭ ላሉ መስዋዕት የሚያቀርቡ
☞ችግር ሲገጥማቸው የፍጡራንን እገዛ የሚሹ
☞ይደርስልናል ብለው የሚጣሩ
☞ለጅን ለቆሌው ለዛሩ ላድባሩ በማለት ቆሎ የሚረጩ
☞ከጉዳት ይከላከልልናል ይጠብቀናል በማለት ቀለበት የሚያጠልቁ ክርን የሚያንጠለጥሉ
☞በትላልቅ ሰዎች የሚመጀኑ
☞ከአላህ ውጭ ባለ ነገር የሚምሉ።

⇄እረ ስንቱን ዘርዝሬ ስንቱን ልተወው ከላይ የጠቀስኳቸውንና መሰሎችን ሽርኪያት የሚሰሩት እናቶች የኔና ያንቺ ናቸው ። ስለዚህ እህቴ ሆይ ሽርክ አስከፊ ወንጀል ነው ከወንጀሎች ውስጥ አላህ የማይምረው ነገር ቢኖር ሽርክ( ማጋራት) ነው ። እርሱ ፈጥሮን ሳለ በርሱ ላይ ማጋራት ከባድ ወንጀል ነው።
እናም ምን ላድርግ ልትይኝ ትችያለሽ ከአስከፊው ሽርክ የምትድኝው ተውሂድን ስትማሪና በሱ ላይ ስትሰሪ ነው አላህም የፈጠረን እሱን ብቻ ለማምለክ ብቻ ቢሆን እንጂ ለሌላ አይደለም።
እናም እህቴ ሆይ አቂዳሽን የተፈጠርሽለትን አላማ በፅኑ ለማወቅ ጣሪ ብሎም በሽርክ ተዘፍቀው እየዋኙ ያሉትን እናቶችሽን ለማስተማርና ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ዘንድ አስፈላጊ ትምህርትን መስጠት የአንቺ ሃላፊነት ነው!! ይህን ሃላፊነት መወጣት የምትችይው ስለ ተውሂድ ምንነት ስትረጂ አቂዳሽን ስትማሪና በተግባር ስታውይ ነው። የሰው ልጅ የዚች አለም ህይወት ሆነ የመጪው አለም ፈላህ ነጃህ የሚወጣው በተውሂድ ነውና
እህቴ ሆይ ወደ ተውሂድ እጠራሻለሁ አንቺንም ቤተሰቦችሽንም ከአስከፊው ሽርክ ትድኑ ዘንድ።