Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የጓደኝነት ተፅእኖ

ustaz jamal yassen hafizahulilhe
የጓደኝነት ተፅእኖ
ኢብኑ በጣህ – አላህ ይዘንላቸውና– እንዲህ ይላሉ:–
ወንድሞቼ እወቁ:
ሰዎችን ከአህለሱና ወልጀማዓ መንገድ ያስወጣቸውን፣
~ ወደ ቢድዓ እና አስፀያፊ ተግባር እንዲገቡ ያስገደዳቸውን፣
~ በልቦናቸው ላይ የመቅሰፍትን በር የከፈተባቸውን፣
~ ከእውቀታቸውም ላይ የእውነታን ብርሃን የጋረደባቸውን ምክንያት አሰብኩኝና ሁለት ገፅታ እንዳለው ደረስኩበት።
አንደኛው:–
☞ አስተዋይ ለሆነ ሰው ማወቁ የምይጠቅመውና ኣለማወቁም የማይጎዳው እንዲሁም ሙእሚን ለሆነም ሰው ይህን ነገር መገንዘቡ የማይጠቅመው የሆነን ተራ ጉዳይ ተከታትሎ መፈላፈል፣ መጨናነቅና ጥያቄን ማብዛት ሲሆን፤
ሌላኛው ደግሞ:-
☞ ፈታኝ ነገር ያመጣ ይሆናል ተብሎ የሚፈራ የማያስተማምንና መጎዳኘቱም ልብን የሚያበላሽ ከሆነ ሰው ጋር መቀማመጥ (መጎዳኘት) ነው።
📓ምንጭ:– " አልኢባና አልኩብራ" ኢብኑበጣህ (1/390)·