Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ባለቤትህን ትንከባከባለህ?

'‎☞ የተንቢሀት መልእክት ለባሎች 

󾀽 ባለቤትህን ትንከባከባለህ?󾀽

ኢስላም ሴትን የማላቅና ለርሷ እንክብካቤ የመጨነቅ ደረጃን ይበልጥ ከፍ በማድረግ ባል ቢጠላት እንኳ እንዲንከባከባት ያዘዋል። ይህ፣ ሴት ልጅ በዚህ ሐይማኖት ካልሆነ በቀር በየትኛውም የታሪክ ወቅትና አስተሳሰብ አግኝታው የማታውቀው ጸጋ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል፡-

وَعَاشِرُوهُنَّ بِالْمَعْرُوفِ ۚ فَإِن كَرِهْتُمُوهُنَّ فَعَسَىٰ أَن تَكْرَهُوا شَيْئًا وَيَجْعَلَ اللَّهُ فِيهِ خَيْرًا كَثِيرًا

“በመልካምም ተኗኗሩዋቸው። ብትጠሉዋቸውም (ታገሱ)። አንዳችን ነገር ብትጠሉ አላህም በእርሱ ብዙ ደግ ነገርን ሊያደርግ ይቻላልና።”  (ኒሣእ፤ 19)

ይህ ቁርአናዊ መልእክት የወንዱን ሕሊና በመንካት ቁጣውን ያበርዳል። ለሚስቱ ያለውን ጥላቻ ይቀንሳል።

ኢስላም በእንዲህ ዓይነት መመሪያዎች ጋብቻ በቀላሉ እንዳይናጋ፣ ስሜቶች በተለዋወጡ ቁጥር ለአደጋ እንዳይጋለጥ ይጠብቀዋል።

ዑመር ቢን አል ኸጣብ ሚስቱን ስላልወደዳት ሊፈታት ላሰበ ሰው የሰጡት ምክር ድንቅ ነው። እንዲህ አሉት፡-

“ወዮልህ፣ ቤት የሚገነባው በፍቅር ላይ ብቻ ነውን? እንክብካቤና ስነ ምግባር የት ጠፋ?”

በኢስላም የጋብቻ ትስስር ከጊዜያዊ ስሜቶችና ከእንስሳዊ ዝንባሌዎች በላይ ነው። ሆደ ሰፊ፣ ታጋሽ፣ ለሌሎች ሕይወት አሳቢ የሆነ ሙስሊም ከሚጠላት ሚስቱ ጋር ያለው ግንኙነት ከእንስሳዊ ስሜት፣ እንዲሁም ከትርፍና ከኪሣራ በላይ የሆነ ስሜት ነው።

ምንጊዜም ቢሆን የአምላክን ቃል ያከብራል። ሚስቱን ይንከባከባል። ቢጠላት እንኳ። ምን አልባትም አላህ በጋብቻቸው ውስጥ በርካታ በጎ ነገሮችን አድርጎ ሊሆን ይችላል። አንድ ሰው አንድን ነገር ሊጠላ ይችላል። ግና ምን አልባትም አላህ በዚያ ነገር ውስጥ በጎ ሁኔታን አኑሮለት ይሆናል። እናም ሙስሊም ሲወድም ሲጠላም በልክ ነው። ሲወድ  ፍቅር እውር ነው ብሎ እውር አይሆንም። የአእምሮውን ልጓም አይስትም። በጭፍኑ አይጎተትም። ሲጠላም እንደዚሁ ሚዛን አይስትም። በሁለቱም ሁኔታዎች ውስጥ ፍጹም ሚዛናዊ ይሆናል።

ሴት ልጅ ባሏ የቱን ያህል ቢጠላትም ከበጎ ባህሪዎች የነጠፈች እንደማትሆን የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ይናገራሉ። ይህን በጎ ጎኗን ትቶ የሚጠላውን ጎኗን ማጉላት አግባብ አይደለም።

 قال صلى الله عليه وسلم ( لا يَفْرَكْ مُؤْمِنٌ مُؤْمِنَةً إِنْ كَرِهَ مِنْهَا خُلُقًا رَضِيَ مِنْهَا آخَرَ ) رواه مسلم 

“ሙእሚን ወንድ ሙእሚን ሴትን አይጥላ። አንድ ባህሪዋን ባይወደው ሌላውን ይወደዋል።” (ሙስሊም)

ተንቢሀት... ሙስሊም ሴቶችን የተመለከቱ ህግጋት
www.facebook.com/tenbihat‎'

☞ የተንቢሀት መልእክት ለባሎች

www.facebook.com/tenbihat