Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ፍቅር በተግባር

'‎የነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
           ፍቅር በተግባር 
        󾁅󾁅󾁅󾁅󾁅

  ልጆች መሰረታዊ የዲናቸውን ትምህርት የሚያገኙት ከወላጆች ሲሆን በተለይም በቤት ውስጥ የእናት ሚና ከፍተኛው ነው።

  አባት ባብዛኛው ውጫዊ ጉዳይ ላይ ስለሚጠመድም የሱ ብቃት የሚለካው ለልጆቹ መማር በሚያመቻቸውና በሚያደርገው ክትትል ላይ ነው።

 ይሁንና ሁለቱም ባገኙት አጋጣሚ ልጃቸውን መቅረፅ ይችላሉ።

  ለዛሬ በተለይ እናቶች ልጆቻቸውን በየእለቱ መቀየር የሚችሉበትን ዘዴ ልጠቁማቸው ወደድኩ።

  ውድ ወላጅ

  ልጆችዎን አጣጥበው ፀጉራቸውን ሲያበጥሩና ሲያለብሷቸው እንዲሁም ሲመግቧቸው እንኳን እንዲሁ በተለምዶ የሚደረግ ነገር አድርገው ብቻ አይለፉት። 

  ከተውሂድ ጀምሮ ሁሉንም ስርዓቶች በትንሽ በትንሹ ለማስተማር በየክስተቶቹ ተያያዥ የሆኑ ቁርኣናዊ ወይም ሀዲሳዊ መረጃዎችን ለልጅዎ ቀለል አድርገው ይንገሩ።

  ለምሳሌ ልጅዎን በአባቱ ወይም በእናቱ ከማስፈራራት ይልቅ መፍራት ያለበት አላህን እንደሆነ መንገር

• ለወላጁ መታዘዝ ያለበትም መልእክተኛው ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ስላዘዙት እንደሆነ ማሳወቅ

• ውሸትን አላህ እንደማይወድ መጠቆም
 
• የሰውን ሀቅ ያለፈቃዱ መውሰድን ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንደከለከሉ እና 

~ የመሳሰሉትን በአቅምዎ ልክ ያስታጥቁዋቸው።

  ለዛሬ እንዲሞክሩት ሸይኽ ሙሀመድ ዑመር ባዝሙል አላህ ይጠብቃቸውና ያሉትን ላካፍላችሁ:_

  የልጅህን ፀጉር ስታበጥር ይህን የምታደርገው ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም

 «ፀጉር ያለው ሰው ይንከባከበው።»
ብለው ስለነገሩን ነው የምንከባከብልህ ብሎ ይንገረው ብለዋል።

ሀዲሱም ከአቢ ሁረይራ ረዲየላሁ ዐንሁ የተወራና፤ አቢ ዳዉድ ዘግበውት ሸይኽ አልባኒ ረሂመሁሙላህ ሰሂህ ያሉት ነውና ይመልከቱት☞

عن أبي هريرة رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال
 ( مَنْ كَانَ لَهُ شَعْرٌ فَلْيُكْرِمْهُ ) 
رواه أبو داود (3632) في صحيح أبي داود
 وصححه الشيخ الألباني في صحيح الجامع 6493

  በቂ መረጃ ከያዙ እርስዎም አስተማሪ ነዎትና ከልጅዎ ይጀምሩ።

  በዚህም የመልእክተኛውን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሱና ዲናቸውን ሊያስተምሩ ይችላሉና።

አላህ እኔንም እርሰዎንም ምርጥ ወላጅ ያድርገን❗
________
󾔧12 Jumadussani 1436
     02 ኤፕሪል 2015‎'
የነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም

አላህ እኔንም እርሰዎንም ምርጥ ወላጅ ያድርገን
________
12 Jumadussani 1436
02 ኤፕሪል 2015

Post a Comment

0 Comments