Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ፦ ኩራት ተፈልጎበት ከሆነ (ሱሪንና የመሳሰሉትን) የማስረዘም ቅጣት ምንድን ነው? ኩራት ተፈልጎበት ካልሆነስ ቅጣቱ ምንድን ነው? የአቡበክርን ሐዲስ በመከራከሪያነት (በማሰረጃነት) ለሚያቀርብ ሰው ምን መልስ ይሰጠዋል? (ሸኽ መሀመድ ኢብኑ ሷሊህ አል- ኡሰይሚን ረሂመሁላህ)

'By Wendemachen Taju Nasir
ጥያቄ፦ ኩራት ተፈልጎበት ከሆነ (ሱሪንና የመሳሰሉትን) የማስረዘም ቅጣት ምንድን ነው? ኩራት ተፈልጎበት ካልሆነስ ቅጣቱ ምንድን ነው? የአቡበክርን ሐዲስ በመከራከሪያነት (በማሰረጃነት) ለሚያቀርብ ሰው ምን መልስ ይሰጠዋል? 

መልስ፦ ልብስን ማስረዘም ኩራት ተፈልጎበት ከሆነ ቅጣቱ በቂያማ ቀን አላህ ወደሱ አለማየቱ፣አለማናገሩ፣ እሱን አለማጥራቱና አሳማሚ ቅጣት ለሱ መኖሩ ነው። ኩራት ተፈልጎበት ካልሆነ ግን ቅጣቱ ከቁርጭምጭሚት በታች በወረደው ልክ በእሳት መቅጣቱ ነው። ነቢዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦«በቂያማ ቀን አላህ የማያናግራቸው፣ ወደነሱም የማይመለከት፣ የማያጠራቸውና አሰማሚ ቅጣትም ያለላቸው ሥስት አይነት ሰዎች አሉ። እነሱም፦(ሽርጡን) የሚያስረዝም፣ተመፃዳቂ እና ሸቀጡን በውሸት መሓላ የሚሸጥ ናቸው።» (ሙስሊም)።በሌላ ሐዲስ ደግሞ ነቢዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) «ለኩራት ብሎ ልብሱን መሬት ላይ የሚጎትት ሰው በቂያማ ቀን አላህ ወደሱ አይመለከትም» ብለዋል (ቡኻሪና ሙስሊም)።ይህ ለኩራት ብሎ ልብሱን ለሚጎትት ሰው ነው።

ኩራትን ሳይፈልግ እንዲሁ ያስረዘመን ሰው በተመለከተ ግን አቡ ሁረይራ ባስተላለፉልን ሐዲስ ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ «ከቁርጭምጭሚት በታች በሽርጥ የተሸፈነ እሳት ይገባል» (ቡኻሪ)።ይህ ከኩራት ጋር አልተቆራኘም። በኩራት የጎተተንሰው በተመለከተ ከላይ የተጠቀሰው ራሱን የቻለ ሐዲስ ስላለ ይህንን ከኩራት ጋር ማቆራኘትም ትክክል አይሆንም። አቡሰዒድንል ኹድሪ ባስተላለፉልን ሐዲስ ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦«የሙእሚን ሽርጥ እስከ መሀል ባት ነው።ከመሐል ባት እስከ ቁርጭምጭሚት ድረስ በየትኛውም ቦታ ላይ ቢሆን ችግር የለውም።ከዚያ በታች ከሆነ ግን እሳት ውስጥ ነው። ለኩራት ብሎ ልብሱን የጎተተ ሰው በቂያማ ቀን አላህ ወደሱ አይመለከትም።»
(አህመድ፣ማሊክ፣አቡዳውድ፣ነሳኢ፣ኢብኑማጃህ እና ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል።) 
ሁለቱ ድርጊቶች የተለያዩ እንደመሆናቸው ቅጣቶቻቸውም የተለያዩ ናቸው።ሑክሙና ሰበቡ እስከተለያዩ ድረስ ጥቅል የሆነውን ውስን ወደሆነው መውሰድ አይቻልም። እርስ በርስ መፃረርን ያስከትላልና።

የአቡበክርን ሐዲስ በማስረጃነት ያመጣብንን ሰው ደግሞ በሁለት መልኩ ማስረጃ ሊሆንህ አይችልም እንለዋለን፣

አንደኛ፦ አቡበክር (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው) «ካልተቆጣጠርኩት በስተቀር የአንዱ ጎን ልብሴ ወደታች ወረድ ይልብኛል» ነው ያሉት፥(ቡኻሪ)። አቡበክር በራሳቸው ምርጫ አይደለም ልብሳቸውን ወደታች የሚያወርዱት። ራሱ ወረድ ይልባቸዋል። ከዚህም ጋር ይቆጣጠሩታል። እነዚህ ልብሳቸውን እያስረዘሙ ኩራትን ፈልገን አይደለም የሚሉት ሰዎች ግን የሚያስረዝሙት ሆን ብለውና በፍላጎታቸው ነው። ስለዚህም እንዲህ እንላቸዋለን፦ ኩራትን ሳትፈልጉ ግን በራሳችሁ ፍላጎት ልብሶቻችሁን ከቁርጭመጭሚት በታች ካወረዳችሁ ከቁርጭምጭሚት በወረደው ልክ ትቀጣላችሁ። በኩራት ልብሶቻችሁን የምትጎትቱ ከሆናችሁ ግን ከዚያ እጅግ በላቀ ነገር ትቀጣላችሁ። በቂያማ ቀን አላህ አያናግራችሁም፤ ወደናንተ አይመለከትም፤ አያጠራችሁምም፤ አሳማሚ ቅጣትም አለላችሁ።

ሁለተኛው፦ አቡበክር ለኩራት ብለው ይህን እንደማያደርጉ ነቢዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መስክርውላቸዋል። ወይም ተዝኪያ አድርገውላቸዋል። ለኩራት አይደለም የምናስረዝመው የሚሉት እነዚህ ሰዎች ይህንን ተዝኪያና ሸሐዳ ከነቢዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አግኝተዋልን? በፍፁም። ነገር ግን ሸይጣን አንዳንድ ሰዎችን የሚሰሩዋቸውን ሥራዎች ትክክል ሊያስመስልባቸው ሲል ከቁርአንና ከሱና «ሙተሻቢህ» የሆኑትን «ኑሱሶች» (አንቀጾች) እንዲጠቀሙ ያደርጋቸዋል። አላህ የፈለገውን ሰው ወደ ትክክለኛ መንገድ ይመራል። እኛንም እነሱንም አላህ እንዲመራን እንማፀነዋለን።

(ሸኽ መሀመድ ኢብኑ ሷሊህ አል- ኡሰይሚን ረሂመሁላህ)'
Taju Nasir

(ሸኽ መሀመድ ኢብኑ ሷሊህ አል- ኡሰይሚን ረሂመሁላህ)