Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ከአላህ ዚክር ውጭ ያለን ወሬ አታብዙ! ወሬ ማብዛት ልብን ያደርቃል።

የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ከአላህ ዚክር ውጭ ያለን ወሬ አታብዙ! ወሬ ማብዛት ልብን ያደርቃል።
በርግጥም ረሱለል ሁዳ እውነት ተናግረዋል ፣ ወሬ አታብዙ…………… የሰው ልጅ የማያገባውን የማይመለከተውን ነገር መጠየቅና ማውራቱ ፋይዳ ቢስነት ነው በተለይ በዚህ በኢንተርኔት ስንቱ ነገር ይወራል በአላህ መንገድ ላይ መተዋወስ ቀርቶ እንዲሁ የማይጠቅም ነገር ሲወራ ሲዘከር ውሎ።ያድራል ዛሬም ያወራል ነገም ያወራል…………………… እንዲሁ ሲያወራ ጌታውን ከማስታወስ ዘንግቶና አፈንግጦ በማይጠቅመው ነገር ተጠምዶ አጀሉ ይደርሳል ፣ ከጌታውም ጋር በሚገናኝ ጊዜ ባሳለፈው ህይወትና ጊዜ ይጠየቃል፣ ምን ብሎ ይመልሳል፣ በማይረባ ጥቅም በሌለው ነገር ተጠምጄ ጊዜየን አሳለፍኩ? ወይስ ጌታ ሆይ መልሰኝና ከደጋግ ባሮች እንዲሁም አንተን እገዛ ዘንድ ብሎ ይጠይቅ ይሆን?
ይህ ሁሉ ከመምጣቱ በፊት ዛሬ ላይ ትኩረት መስጠት ይኖርብናል በርግጥም ወሬ ማብዛት ቀልብን ይገድላል ፣አላህን ማስታወስ፣ ቀልብን ያረጥባል፣ የልብ እርጋታን ይፈጥራል፣ ወደ አሏህ ያቃርባል፣ ትልቅ ደረጃን ያጎናፅፋል፣ ይህን ሁሉ ፈድል በማይረባ እንቶ ፈንቶ ነገር አናሳልፈው ጊዜን እንጠቀምበት ኦን ላይ( on line) ቁጭ ብለሽ/ ብለህ ከማይፈቀድልን ሰው ጋር ማውራቱ ይቅርብህ/ ያጠፋል እንጂ አያለማም: ቀልብን ያደርቃል እንጂ አያረጥብም/ ከአላህ እዝነት ያርቃል እንጂ አያቃርብም ስለዚህ ይቅርብን በወሬ ብዛት የተጠቀመ ሰው አላየንም የተጎዳ ቢሆን እንጂ ፣
ኢኽዋኒ የስከዛሬው ይበቃል ከአሁን በኋላ ግን መንቃት ይኖርብናል ። ጊዜን እንጠቀም እንቅራ ኢልምን እንፈልግ አቂዳችንን ለማሳመር እንጣር ዲናችንን እንወቅ ተራ አሉባልታ ወሬ ለመተው እንሞክር።

Post a Comment

0 Comments