Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰሀቦች ማለት እነማን ናቸው??

A user's photo.
ሰሀቦች ማለት እነማን ናቸው???
የኢስላም ምሁሮች ይህን ሲያብራሩ እንዲህ ብለዋል:-
"ሰሀባ ማለት ነብዩ የአላህ ውዳሴና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁንና በህይወት እያሉ ያገኛቸውና አማኝ ሆኖ በዛው የሞተ ማለት ነው"
እንግዲህ የነርሱ መታወቂያ በዚህ መልኩ ከመገለፁ ጋር ከውቅያኖስ ላይ መጭለፍ ቢሆንብኝም እንኳን ጥቂት ደግሞ ስለነርሱ አቻ የለሽነት ለማከል እወዳለው ።
ከቁርአን ልጀምርና አላህ እነርሱ ኢስላምን በትክክል አውቀው ተግባሪዎችና ከነርሱ በኃላ በየትኛውም ዘመንና ቦታ ለሚመጡት ትውልዶች እስከ አለም ፍፃሜ ድረስ በቂና ልዩ መሪዎች እንደሆኑ እንዲህ ሲል የማይሻር ብይኑን አስተላልፋል ።
‹‹ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲሆኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ስራ የተከተላቸው አላህ ከነርሱ ወዳል ( እነርሱም ) ከርሱ ወደዋል ። በስሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ዘለአለም ነዋሪዎች ሲሆኑ ለነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል ይህ ታላቅ እድል ነው።››(9፡100)
ከዚህ ጎን ለጎንም አላህ ሶሃቦችን ካሞገሰ በኃላ አንዳንዶች ይህን የመሪነታቸውን ማእረግና ዘውድ ለመቀናቀንና ለመሻር ቆራጣና ስንኩል አመለካከታቸውን ተንተርሰው የሚፍጨረጨሩ ጎጠኛ ግለሰቦችና አንጃዎች ካሉ ለለውድቀትና ለጥመት ለመከፋፈልና ለመሰነጣጠቅ እንደሚበቁ እንዲህ ሲል ተናግሯል ።
‹‹በርሱ ባመናችሁበት ቢጤ ቢያምኑ በርግጥ ተመሩ ቢዞሩም እነርሱ በጭቅጭቅ ውስጥ ብቻ ናቸው›› (2፡137)
ነብዩም (ﷺ) የአላህ ውዳሴና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁንና ስለነዚህ ውድ ባልደረቦቻቸው ከተናገሩት ውስጥ አንዱን ብቻ እንካችሁ እላለው
<<ባልደረቦቼን አትስደቡ ። ከናንተ ውስጥ አንዳችሁ የእሁድ ተራራን ያህል ወርቅ ቢመፀውት እንካን አንዱን ያህል እንካን አይመጥንም ። ኧረ ግማሹንም >>
እዚህ ጋር ግን አትሳደቡ ሲባል አንዳንድ ሰዎች መቼ ተሳደብን ? የሚል ከእውነት የራቀን ጥያቄ ሊጠይቁ ይችላሉ ። በርግጠኝነት በግልፅ የተሳደቡ አሉ ። ነገር ግን ደግሞ ከዚህ በተለየ መልክ የሚሳደቡ ብዙዎች ናቸው ። ይህም የነርሱን መመሪያ ( አካሄድ) በሁሉም የህይወት ዘርፍ በተለይ በዳዕዋ ጠብቆ መያዝ አለበት ሲባሉ አሻፈረኝ ብለው የሚነጉዱ ናቸው።
ምክንያቱም እንደሚታወቀው አንድ ሰው ከሆነ መንገድ ወደ ሌላ መንገድ አያዘነብልም አሊያም አይዞርም የተወውን መንገድ ነውርና አላዋጣ ባይነት ቢያምንና የያዘውን መንገድ (አካሄድ) ደግሞ ምልኡነት ቢያምንበት እንጂ ። ታዲያ ከዚህ የበለጠ ለእነዚህ ውድ መሪዎች ስድብ አለን ??? ወይስ ቂሎች እንደሚሉት አንተ ልክስክስ ቆሻሻ ና ወዘተ እንዲባል ነው ምንሻው ???
ኢማሙ አህመድ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል:-
‹‹አንድን ሰው ከሰሀቦች ውስጥ አንዱንም ቢሆን እንካን በመጥፎ ቢያነሳ ካየህው እስልምናውን ተጠራጠር ።››
ጌያዬ ጥራት ይገባው ሙስሊም ነው አይደላም ብለህ ተጠራጠር ማለት እኮ ነው ይገርማል።
አላህ የሶሃባዎችን መንገድ የምንከተል ያድርገን!
በኡሙ ዓብደላህ ሙሀመድ
— with Ummu Abdellah Muhammed.

Post a Comment

0 Comments