Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መልካም ነገርን ሁሉ ሚሻ የአሊሞችን ምክር ዋጋ ይስጥ!!! የቀድሞው ሙፍቲ እና የዓለማችን ታላቅ ሸይኽ፤ ዓብዱልዓዚዝ ኢብኑ ዓብዲላህ ኢብኑ ባዝ እንዲህ ብለዋል፤

መልካም ነገርን ሁሉ ሚሻ የአሊሞችን ምክር ዋጋ ይስጥ!!!
የቀድሞው ሙፍቲ እና የዓለማችን ታላቅ ሸይኽ፤ ዓብዱልዓዚዝ
ኢብኑ ዓብዲላህ ኢብኑ ባዝ እንዲህ ብለዋል፤
«መልካም አቀራረብ ሰዎች እውነትን እንዲቀበሉ ከሚያደርጉ ዋና
ዋና ነገሮች አንዱ ነው። ጽንፈኝነት ያለበት መጥፎ አካሄድ
ደግሞ፤ እውነት ተቀባይነት እንዳያገኝ፣ሁከትና ስጋት እንዲነግስ፣
ግፍና ወሰን መተላለፍ እንዲፈጸም ያደርጋል።ከዚህ ጋር አብሮ
የሚታየው አንዳንድ ሰዎች የሚፈጽሙት የተቃውሞ ሰልፍ ነው።
ለዳዕዋና በዳዕዋ ላይ በተሰማሩ ሰዎች ላይ በጣም መጥፎ
መዘዝ አለው። ለዳእዋና ችግሮችን ለማስወገድ መንገዶቹ
በጎዳናዎች ...ላይ የሚደረጉ ሰልፎችና መፈክሮች አይደሉም።
ትክክለኛው የእርምት መንገድ፤ ለሀገር መሪ፣ ለሹማምንት፣
ወይም ለጎሳ መሪዎች በመጻፍ ወይም በአካል ሄዶ ጉብኝት
በማድረግ ምክርን መለገስ ነው እንጂ የተቃውሞ ሰልፍ እና ሁከት
አይደለም። የአላህ መልዕክተኛﻩ በመካ አስራ ሶስት ሲቆዩ
የተቃውሞ ሰልፍን አልተጠቀሙም፣ ሰዎችን በማገትና ንብረትን
በማውደምም አላስፈራሩም። ይህ አይነቱ አካሄድ (በዲን ስም
ሲፈጸም) ኢስላማዊ ዳዕዋንና የዳዕዋ ሰዎችን እንደሚጎዳ፣
ስርጭቱንም እንደሚገድበው፣ መሪዎችንና ባለስልጣናትንም
ዳዕዋን እንዲጠሉና በተገኘው መንገድ ለመጻረር እንደሚገፋፋ
ጥርጥር የለዉም። ሰልፈኞች ጥሩን ነገር ቢያልሙም የሚከሰተው
ግን ተቃራኒው ነው። ዳዒ የሆነ ሰው፤ እንዲህ ዓይነት ዳዕዋንና
ዱዓቶችን የሚጎዳ፣ የዳዕዋ መንገዶችን የሚያጠብ እና ብሎም
ዳዕዋን የሚያስቆም አካሄድን ከሚመርጥ፤ምንም እንኳ ጊዜ
ቢፈጅበት፤ የአላህን መልዕክተኞች እና የቅን ተከታዮቻቸውን ፈለግ
ቢከተል ይበጀዋል። ሀይልና ብልሀት ከአላህ ብቻ ነው»
ምንጭ- የኢስላማዊ ጥናቶች መጽሄት 38ኛ እትም ገጽ 210
قال الشَّيخ عبد العزيز بن باز -رحمه الله-: «فالأسلوبُ الحسنُ مِنْ أعظمِ الوسائل لقَبولِ الحقِّ، والأسلوبُ السَّيِّء العنيفُ مِنْ أخطَر الوسائل في ردِّ الحقِّ وعَدَم قبولِه، أو إثارةِ القلاقل والظُّلم والعُدوان والمضاربات، ويُلحَق بهذا البابِ ما يَفْعلُه بعضُ النَّاس مِنَ المظاهرات الَّتي تُسَبِّب شرًّا عظيمًا على الدُّعاة، فالمسيرات في الشَّوارِع والْهُتافاتُ ليسَت هيَ الطَّريق للإصلاح والدَّعوة، فالطَّريقُ الصَّحيحُ بالزِّيارة والمكاتبات بالَّتي هي أحسنُ فتنصَحُ الرَّئيسَ والأميرَ وشيخَ القبيلةِ بهذه الطَّريقةِ، لا بالعُنْفِ والمظاهرَةِ، فالنَّبيُّ صلَّى الله عليه وسلَّم مكثَ في مكَّة ثلاثَ عشرةَ سنةً لم يَستعمل المظاهرات ولا المسيرات، ولم يُهَدِّدِ النَّاسَ بتخريبِ أموالِهم واغتيالِهم، ولا شكَّ أنَّ هذا الأسلوبَ يَضرُّ بالدَّعوةِ والدُّعاةِ، ويَمنَعُ انتشارَها، ويَحمِلُ الرُّؤساءَ والكبارَ على مُعاداتِها ومُضادَّتِها بكلِّ مُمْكِن، فهُم يُريدون الخيرَ بهذا الأسلوب، ولكن يَحصُل به ضدُّه، فكَونُ الدَّاعي إلى الله يَسلُك مسلكَ الرُّسل وأتباعِهم -ولو طالَت المدَّة- أولى به مِنْ عملٍ يضرُّ بالدَّعوة ويُضايِقُها أو يَقضِي عليها، ولا حولَ ولا قوَّةَ إلاَّ بالله» مِنْ مجلَّة «البحوث الإسلاميَّة» العدد38 ص210.