Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የዘመናችን ዑለማዎች ጀመዐቱል አሕባሽ ላይ መልስ ከሰጡት በላይ ጀመዐቱል ኢኽዋን ላይ ሰጥተዋል!

የዘመናችን ዑለማዎች ጀመዐቱል አሕባሽ ላይ መልስ ከሰጡት በላይ ጀመዐቱል ኢኽዋን ላይ ሰጥተዋል!
ጀመዐቱል አሕባሽ ግልፅ ጥመት ላይ ያለ አንጃ ከመሆኑም ጋር የተበከለ አቂዳውን ለሕዝቡ ቢያሰራጭም ከብዙ ጥቂት ቢያገኝ ነው! (ቀድሞውኑ በአእምሮ ጋር የሚላተም ነውና)
ጀመዐቱል ኢኽዋን ግን እንደ እስስት ተለዋዋጭ ከመሆኑም ጋር እጅጉን ሲበዛ በሹብሐ (ማምታቻና ማደናገሪያ) የታጨቀ አደገኛ አንጃ ነው ። በየሄደበት አካባቢውን መምሰል የሚችል የእስስትነት ባሕሪው ብዙዎችን ሊሸውድና የሕዝቡን ስስ ብልት እየፈለገ እራሱን የሕዝብ ጠበቃና ‘ጉዳይ አስፈፃሚ’ አድርጎ ስለሚሾም ለብዙዎች መታለል ም/ት ነው ።
ጀመዐቱል ኢኽዋንን በጥመት ቡድንነቱ ከመሠከሩበት ታላላቅ ስመጥር ዑለማዎች በጥቂቱ
— ኢትዮጵያዊው ሸኽ ሙሐመድ አማን አል ጃሚ (ረሒመሁላህ)
— አልባኒያዊው ሸኽ ናስሩዲን አል አልባኒ (ረሒመሁላህ)
— የመናዊው ሸኽ ሙቅቢን ቢን ሃዲ (ረሒመሁላህ)
— ስዑዲያዊው ሸኽ አሕመድ ቢን የህያ አን–ነጅሚ (ረሒመሁላህ)
— ሱዑዲያዊው ታላቅ ሸኽ ሙጀዲድ ኢብኑ ባዝ (ረሒመሁላህ)
— ሱዑዲያዊው ኢማም ሸኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊህ አል ዑሰይሚን (ረሒመሁላህ)
— በሕይወት ካሉት
ፈውዛን፣ ሉሃይዳን፣ ረስላን፣ አሉ ሸይኽ፣ ረቢዕ፣ ዑበይድ፣ የሱዑዲ ዐረቢያ የፈታዋ ቋሚ ኮሚቴ ወ ዘ ተ
————
ታዲያ ምን ትጠብቃለህ ጎበዝ?
ዛሬውኑ ወደ ጥንት የጠዋቱ የሰለፎች መንገድ ና!
አላህ በሐቅ ላይ ያፅናን

Post a Comment

0 Comments