Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ፦ ወላእና በራእ ምንድን ነው? ሸኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል- ኡሰይሚን ረሒመሁላሕ



ጥያቄ፦ ወላእና በራእ ምንድን ነው?
መልስ፦ ወላእና በራእ ለአላህ ሲባል አላህ ከጠላቸውና ከራቃቸው ነገሮች ሁሉ መራቅና መጥላት ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦
﴿قَدْ كَانَتْ لَكُمْ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌۭ فِى
ٓ إِبْرَٰهِيمَ وَٱلَّذِينَ مَعَهُۥٓ إِذْ قَالُوا۟ لِقَوْمِهِمْ إِنَّا بُرَءَٰٓؤُا۟ مِنكُمْ وَمِمَّا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ كَفَرْنَا بِكُمْ وَبَدَا بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمُ ٱلْعَدَٰوَةُ وَٱلْبَغْضَآءُ أَبَدًا ﴾
« በኢብራሂምና በእነዚያ ከእርሱ ጋር በነበሩት (ምእምናን) መልካም መከተል አለቻችሁ፡፡ ለሕዝቦቻቸው «እኛ ከእናንተ ከአላህ ሌላ ከምትግገዙትም ንጹሖች ነን፡፡ በእናንተ ካድን፡፡ በአላህ አንድ ብቻ ሲኾን እስከምታምኑ ድረስ በእኛና በእናንተ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር ተገለጸ፡፡» ባሉ ጊዜ (መልካም መከተል አለቻችሁ)፤…»(አል-ሙምተሒና 60፥4)
ኢብራሒም ከናንተ ንፁህ ነን በኛና በናንተ መካከል ጥላቻ አለ ያሉት ሙሽሪኮችን ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦
﴿وَأَذَٰنٌۭ مِّنَ ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦٓ إِلَى ٱلنَّاسِ يَوْمَ ٱلْحَجِّ ٱلْأَكْبَرِ أَنَّ ٱللَّهَ بَرِىٓءٌۭ مِّنَ ٱلْمُشْرِكِينَ ۙ وَرَسُولُهُۥ ۚ﴾ٍ
« (ይህ) ከአላህና ከመልክተኛው በታላቁ ሐጅ ቀን የወጣ አላህ ከአጋሪዎቹ ንጹሕ ነው መልክተኛውም (እንደዚሁ ንፁህ ናቸው)፤… በማለት ወደ ሰዎች የሚያደርስ ማስታወቂያ ነው፤…» (አልተውባ 9፥3)
ማንኛውም ሙእሚን ከሙሽሪክና ከካፊር ንፁህና የራቀ መሆኑን ማወጅ አለበት። ይህ ሰዎችን በተመለከተ ነው። እንደዚሁም ሙስሊም ሁሉ አላሕና መልክተኛው ከማይወዷቸው ሥራዎች ሁሉ የሚያስከፍሩ ባይሆንም እንኳን ንፁህ መሆን አለበት። ከአመፅ (ፉሱቅ)፤ከእምቢተኛነት(ዒሲያን) እና ከመሳሰሉት። አላህ እንዲህ ይላል፦
﴿ْ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ حَبَّبَ إِلَيْكُمُ ٱلْإِيمَٰن
َ وَزَيَّنَهُۥ فِى قُلُوبِكُمْ وَكَرَّهَ إِلَيْكُمُ ٱلْكُفْرَ وَٱلْفُسُوقَ وَٱلْعِصْيَانَ ۚ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلرَّٰشِدُون﴾َ
«… ግን አላህ አምነትን ወደናንተ አስወደደ፡፡ በልቦቻችሁም ውሰጥ አጌጠው፡፡ ክህደትንና አመጽንም እንቢተኛነትንም ወደናንተ የተጠላ አደረገ፡፡ እነዚያ (እምነትን የወደዱና ክሕደተን የጠሉ) እነርሱ ቅኖቹ ናቸው፡፡» (አል-ሑጅራት 49፥7)
አንድ ወንጀል የሚሰራ ሙእሚን ካለ በኢማኑ ምክንያት እንወደዋለን ወዳጃችን እናደርገዋለን። በሚሰራው ወንጀል ደግሞ እንጠለዋለን። ይህ በራሳችን ህይወት ላይም ይከሰታል። ለምሳሌ በጣም መራራ የሆነ መድሀኒት ምሬቱን እየጠላህ ትወስደዋለህ። ከበሽታ ስለሚፈውስ ደግሞ ትፈልገዋለህ። ወንጀል የሚሰራ ሙኡሚን እንደዚሁ ነው። አንዳንድ ሰው ሙኡሚን ሆኖ ወንጀል የሚሰራውን ሰው ከካፊር የበለጠ ይጠላዋል። ይህ የሚያስገርም ነው። ካፊር የአላህ፣የመልክተኛውና የምእመናን ጠላት ነው።ከልብ ልንጠላው ይገባል። አላህ እንዲህ ይላል፦
﴿يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَتَّخِذُوا۟ عَدُوِّى وَعَدُوَّكُمْ أَوْلِيَآءَ تُلْقُونَ إِلَيْهِم بِٱلْمَوَدَّةِ وَقَدْ كَفَرُوا۟ بِمَا جَآءَكُم مِّنَ ٱلْحَقِّ يُخْرِجُونَ ٱلرَّسُولَ وَإِيَّاكُمْ ۙ أَن تُؤْمِنُوا۟ بِٱللَّهِ رَبِّكُمْ إِن كُنتُمْ خَرَجْتُمْ جِهَٰدًۭا فِى سَبِيلِى وَٱبْتِغَآءَ مَرْضَاتِى ۚ تُسِرُّونَ إِلَيْهِم بِٱلْمَوَدَّةِ وَأَنَا۠ أَعْلَمُ بِمَآ أَخْفَيْتُمْ وَمَآ أَعْلَنتُمْ ۚ وَمَن يَفْعَلْهُ مِنكُمْ فَقَدْ ضَلَّ سَوَآءَ ٱلسَّبِيل﴾
ِ
«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጠላቶቼንና ጠላቶቻችሁን ወዳጆች አድርገችሁ አትያዙ፡፡ ከእውነቱ የመጣላችሁን ሃይማኖት በእርግጥ የካዱ ሲኾኑ ውዴታን ወደእነርሱ ታደርሳላችሁ፡፡ መልክተኛውንና እናንተን በአላህ በጌታችሁ ስላመናችሁ (ከመካ) ያወጣሉ፡፡ በመንገዴ ለመታገልና ውዴታዬን ለመፈለግ የወጣችሁ እንደኾናችሁ (ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙዋቸው)፡፡ እኔ የምትደብቁትንና የምትገልጹትን ሁሉ የማውቅ ስኾን ወደእነርሱ በፍቅር ትመሳጠራላችሁ፡፡ ከእናንተም (ይህንን) የሚሠራ ሰው ቀጥተኛውን መንገድ በእርግጥ ተሳሳተ፡፡» (አል-ሙምተሒናህ 60፥1)
﴿۞ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَتَّخِذُوا۟ ٱلْيَهُودَ وَٱلنَّصَٰرَىٰٓ أَوْلِيَآءَ ۘ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَآءُ بَعْضٍۢ ۚ وَمَن يَتَوَلَّهُم مِّنكُمْ فَإِنَّهُۥ مِنْهُمْ ۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلظَّٰلِمِين﴾َ
«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ፡፡ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ረዳቶች የሚያደርጋቸው ሰው እርሱ ከነርሱ ነው፡፡ አላህ አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም፡፡» (አል- ማኢዳ 5፥51 )
እነዚህ ኩፍሮች የራስህን ሀይማኖት ሽጠህ የነርሱን እስከምትከተል ድረስ አይወዱህም አላህ እንዲህ ይላል፦
﴿وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ ٱلْيَهُودُ وَلَا ٱلنَّصَٰرَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ۗ﴾
«አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፤…» (አል-በቀራ2፥120)
﴿وَدَّ كَثِيرٌۭ مِّنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ لَوْ يَرُدُّونَكُم مِّنۢ بَعْدِ إِيمَٰنِكُمْ كُفَّارًا ﴾
ۭ
«ከመጽሐፉ ባለቤቶች ብዙዎች… እውነቱ ከተገለጸላቸው በኋላ ከነፍሶቻቸው በኾነው ምቀኝነት ከእምነታችሁ በኋላ ከሓዲዎች አድርገው ሊመልሱዋችሁ ተመኙ።» (አል-በቀራ2፥109)
ይህ ሁሉንም የኩፍር አይነት ይመለከታል፦ ክህደትን፣ መፃረርን፣ ሽርክንና ኢልሀድን።
ሥራዎችን በተመለከተ ደግሞ ከሁሉም ሐራም ከሆኑ ሥራዎች ንፁህ (በሪእ) መሆን አለብን።ሐራም የሆኑ ስራዎችን መላመድም ሆነ መስራት የለብንም። ወንጀል የሚሰራውን ሙኡሚን ከወንጀል ስራው ንፁህ እንሆናለን፤ በዚህ ስራው እንርቀዋለን። ነገር ግን ባለው ኢማን ምክንያት እንወደዋለን እናቀርበዋለን(ወላእ) እናደርጋለን።
(ሸኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል- ኡሰይሚን ረሒመሁላሕ)