Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኡሡሉ ሠላሣ ክፍል 19

'አሠላሙ አለይኩም ወራህመቱላሒ ወበረካቱ 

ኡሡሉ ሠላሣ ክፍል 19 

የኪታቡ ፀሀፊ እንዲህ አሉ 

ከሀዲስ መረጃ  0·5   

የሙእሚኖች መሪ የሆነው ዑመር ኢብኒ ኸጣብ እንዲህ አለ። “የሆነ ቀን ከአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] ጋር ተቀምጠን እያለ፡ በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው፥ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰ፥ የመንገደኛ ምልክት የማይታይበት፥ ከኛ ውስጥም ማንም የማያውቀው ሰውዬ ብቅ አለና እነብዩ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] ጋር ተቀመጠ። ጉልበቱን ከጉልበታቸው ጋር አገጣጠመ፥ መዳፉንም ታፋው ላይ አስቀመጠ። ከዛም አንተ ሙሓመድ ሆይ! ስለ ኢስላም ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ኢስላም ማለት ፦ በእውነት የሚመለክ ጌታ አንድ አላህ ብቻ ነው ብሎ እና ሙሓመድም የአላህ መልእክተኛ ናቸው ብሎ መመስከር፣ ሶላትን በወቅቱና ቀጣይነት ባለው መልኩ መስገድ፣ ዘካን ማውጣት፣ ረመዳንን መጾም፣ የአላህ ቤትን ከቻልን መጎብኘት።” ሰውየውም “እውነት ተናገርክ” አለ። ዑመርም እንዲህ አለ “በሱ ተገረምን! እሳቸውን ይጠይቃል መልሶ እውነት ተናገርክ ይላቸዋል!” ከዛም ሰውየው ቀጠለና ስለ ኢማን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ[ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ኢማን ማለት ፦ በአላህ ማመን፣ በመላኢኮች ማመን፣ በመጻህፍት ማመን፣ በመልእክተኞች ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን፣ በአላህ ውሳኔ ከፋም በጀም ማመን” ሰውየውም “እውነት ተናገርክ” አለ። ከዛም ሰውየው ቀጠለና ስለ ኢሕሳን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ኢሕሳን ማለት አላህን እንደምታየው አድርገህ ልታመልከው ነው፥ አንተ ባታየውም እሱ ያየሃል እና።” ከዛም ሰውየው ቀጠለና የየውመል ቅያማ ሰአቷን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ተጠያቂው ከጠያቂው የበለጠ የሚያውቅ አይደለም¹ ” ከዛም ሰውየው ቀጠለና የየውመል ቅያማ ምልክቶቿን ንገረኝ አላቸው። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ ባርያ ጌታዋን ልትወልድ ነው² ፣ በባዶ እግራቸው የሚሄዱ፥ እርቃናቸውን የነበሩ፥ ድሆች የነበሩ የፍየል ጠባቂዎች ህንጻ ለመስራት ሲሽቀዳደሙ ልታይ ነው።” ከዛ ቡሃላ ሰውየው ሄደና ብዙ ቆየን። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “አንተ ዑመር ሆይ!ጠያቂው ማን እንደሆነ ታውቃለህን?” ዑመርም “አላህና መልእክተኛው ያወቁ ናቸው።” በማለት መለሰ። የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም] እንዲህ አሉ “ የመጣው እኮ ጂብሪል ነው፥ ሃይማኖታቹህን ሊያስተምራቹህ መጣቹህ።”  ሙስሊም 

↩↩↩↩↩↩↩↩↩↩
አጭር ማብራርያ 

↩↩↩↩↩↩↩↩↩
0·5 ለኢስላም ፣ ለኢማን እና ለኢህሣን መረጃ 

¹ ተጠያቂው ከጠያቂው በላይ አያውቅም ማለት እኔም አንተም አናውቅም ማለታቸው ነው

ከዚህ ንግግራቸው የቂያማ ቀን መች እንደሆነ ከአላህ ውጪ ማንም እንማያውቅ እንረዳለን 

² ባርያ ጌታዋን መውለዷ በሁለት አይነት መልኩ ሊታይ ይችላል 

1 አንድ ሤት ባርያ  ከአሣዳሪዋ ትወልድና አሣዳሪዋ ሢሞት ልጅ የአባቱን ንብረት ሢወርስ እናቱም የሡ ውርስ (ባርያው) ትሆናለች 

2 ልጅ ወላጆቹን ሢበድል 

ይቀጥላል'

አሠላሙ አለይኩም ወራህመቱላሒ ወበረካቱ

ይቀጥላል