Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መሐመድ አወል ማለት ወላሂ ይሄን ምስኪን ሕዝብ ወደ ሽርክ የሚነዳ አደገኛ! አደገኛ! ግለሰብ ነው።



#መሐመድ_አወል ማለት ወላሂ ይሄን ምስኪን ሕዝብ ወደ ሽርክ የሚነዳ አደገኛ! አደገኛ! ግለሰብ ነው።
የድምፁን ማማር ፣ ቅላፄው ፣ የሚያወራው ያልተረጋገጠ ሲራ አያታልላቹ ። ረሱልን የሚወድ ወደ ሽርክ አይጣራም ። ረሱልን የሚወድ ሱናቸውን ይከተላል ። ያኔ በአላህም ይወደዳል። ይሄ ሰው ግን ቁጥር አንድ የሽርክ ተጣሪ እንደሆነ መንዙማዎቹ ራሳቸው መስካሪዎች ናቸው።
አሕባሾች ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈው እንዲው በዘፋኝነቱ እንዳይመስላቹ በጭራሽ!! ነገር ግን (ሕዝቤን ወደ ሽርክና ቢድዐ የመንዳት) ዕቅዳቸውን ስለሚያሳካላቸው ነው።
እኛ ሙስሊሞች አላህ በቁርአኑ እንደነገረን ረሱልም በሃዲሶቻቸው እንዳስተማሩን «አላህን ከአርሽ በላይ ነው» እንላለን ። ለዚህም አሕባሾች ክዳቿል ይሉናል የሚገርመው ይሄ መንዙማ ባይ በክሕደት በብዙ ኡለማዎች የተፈረደበትን " ከሱ እምነት የነሷራዎችና የአይሁዶች እምነት ይሻላል" ያሉትን «አላህ በሁሉም ቦታ ይገኛል እኔም ላይ ሰፍሯል!»
ብሎ « እኔ አላህ ነኝ» የሚል አዝካር የፈጠረን አደገኛ ሱፊ «ወሕደተል ውጁድ» ፈልሳፊ 'መሐመድ ኢብን አረቢ' ሸይኹል አክበር እያለ ሲያሞግሰው አሕባሾች ግን ይሁን ብለው ይቀበሉታል ። ለምን? በሽርክና በኹራፋት አንድነት ስለተሳሰሩ ነው።

ሕዝቤ ሆይ ንቃ! ቀብር ውስጥ የመጀመሪያ ጥያቄዎችህ የተውሒድ ናቸው ። ዛሬ ላይ በመሐመድ አወል መንዙማ «.. ሸኸና ሁሴን ፣ አብዱል ቃድር ጀይላኒ ፣ ሸኾቹ ፣ አውሊያዎቹ ከጭንቅ አውጡኝ!..» እያልክ የምትወዛወዝ ከሆነ ነገም ቀብር ውስጥ ለናኪርና ሙንከር ጥያቄ ይህንኑ ትመልሳለክ ። የቀብር ቅጣቱ እንዳለ ሆኖ ዘውታሪ ወደ ሆነው የጀሃነም እሳት ትጣላለህ ። አላህ ሌሎችን ወንጀሎች ይምርህ ይሆናል ነገር ግን በሽርክ ድርድር የለም ። ንቃ!
{{ አላህ በርሱ ማጋራትን በፍፁም አይምርም፤ ከዚህ ሌላ ያለውንም (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል። በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኀጢያት በእርግጥ ቀጠፈ። }}
[ ኒሳእ -48 ]

ይሄንን አደገኛ የሽርክ ተጣሪ በ «ኢስላማዊ» ቴሌቪዥን እያስተዋወቃቹ ሕዝቡ አልበሙን ገዝቶ ወደ እሳት እንዲነዳ ምክንያት የምትሆኑ ሰዎች ወላሂ አላህን ፍሩ! እምቢም ካላቹ ነገ አላህ ፊት ምን እንደምትመልሱ መልስ አዘጋጁ።

አንዳንድ የዋሆች ሰው አትማ ይላሉ ። አጂብ የ አብዱላህ ሀረሪ ስም ተነስቶ ሰውን ተጠንቀቁ ሲባል ደስ ይላቸዋል ። ግን የሌላው ሲነሳ ያኮርፋሉ ። ያም ሽርክ ይዞ ነው የመጣው ይሄም ሽርክ ይዞ ነው የመጣው ። ነው ወይንስ ይሄም ስሙን ማንሳት በናንተ ቤት ሃላል እንዲሆን የመጅሊስ ሹመኛ መሆን አለበት ? የዋሆች አት ሁኑ ። እኔ ስም እያነሳው የማስጠነቅቃቹ ሸሪዐው ስለሚፈቅድልኝ ነው። ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ስም አንስተው ሕዝቡን አስጠንቅቀዋል ሶሃቦችም ስም አንስተው አስጠንቀቋል በበጎ የተከተሏቸው ሰለፎችም እንዲሁ ። ታዲያ ይሄ ሰው ሽርኩን በ አልበም ሲረጭ እኔ ዝም እንድል ነው የምተጠይቁኝ ? ይሄ አላህ ፊት ያስጠይቀኛልም ። የምትወደው ሰው ስለተነካ ከሆነ ። ይሀው በማስረጃ የሽርክ ስንኞቹን ፅፌልሃለውና ውዴታው ይውጣልህ ።

እንዲህ እያለ ነው ከአላህ ውጭ ያለን ‹‹እርዱን፤ሸሸንባችሁ፤ ዱስቱር ብለናል፤ የሩቁን አዋቂ...›› የሚላቸው

1) በዘመን ያላችሁ ሳዳቶች አህያር
ቀኝ እጄን ጨብጡኝ ወድቄ እንዳልቀር
ሺሊላህ ጌቶቼ አርሂቡ ዱስቱር
መቼም ያለናንተ ሁሉም አያምር
በናንተ የሸሸ ምንም አያፍር
ጌቶቼ አትለፉኝ አዳቤም ባያምር
አደበቢስ ቡልሀ እንደኔ ቢኖር
ባሪያ ሲባል ማጥፋት እለት ነው እድር
ለናንተ ይገባል ያጠፋል መማር፡፡
2) በዘመን ያላችሁ ሳዳቶች አኽያር
ቀኝ እጄን ጨብጡኝ ወድቄ እንዳልቀር
ሺሊላህ ጌቶቼ አርሂቡ ዱስቱር
መቼም ያለናንተ ሁለም አያምር
በናንተ የሸሸ ምንም አያፍር
ጌቶቼ አትለፉኝ አዳቤም ባያምር
አደበቢስ ቡልሀ እንደኔ ቢኖር
ባሪያ ሲባሌ ማጥፋት እለት ነው እድር
ለናንተ ይገባል ያጠፋን መማር፡፡
3. አልሀምዱሊላሂ ይመስገን ገፋር
ቀልቤን ያዞረልኝ ወደናንተ በር
በናንተ የሸሸ ያገኛል ሹም ሽር
ሊለግስ ነው መሰሌ ዳመናው ዟዟረ
የስልካችሁ ንባብ ይሰማ ጀመረ፡፡
4. ሁለም ባንድ ሆነው ከሙስጠፋ ጋር
ዛሬ ይድረሱልን ላገኘን ችጋር
5. አንተል ቁረይሺዩ አንተ ነብዩና
ቢሲሪ ሲሪከ ዘይን ባጢነና

6)ሰለፍም ኸለፍም ማወረአል ባህር
በሁለም ሸሸሁኝ አንድ እንኳን ሳይቀር
ከዛፍ ከቅጠሉ በዝቶብኝል ነውር
እሜዳው ላይ ሆኜ ወድቄ በዱር
መግቢያ በር አጥቼ ታግቼ ባጥር
አልሄድ ወደፊት ወደኋላ አልበር
በቀኝ በግራዬ እሳት ገደል ባህር
አቤት ጠራኋችሁ ጌቶቼ ዱስቱር፡፡
ረዳቴ ማንነው ከናንተ በቀር
7. የአበራ ሙዝ አባት የማይደፈር
አቤት ይታይልኝ ምነው የኔም ዱር
ዘሩልኝ ጌቶቼ በአውን በነስር
ከጃችሁ ከጅዬ ቆሜያለሁ ከበር፡፡
በናንተ የሸሸ ምን ጊዜም አያፍር
ሀጃዬን አውጡልኝ በዟሂር በሲር

8)መጀን በኑር ሁሴን በአሩሲው ኑር
የአውሉያዎቹ ሻምበል የበርም የባህር
ከራማው ይፋ ነው አይደለም መስቱር
እጣው እንደ ነቢይ በርዳዳው ገበር፡፡
የሪጀልች አባት የነዚያ ያብራር
የነአህመድ ኑረላህ ዚልፈይዲል ሚድራር
ተብል አላህ ዘንዳ በሻሀው አብሽር
ጌታዬ ኑር ሁሴን በለኝ እንጂ አጀብ
በለኝ የኔ አሽከር
በዱንያ በአኸይራም እንዳልቸገር
በናንተ የሸሸ እንዲሁም አይቀር
አላህ ሰጥቷቸኋል ሳይሰፍር ሳይቆጥር፡፡
9. ጌታችን ቃዲር እኩሉንም አለው
አብሽር አጋፍር
አልብስም አጉርስም አመኩስ አክብር
ኢንስም ጂን ቢሆን በጫማህ ይደር
ይፍራህም ይወቅህ አውሪ እንኳ በዱር
አውቆና ለጥቆ ሰልቶ ባንተ አምር
ለሀልቁ ገበያ መድሀኒት ነበር፡፡
የቸገረው ሄዶ የለውም ማፈር
ከሀያቱ በልጧል ውለታው በቀብር
ወዲያልኝ የሱ ጉድ አያልቅም ይቅር
10. የሀድራ ጦያራ ይዞ የሚበር
ሲጠሩት ፈጣን ነው ቶል የሚሀድር
ተምኪን የተሰጠው ዞሂር ወባጢን
እኔ ያለሁበት እክጀላ በር
ቀድሬም አያደርሰኝ መቃም ለመቁጠር
ስንቱን አሳደገው ገና በነዝር
ፈይዱ ከአፍ ሲፈልቅ የአጀብ ነበር
እንኳን ሰው መላኢካ ያዳምጠው ነበር፡፡
11. ጌታው ሰይድ አህመድ የደባቱ ኑር
ዶላል ያስፈቀተው የዲኑ ጨረር
ስፍር ቁጥር የለው ስንቱ በእጁ ሻረ
አላህ ዘንድ ነበር ተናግሮ የማያፍር
ቢያለብስም ቢገፋም ቢያደኸይ ቢያከብር
ይግባኝ የለበትም በፈረደው አምር
ተብሎ አላህ ዘንዳ በሻሀው አብሽር
12. ጌታው ሸረፈዲን የደግየው ኑር
አላህ ትላቅ እጣ አድሎት ነበር
ሰውም ጂንም ቢሆን አውሬውም የዱር
ሁለም አቤት ብሎ ተገዝቶ ነበር
ጥላው የሚበቃው በሁለት አገር
በሱ ይወሰላል እስላምም ካፊር
ሴትም ወንድ ቢሆን
አብድ ቢሆንም ሁር
በሱ ተወስል የለውም ችጋር
13. ይመነጥቁታሌ ያወጡታሌ ከጭንቅ
14. እኝህን ሳዳቶች ድረሱ አንበላቸው
እሱ ወደደና እሱ መረጣቸው
አመሀባው ባህር ሺህ አመት አስዋኛቸው፡፡
እሱ ወደዳቸው በፊት ሳይሰራቸው
ዩሂቡሁም ወዩሂቡነሁ አላቸው ጀባሩ፡፡
አቤት እርዱኝ ይላል የቤት ልጅ አሽከሩ
በናንተ የሸሸ የቂን ነው ማማሩ
ጥላቸው ጠባቂ በሁለት አገር
15. ደግሞ ጌታ ሰይድ የማይባሩ ኑሩ
ረህመት አድርጎ አላህ አዝልቆት ነበረ
ለኸልቁ ነበረ በልግና መህር
ሰውም ጂንም መላኢካም ተገዝቶ ነበር
16. አልዩ ሀይደር ነበረ
ለነቢ ማኖሪያ ሚስጥር
ኢልመልገይብ ከሱ ይጠየቅ ነበር፡፡
17. ሙሀመዱ ሰማን ገፍታሪው ቀደር
18. ሸህ ሙሳ ሰገራት ውስጡ ላዩ ኑር
የከሽፋን መነጥር ታድል ነበር፡፡
19. ሸህ ሙሀመድ ሸሪፍ የርጎየው ገበር
ሲሞድህ ሙስጠፋን እያየ ነበር፡፡
20. ሰይድ ቡሽራ ገታ ቀምጣላው ገበር
ከልካይ የለበትም ሲዘልቅኝ እልፍኝ በር
ጨወታው ነበር ቀዷ ቀደር ጋር
ከሙስጠፋ ጋራ የሚነጋር
ማሂሩ ወጌሻ ለዟሂር ለሲር
ስንቱ በሽተኛ ዛቱን አይቶ ሻረ
ሰውም ጂንም ለሱ ታጠቀ ገበረ
ከራማ በበጠልሻ ነዳፊ ነበረ
ሙቶም በሀያቱ ጠቃሚ ገበር፡፡
21. መጂት ሀጅ ቡሽራ የራቀው ገበር
አገላባጭ ነበር የቀዷ ደብተር
ለውሀል መህፉዝ አይቶ ነበር ሲናገር፡፡
22. እነሀጅ አረቦ የሳልመኔው ኑር
ሀለዋውን ያደረገው ከነብዩ ጋር
23. ሸህ መሀመድ ፈቂህ ባለመነጽር
የታደለው ገበር ከአላህ ዘንዳ ሲር
24. ለካ ገረዋ ላይ አብርቷል
ጀምበር ሲፈቱ መለኪያ ዛቱ በበሽር
ተብሎ አላህ ዘንዳ በሽር ወአንዙር
ጎራ የማይጋርደው ይዟል መነጸር
ይናገር ነበረ የዟሂር የሲር
ይገልጠው ነበረ የኸልቁን ሀጢር
25. እንደሁሴን ጂብሪል ደግሞ ማን ነበረ
የከሽፉን መነጸር አይኑ ላይ ነበር
የፊቱን የኋላን ይናገር ነበር
ሁለም ተገላሌጦ ይታየው ነበር፡፡
26. እነሸህ ሀቢቡ ጉደኛው ገበር
ከአርሽ እስከ ሰራ ይታየው ነበር
አላህ እድርጎት ነበር የሚስጥር ሰፈር
27. ቁንዲ ሸህ አብደላ ወልዩ ገበር
ከአላህ ጋር የፈጀው ሚስጥሩን በሲር
ይናገረው ነበር አሟቱ በቀብር

28) የቃጥባሪው ጌታ ኢሳ የአላህ ኑር
ከሚን ኢንደላሂ የተባለ አብሽር
29. ለገሂዳም ጃማ ስንቱ ጉድ ነበር
እነ ነብዩ ሀድራ የተባሉ አብሽር
ባልከው ይሁን ያለው ገና ሲፈጠር
30. ጌታው አባ ረህማ የአውሉያ መምህር
ጨዋታው ነበረ ሰይድ ከድር ጋር
ሁለም ከሀድራው ይቀስም ነበር፡፡

አዲስ አበባ የሚገኘው መስጊድ ኑር ውስጥ ሰዎችን ስለሀጅ ለማነቃቃት መንዙማ ልበል ብሎ
ተነስቶ ያለውን አንብቡ
መካና መዲና[1]
በእሳትና በውሃ ቢታጠርም
እርሶ (ነብያችንን) ይጥሩን እንጂ አንቀርም፡፡

[1] በዛ አመት የሀጅ ማድረጊያ ገንዘብ 36000 ብር ደርሷል ስለተባለ፤ ይህ ሰው እንዲህ ብሎ ጀመረ አደለም በብር በእሳትና በውሃ ቢታጠርም፡፡ የአላህ ባርያዎች ሆይ! ለበይክ የሚባለው ለፈጣሪ አላህ ነው ወይንስ ለፍጡር ነብዩ (ሰለላሁ አለይ ወሰለም) ስለዚህ ሙሀመድ አወል ይህ ነው፡፡ አላህ የ18 ነብያትን ገድል ከተናገረ በኋላ ቢያጋሩ ኖሮ ስራቸው ውድቅ ይሆናል ይላል፤ የአደም ልጆችን ምርጥ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ብታጋራ ኖሮ ስራህ ውድቅ ይሆናል ከከሳሪዎችም ትሆናለህ ይላቸዋል፡፡

ተረተረቶች
31) ኢስማኤል ጀበርቴ ጉድ ያለው ነበር
ከራማው እንደ ባህር የሞላው ገበር
ሰውንም ጂንም ጨልጦ የሚያስቀር
እሱነው ይባላል የቃማቴ ሲር [1]

[1] ምስጋና
ለአላህ ይገባው ሱፍዮች ጫትን ነብያችን አመጡልን ባለማለታቸው፡፡ ጫትን ያመጣው ኢስማኢል ጀበርቲ ነው ብለው ያምናሉ፤ ለዚህም
ሲባል እሱ ነው ይባላል ‹‹የቃማቴ ሲር›› የቃሚዎችን ሚስጥር ያዥ ብለው ይገምታሉ ይሞግታሉ

32) የጌታው ስጦታ ስፍር የለው ቁጥር ለሸህ አሊ ጎንደር አድርጎት ነበር ባመነጠር አጀብ
ለበረካው ያህል ጥቂት ላናገር
አንዲት ላም ኮሬብ ላይ ስትበላ ሳር
እላይዋ ላይ ወጥታ በናትዎ ቀብር
ጎንደር ሆነው አዩዋት የሚያጅብ ነገር
ተዛ ተቆጡና ሸህ አሊ ጎንደር

የሰው ልጆች ምርጥ ለሆኑት (አለይሂ አፍደሉ ሰለዋት) አላህ እንዲህ ብሎ ያዛቿል

“ስግደቴም ማረዴም ህይወቴም ሞቴም ለአለማት ጌታ አላህ
ነው በል ለርሱ ተጋሪ የለውም በዚህም (በማጥራት) ታዘዝኩ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ (በል)አልአንአም 162-163 ታዲያ እሳቸው ለአላህ እንዲህ ከነበሩ እኛ የሳቸውን ፈለግ እንጂ ሌላ ሊኖረን አይገባም፡፡
ሙሃመድ አወል ታድያ ይህን ሁሉ ሽርክ ለኡመት ሙሀመድ በኢስላም ስም አቅርቦ እንዴት ዝም ይባል???

አረ አላህን እንፍራ ለባጢል (ለኩፍር እና ሽርክ) ከለላ የሚሰጡ ብሎም የዚህን ሰው ጥመት በቻናል ለሚያሰራጩ እና እሱን ለሙስሊሞች እንደጥሩ ሰው ለሚያስተዋውቁ አላህን ፍሩ አላህን ፍሩ አለበለዚያ አላህ አያያዙ የበረታ ነው በውርደት ላይ ውርደት ያከናንባል፡፡
አላህ ሆይ! ከአጥማሚዎች እኛንም ዝርያዎቻችንንም ጠብቀን፡፡