Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በአላህ እጠበቃለሁ!! እህቴ ሆይ! አንተም ወንድሜ!

'‎በአላህ እጠበቃለሁ!!

እህቴ ሆይ! 
የሰው ሰይጣኖች ከስክሪን በስተጀርባ እንዳሰፈሰፉ መሽቶ ይነጋል። የሚያሳዝነው ሂጃብሽ ትርጉም እንዲያጣ በሚያደርግ መልኩ ወሬ ለጀጀመረ ሁሉ በርሽ ክፍት ነው!

አንተም ወንድሜ!
ገና እውነተኛ ማንነቷ በውል ላልተረጋገጠች ሴት የቻት ወሬ ውሃ ውስጥ እንደገባ ጨው ትሟሟለህ። ሀራምን የመራቅ የብቃትህ ሃይልና ሰብርህ ሁሉ ይመክናል!

እናስተውል...
ዩሱፍ አለይሂሰላም እንደፈለጉ ቢያዙትም አቤት ሊል በሚገባው የንጉስ ቤት ነዋሪ ነበር። በክፍሉ ውስጥ ብቻውን እያለ እጅግ በጣም ተውባና ተቆንጅታ የንጉሱ ሚስት ዘው አለችበት። በር ብቻ ሳይሆን በሮቹን ሁሉ ቆላለፈቻቸው። ለእርሱ ስትል ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀችም አበሰረችው። 

አላህ ቁርአን ላይ እንደገፀልን፦ 

{وَرَاوَدَتْهُ الَّتِي هُوَ فِي بَيْتِهَا عَن نَّفْسِهِ وَغَلَّقَتِ الْأَبْوَابَ وَقَالَتْ هَيْتَ لَكَ ۚ قَالَ مَعَاذَ اللَّهِ ۖ إِنَّهُ رَبِّي أَحْسَنَ مَثْوَايَ ۖ إِنَّهُ لَا يُفْلِحُ الظَّالِمُونَ} [يوسف : 23]

« ያቺም እርሱ በቤትዋ የነበረባት ሴት፣ ከነፍሱ አባበለችው፤ ደጃፎችንም ዘጋች፤ ላንተ ተዘጋጅቼልሀለሁና ቶሎ ና አለች፤ "በአላህ እጠበቃለሁ" እርሱ (አሳዳሪዬ የገዛኝ) ጌታዬ ኑሮዬንም ያሳመረልኝ ነውና (አልከዳውም)፤ እነሆ! በደለኞች አይድኑም፤ አላት።» 

ምንም ስሜትን ከጫፍ የሚያደርሱ ነገሮች ቢመቻቹለትም ራሱን አቅቦ ይህን አጭር ምላሽ ሰጣት:-

"قال معاذ الله"
 «በአላህ እጠበቃለሁ አላት»  (ምእራፍ ዩሱፍ 23)

ይህ አይነቱ ጥሪ ዛሬ በቻት መስኮቶች ይደጋገማል፤  ነገር ግን የነብዩ ዩሱፍን ምላሽ ማን ይስጥ!?? 
«በአላህ እጠበቃለሁ!» ማን ይበል??

አላህ ሆይ ከጥፋት ሁሉ ጠብቀን!!

---------////--------
www.facebook.com/tenbihat‎'
በአላህ እጠበቃለሁ!!

www.facebook.com/tenbihat