Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኡሡሉ ሠላሳ ክፍል 20

A user's photo.

አሠላሙ አለይኩም
ኡሡሉ ሠላሳ ክፍል 20
የኪታቡ ፀሀፊ እንዲህ አሉ
ሦስተኛው ¹ መሠረት ፦ ነብያችን ሙሀመድን ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ማወቅ እሡ ፦ ሙሀመድ ኢብን አብደላህ ቢን አብድል ሙጠሊብ ባን ሀሺም ሀሺም ከቁረይሽ ጎሣ ነው ቁረይሾች ደግሞ ከአረቦች ናቸው አረቦች ደግሞ የእስማኤል ኢብኑ ኢብራሒም አልሀሊል ዝርያ ናቸው (የአላህ ሠላትና ሠላም በሦስቱም ላይ ይሁን)
እድሜያቸው ስልሣ ሶስት ነው ከዛ ውስጥ አርባው ከነብይነት በፊት ሲሆን ሀያ ሶስቱ ደግሞ ከነብይነት ቡሀላ ነው
ነብይ የተደረጉት ﺍﻗْﺮَﺃْ ሲሆን ሩሱል የተደረጉት ﺑﺎﻟﻤﺪﺛﺮ ነው²
የትውልድ ሀገራቸው መካ ነው ወደ መዲና ተሠደዱ ሠውችን ከሽርክ ያስጠነቅቁ ወደ ተውሒድ ይጣሩ ዘንዳ አላህ ላካቸው
መረጃ አላህ እንዲህ ይላል "አንተ ተከናናቢ ሆይ ๏ ተነስ አስጠንቅቅ ๏ ጌታህንም አልቅ๏ ልብስህንም አፅዳ๏ ጣኦትንም እራቅ ๏ ማብዛትን ፈልገህ አትመፅውት በጌታህም ታገስ "
ትርጉሙ(( ﻗُﻢْ ﻓَﺄَﻧْﺬِﺭ)ْ ከሽርክ ያስጠነቅቃሉ ወደ ተውሒድ ይጣራሉ ( ﻭَﺭَﺑَّﻚَ ﻓَﻜَﺒِّﺮْ ) ማለት በተውሒድ አልቀው ( ﻭَﺛِﻴَﺎﺑَﻚَ ﻓَﻄَﻬِّﺮ ) ማለት ስራህን ከሽርክ አፅዳ ( ﻭَﺍﻟﺮُّﺟْﺰَ ﻓَﺎﻫْﺠُﺮْ))
( َﺍﻟﺮُّﺟْﺰ) ጣኦት ነው) ((ﻓَﺎﻫْﺠُﺮْ) መራቅ
(ከሽርኳ እና ከሽርኳ ባልተቤት
---------------------------------
አጭር ማብራሪያ
-------------
¹ ሁለቱ የሠው ልጆች ጠንቅቀው ሊያውቋቸው የሚገቡ እንዲሁም ግዴታ የሚሆኑ ነገራቶችን አሣልፈናል ሦስተኛው ደግሞ የአላህ መልዕክተኛን ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ማወቅ ነው እሣቸውን ማወቅ ማለት
① የዘር ግንዳቸውን በሚገባ ማወቅ
② እድሜያቸውን የተወለዱበትን ቦታ የተሠደዱበትን ቦታ
③ ከነብይነት ቡሀላ የነበራቸውን ታሪክ ማወቅ
④ ለምን እንደተላኩ ጠንቅቆ ማወቅ
² ነብይ እና ረሡል ይለያያሉ አይለያዩም በሚለው ላይ ኡለሞች የተለያየ አመለካከት ቢሠነዝሩም ከመረጃዎች የተሻለ የሚመስለው ግን ነብይ ማለት "ለሠዎች ለማድረስ ያልታዘዘ ሩሡል ደግሞ በማድረስ የታዘዘ "ነው አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው
ይቀጥላል