Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የ لا إله إلا الله ተቃራኒ (ሽርክ)

እምነትህን ጠብቅ
📔 የ لا إله إلا الله ተቃራኒ (ሽርክ)
ተውሂድ አምልኮን በሙሉ ለአላህ ብቻ ማድረግ ሲሆን ሽርክ ደግሞ ከአምልኮ አይነቶች አንዱን እንኳ ቢሆን ከአላህ ውጭ ማድረግ በመሆኑ “لا إله إلا الله” የሚለውን ቃል ያፈርሣል፡፡
ሽርክ ሰዎች የተፈጠሩለትን ቁም ነገርንና ነቢያትም የተነሱለትን አላማ በቀጥታ የሚፃረር በመሆኑ አላህ ፈፅሞ የማይምረው ወንጀል ሆኗል፡፡
አላህ እንዲህ ብሏል፡-
«አላህ በእሱ የማጋራትን (ወንጀል) አይምርም፡ ከዚህም ወዲያ ያለውን ለሚሻው ሰው ይምራል በአላህም የሚያጋራ ሰው (ከእውነት) የራቀን መሣሣት በርግጥ ተሣሣተ»
📚 [አል ኒሣእ 116]
የሽርክ አይነቶች
የሽርክ አይነቶች ሁለት ናቸው፡፡
1ኛ- ትልቁ ሽርክ:-
ከኢባዳ አይነቶች አንዱን እንኳ ቢሆን ከአላህ ሌላ ለሆነ አካል መፈፀም ሲሆን ይህ ተግባር ከእስልምና ያስወጣል ስራንም ባጠቃላይ ያበላሻል፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-
«ብታጋራ ሥራህ በእርግጥ ይታበሳል በእርግጥም ከከሃዲዎቹ ትሆናለህ»
📚[አል-ዙመር 65]
«ባጋሩም ኖሮ ይሠሩት የነበሩት ከነሱ በታበሰ ነበር»
📚[አል-አንአም 88]
2ኛ- ትንሹ ሽርክ:-
ለአላህ በሚደረግ ኢባዳ ላይ በከፊል ወደ ፍጡር መዘንበል ማለት ነው።
ለምሣሌ
ኢባዳን ሲፈፅም ሰዎች እንዲያዩለትና እንዲያውቁለት መፈለግ፡፡
ይህ ሽርክ ሰሪው በእድሜው የሰራውን ሁሉ ሣይሆን እንዲህ እይነቱ ሽርክ የተቀላቀለበት ስራ ብቻ ይታበስበታል፡፡ በዚህ ሽርክ እስልምናው ቢጓደልም ነገር ግን ከእስልምና ሙሉ በሙሉ አይወጣም፡፡
🔜ኢን ሻአ ላህ ይቀጥላል…
🔚ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!

Post a Comment

0 Comments