Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የወንድማማችነት‬ ሐቅ

#‎የወንድማማችነት‬ ሐቅ
ከሸይኽ ሷሊህ አልሸይኽ
#⃣የወንድማማችነት ሐቅ#⃣
1⃣ ለዱንያ ጥቅም ሳይሆን ለአላህ ብሎ ወንድሙን ሊወድ
2⃣ለወንድሙ በገንዘብም በነፍስም እገዛ ሊያደርግ
3⃣ ክብሩን መጠበቅ ይህን ክብርም ለመጠበቅ
▶ ነውሮቹን ከማውራት መቆጠብ
▶በጥያቄ ከማፋጠጥ መታቀብ
▶ሚስጥሮቹን መጠበቅ
4⃣ ወንድምህን በርሱ ላይ መጥፎ ጥርጣሬን ከመጠርጠር መጠበቅ
5⃣ ከወንድሞችህ ጋር ንትርክና ክርክርን መተው
⏩ ለክርክር ምክኒያት ከሚሆኑትም
▶ለአስተያየቱ ቦታ አለመስጠትን ማሳየት
▶የአሸናፊነት ፍላጎት
▶ ምላስን ከመጥፎ ንግግር አለመጠበቅ
6⃣ለወንድምህ ምላሳዊ ችሮታን አለመንፈግ
⏩ የምላሳዊ ችሮታ ገፅታዎቹ
▶ላደረገልህ ነገር በምላስህ ከማመስገን አትሰስት
▶ በሌለበት ቦታ ላይ በመልካም ልታነሳውና ልታመሰግነው
7⃣ስህተተቶቹን ይቅር ማለት
8⃣ አላህ ልቅናው ከፍ ያለው ጌታ በቸረው ገንዘብ:እውቀት:ዲን:ቀጥ ማለትና መስተካከል ልትደሰት
9⃣ ባንተና በወንድሞችህ መካከል በበጎ ላይና ነገሮችን በማስተካከልና በማበጀት ላይ ትብብር መኖር
በተለይ በወንድማዊ ጓደኛማቾች መካከል መወያየት አንድ መሆንና መለማመድ መኖር
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ሼኹ ወንድም በወንድሙ ላይ ያለው ብለው በሙሀደራ ላይ የጠቀሷቸው ናቸው።
(የተኮረጀ)
ከሸይኽ ሷሊህ አልሸይኽ
ኡስታዝ ጀማል ያሲን ካወረደው አረብኛ ፅሁፍ የተወሰደ

Post a Comment

0 Comments