Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የቫለንታይንስ ቀንን በተመለከተ የኡለማዎች ፈትዋ‬!

by Haider Khedir
‪#‎የቫለንታይንስ_ቀንን_በተመለከተ_የኡለማዎች_ፈትዋ‬!
ብዙዎቻችችን እንደምናውቀው (በፈረንጆቹ የጊዜ ቀመር 2ኛው ወር) february የፍቅር ወር በመባል መከበር ከጀመረ ረጅም ጊዜያትን አስቆጥሯል::ይህም የቅዱስ ቫለንታይን ቀን በመባል ይታወቃል:: ዛሬ ላይም የምናየው (የበዓሉ ስርአት) የጥንት ሮማኖችን እና የክርስትያኖችን ባህል ቅሪት ይዞ እናገኛለን::በመሆኑም ከተለያዩ ምክንያቶች አንጻር ለሙስሊሞች ማክበር ክልክል ይሆናል።
1 በመጀመሪያ ይህ በሸሪዓ ምንም ዓይነት መሰረት የሌለው የፈጠራ ተግባር ነው:: በሸሪዓ መሰረት የሌለውን ተግባር መፈጸም ደግሞ የተወገዘ ክልክል ነው:: በመሆኑም ይህ ጉዳይ እናታችን አዒሻ ካስተላለፈችው ሀዲስ ውስጥ ይካተታል የአላህ መልዕክተኛ (صلى الله عليه وسلم) ተከታዩን ተናግረዋል
‹‹በዚህ በዲናችን ላይ ከርሱ ያልሆንን ያመጣ (ሰው) ስራው ተመላሽ ነው፡፡ (ተቀባይነት አይኖረውም)›› (ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል)
ውድቅ ተግባር በመሆኑ ወደ ሰሪው አካል ተመላሽ ይሆናል።
2 ይህ በዓል መሰረቱ ሙስሊም ካልሆኑ አካላት ነው። ስለዚህም በዚህ ተግባር መሳተፍ ለነርሱ እውቅና መስጠት በጉዳያቸው ላይ አድናቂ መሆን እንዲሁም በሚያደርጉት ተገባርም ላይ መተባበር እና ከነርሱ ጋር መመሳሰል ማለት ነው። ይህን ተገባር መፈጸም ደግሞ የመልዕክተኛው (صلى الله عليه وسلم) ትዕዛዝ ለመዳፈር ወደዛቱበት ቀይ መስመር ውስጥ ለመግባት ይዳረጋል ከከሃዲያን ጋር መመሳሰልን እንዲህ ሲሉ አስጠንቅቀዋል
‹‹ከህዝቦች የተመሳሰለ እረሱ ከነርሱ ነው፡፡›› (አቡ ዳውድ ዘግበውታል)
3 በዚህ በዓል ላይ የተለያዩ ሸሪዓ የከለከላቸው ተግባራት ተፈጻሚ ይሆናሉ ከብዙ በጥቂቱ ፓርቲዎች ይዘጋጃሉ ፣ ሙዚቃዎች ፣ የተለያዩ የብልግና ተግባራት ፣ ስርአት አጥነት እንዲሁም ልቅ የሆነ የወንዶችና የሴቶች መቀላቀል በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው። እነዚህ ተግባራት ደግሞ ሸሪዓ አምርሮ የሚቃወማቸው መጥፎ ተግባራት ናቸው። በመሆኑም ስለ ራሱ የሚጨነቅ ማንኛውም ሰው ከነዚህ ስርአት አጥነት ከሚስተዋልባቸው ዋልጌነት ከተንሰራፋባቸው መጥፎ ተግባራት ራሱን ሊቆጥብ ይገባል።
4 ይህ ተግባር የሰዎችን አዕምሮና ልብ በውሸት ነገሮች ቢዚ እንዲሆን የሚያደርግ እንዲሁም ከነዛ ምርጥ እና ጻድቅ የነበረሩ አርአያ ትውልዶችን ፋናን የሚጻረር በመሆኑ ዛሬም ላይ ቢሆን ከዚህ በዓል ጋር ተያያዢነት ያላቸውን ልማዳዊ ተግባር መፈጸም ክልክል ይሆናል::ማለትም ምግቦች፣ መጠጦች ፣ ልብሶች እንዲሁም የስጦታ ልውውጦችን እና መሰል ተገባራትን ያጠቃልላል። ሙስሊሞች በሀይማኖታችን ልንኮራ ይገባል። ደካማዎችና የጮሃን ሁሉ ተከታይ መሆን የለብንም።
ማሳሰቢያ
በዚህ በዓልም ይሁን በ ሌሎች ክልክል በሆኑ በዓላት ላይ በማንኛውም መንገድ እነርሱን መተባበር ለሙስሊሞች የተከለከለ ነው። ምግብ ና መጠጥ የስጦታ እቃዎች በመግዛት ፣በመሸጥ ፣በማዘጋጀት ፣ በማከፋፈል ፣ በማስተዋወቅ እንዲሁም በሌሎች ማንኛውም መንገዶች መርዳት ክልክል ነው። ምክንያቱም እንዚህ ሁሉ በመጥፎ ተግባራት አንዱ ለሌላው ደጋፊ እንደሆኑ ይቆጠራሉና ነው። የአላህና የመልዕክተኛውን ህግ ለመጣስና ለመተላለፍ ተባባሪ መሆን አይገባ አላህ እንዲህ ይላል
በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡(5:2)
በመሆኑ ራሳችንንም ሆነ ቤተሰቦቻችንን ከዚህና መሰል በሸሪዓ መሰረት ከሌላቸው ተግባራት በመቆጠብ የራሳችንንም ክብር እንዲሁም በዚህ ምድር ላይ ስንኖር ያለንን ብቸኛ አንጡራ ሀብታችን የሆነውን ዲናችንን ከብክለት ልንጠብቅ ይገባል። የመዕልክተኛውን ሱናህ አጥብቀን በመከተል የከሃዲያንን መንገድ ልንርቅ ይገባናል፡፡
ሙስሊሞችን በጠቅላላ ከውጫዊም ሆነ ውስጣዊ ከሆኑ መጥፎ ተግባራት እንዲጠብቀንና በእምታችን ላይ ጽናት እና ብርታት እንዲሰጠን አላህን እማጸነዋለው። አላህ የተሻለ ያውቃል።
ማስታወሻ :ይህን ጽሁፍ ያዘጋጀሁት የተለያዩ ዑለማዎች ስለዚህ በዓል ተጠይቀው የሰጡትን ፈትዋ መሰረት አድርጌ ሲሆን ። የመልእክት መደጋገም እንዳይኖርና ለንባብ አሰልቺ እንዳይሆን ፍሬ ነጥቦችን አሳጥሬ ለማውጣት ሞክርያለው። ባለማወቅም ይሁን በመዘንጋት የተሳሳቱ ሙስሊም ወንድምና እህቶችን ማረሚያና መገሰጫ እንዲሆን ጌታዬን በመልካም ስሞቹና በሙሉባህሪዎቹ እማጸነዋለው።