Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ወንጀልን ለማቆም የሚረዱ መንገዶች ምን ምን ናቸው?

ከወንጀል ለመገላገል
ጥያቄ፦ ወንጀልን ለማቆም የሚረዱ መንገዶች ምን ምን ናቸው?
መልስ፦ ብዙ ነው ...
በቅድሚያ፦ ያለድንበር ማለፍ ትክክለኛ ንሰሀ ማድረግ፤ ይህን ያልኩት አንዳንድ ሰዎች ብርቱ ከሆነ ስለት ጋር ንሰሀ እንደሚያደርጉ ስለደረሰኝና ስላረጋገጥኩም ነው። ለምሳሌ ሰውየው ሲጃራ ከማጨስ ይቶብታል ከተመለስኩ ግን ይህን ይህን ከሶደቃ ከመሳሰሉት አደርጋለሁ(ይላል)። ይህ ክልክል ነው፤ ይህ ድንበር ማለፍ ነው፤ ይህ ቢድዓ ነው። ይህ ተውባ በቢድዓ የተለወሰ ነው። (የሚያስፈልገው) ትክክለኛ ተውባ ብቻ ነው።

2. ትርፍ የአምልኮ ስራዎችን ማብዛት፦ ለምሳሌ የአዱሀ ሁለት ረከዓ፣ ከዙሁር በፊት አራት ወይም ሁለት ረከዓ(ቀብሊያ)፣ ከዙሁር በኋላ አራት ወይም ሁለት ረከዓ፣ ከዓስር በፊት አራት ወይም ሁለት ረከዓ፣ ከሁሉም አዛን በኋላ ሁለት ረከዓ፣ ከመግሪብ በኋላ ሁለት ረከዓ፣ ከዒሻ በኋላ ሁለት ረከዓ፣ በለሊት የቀለለውን ያህል ከዊትር ጋር፣ ትርፍ ፆሞች ሶስቱን የአያመል-ቢድ ቀናት ይመስል፣ ሰኞና ሐሙስ፣ የሸዋል ስድስቶ፣ ከዚህም ሌላ በትክክል ከሱና የተገኘውን መፆም!
3. ከመጥፎ አቀማማጮች መራቅ፦ ነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ "አንድ ሰው በወዳጁ ዲን ላይ ነው፤ (ስለዚህ) ማንን እንደሚወዳጅ ያስተውል"
4. አላህን ማውሳት ማብዛት፦ ወደርሱ መጠጋት በወንጀል ላይ ባትወድቅ እንኳ፣ ከወንጀል አላህ እንዲጠብቅህ መለመን፣ አላህ ደጋግ ባሪያዎቹን በተወዳጀበት እንዲወዳጅህ መለመን።
5. ደጋግ የአላህ ባሪያዎችን(ሷሊሆችን) መጎዳኘት፣ ካመቸ ከነርሱ መቀላቀል በመስጂድ በስልክ በመገናኘትም ቢሆን፤ ስለሁኔተው ትጠይቀዋለህ፣ ስለሁኔታህ ይጠይቅሀል፣ ካንተ የተደበቀን ነገር ይጠቁምሀል ወይ ትጠቁመዋለህ።
ይህ ሁሉ በአላህ ፈቃድ ከወንጀል ለመጠበቅና ፀንቶ ለመቀጠል ያግዝሀል።
ዕውቁ ዓሊም ዑበይድ አል-ጃቢሪ(አላህ ይጠብቃቸው)
በዓረብኛ ፖስት ከተደረገ ፅሁፍ የተተረጎመ

سؤال: ما هي الأسباب المعينة لترك المعاصي؟
الجواب:
كثيرة ..
1⃣أولًا: التوبة النصوح بدون اعتداء؛ قُلت هذا لأنَّه بلغني وثبتَ عندي أيضًا أنَّ بعض الناس يتوبُ مع النذر الشديد،
فمثلًا يتوب عن شرب الدخان وإن عادَ يفعل كذا وكذا من صدقات من كذا، فهذا حرام، هذا اعتداء، هذا بدعة، هذي توبة مخلوطة بالبدعة؛ توبة نصوح فقط.

2⃣الثاني: الاستكثار من نوافل العبادات، مثل: ركعتَيْ الضحى، وأربع قبل الظهر أو ركعتين، وأربع بعدها أو ركعتين، وأربع قبل العصر أو ركعتين، وركعتين بعد كُلِّ أذان، وركعتين بعد المغرب، وركعتين بعد العشاء، وما تيسَّر من الليل مع الوتر، ونوافل الصيام،كصيام البيض الثلاث، والاثنين والخميس، وست من شوال، وغير ذلك مِمَّا صَحَّت به السُّنة .
3⃣الثالث: البُعد عن جُلساء السوء، قال – صَلَّى الله عليهِ وسلَّم -: ((الْمَرْءُ عَلَى دِينِ خَلِيلِهِ فَلْيَنْظُرْ أَحَدُكُمْ مَنْ يُخَالِلْ)).
4⃣الرابع: الاستكثار من ذكر الله – عزَّ وجل -، واللُّجوء إليه بالدُّعاء دائمًا حتى لو لم تقع في معصية، سَل الله العصمة من المعاصي، سل الله أن يتولاك بما يتولى به الصالحين من عباده.
5⃣والخامس: مُلازمة الصالحين، بالاختلاط بهم إن أمكن ولو في المساجد أو بالاتصال الهاتفي، تسأله عن حاله، ويسأل عن حالك، ويرشُدك إلى شيء خَفِي عليك أو تُرشده، هذه كلُّها معينة على الاستقامة والحماية من المعاصي – إن شاء الله تعالى
☑العلامة الفقيه عبيد الجابري حفظه الله ورعاه.