Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

شفاعة /ምልጃ/

شفاعة /ምልጃ/
አጋሪዎች ለሽርካቸው ከሚያቀርቡት ምክንያት አማልክቶቻቸው ለአላህ አማላጅ እንደሚሆኗቸው ማሰብ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
«ከአላህም ሌላ የማይጐዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይገዛሉ፤ እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው»
📚[ዩኑስ/ 18]
አላህ ምክንያታቸው ከንቱ መሆኑን በተከበረ ቃሉ አረጋገጠ።
የ شفاعة አይነቶች
ሸፋዓ በሁለት ይከፈላል፡-
1ኛ الشفاعة المثبته (የሚፈቀድ ምልጃ) ይህ ምልጃ ከአላህ ብቻ የሚለመን ሲሆን ጠቃሚ የሚሆነው
አንደኛ፡- ምልጃ ጠያቂውን (አማላጁን)ና የሚጠየቅለትን አላህ ሲወዳቸው፡፡
ሁለተኛ፡- አላህ አማላጁን ሲፈቅድለት ብቻ ነው፡፡
2ኛالشفاعة المنفيه (የማይፈቀድ ምልጃ) ከአላህ ሌላ ማንኛውንም ፍጡር እንዲያማልዱን መለመን ነው፡፡
ይህ ከኢስላም ከሚያስወጣው ትልቁ ሽርክ የሚመደብ ነው፡፡
🔜ኢን ሻአ ላህ ይቀጥላል…
🔚ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!