Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በኮቪድ 19 (ኮሮና ቫይረስ) ጉዳይ ብዙ ሰው ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እየገባ ነው።


በኮቪድ 19 (ኮሮና ቫይረስ) ጉዳይ ብዙ ሰው ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እየገባ ነው። በመጨነቅ የሚቀየር ላይኖር መጨነቅ አያስፈልግም። ይልቁንም የሚያስፈልገው:–
① ስለበሽታውና ጥንቃቄዎች በቂ ግንዛቤ መያዝ፣
② ተጋላጭነትን ከሚጨምሩ ነገሮች መጠንቀቅ፣ ከአላስፈላጊ ቅልቅል በመታቀብ ሰበቡን ማድረስ፣
③ የተያዘንም ሆነ ያልተያዘን የሚመለከተውን ሸሪዐዊ ህግ መጠበቅ (በሽታው ወዳለበት ሃገር አለመሄድና በሽታው ካለበት አለመውጣት)፣
④ በሽታው አገር ውስጥ መግባቱ ኦፊሻሊ ቢነገር ሊከሰቱ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱ ነገሮች በማሰብ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ፣
⑤ ዱዓእና ዚክር ማድረግ፣
⑥ ህመሙ ካጋጠመ ወደ ሌሎች እንዳይተላለፍ ጥንቃቄ መውሰድ፣ ሃኪም ማማከርና አስፈላጊውን ክትትል ማድረግ፣
⑦ የበሽታው የገዳይነት ደረጃ እስካሁን እየተዘገበ ባለው ከ2%–4% ብቻ ነውና ተስፋ መቁረጥ ውስጥ መግባት አይገባም። ከዚያህም የከፋ ቢሆን ከአማኝ የሚጠበቀው በጌታው ላይ ያለውን ተስፋ ከፍ ማድረግ ነው።
⑧ የሚመጣው አይታወቅምና ለማንኛውም ነገር እራስን ማዘጋጀት። እዳ ካለ በመክፈል፣ ተውበት ማድረግ። ሙእሚን እያንዳንዱን ክስተት ወደጌታው ለመቃረብ ነው የሚጠቀመው።

Post a Comment

1 Comments

  1. ማሻ አላህ እንደናንተ አይነቱን አላህ ያብዛልን

    ReplyDelete