Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በአላህ ላይ ተመካ

በአላህ ላይ ተመካ!
~
ሰሞንኛው ፈተና ሁለት ጫፎችን እያሳየን ነው። አንዱ ጫፍ አላህን ትቶ ሰበቦች ላይ መንጠልጠል ነው። ሌላኛው ጫፍ ሰበቦችን የሚያጣጥል አጉል ጀብደኝነት ነው።
|
የመጀመሪያው ጫፍ:–
|
ሁላችንም እንደምናውቀው ኸይሩም ሸሩም ከአላህ ነው። ያንተ ሰበብ ሰበብ ብቻ ነው። አድራጊና ፈጣሪ አላህ ብቻ ነው። ስንቶች ተጨንቀው ተጠበው፣ ጥረው ግረው፣ ሰበብ በማድረስ ከኛ ልቀው ነገር ግን ልፋታቸውን ውሃ በልቶታት! ለምን? አላህ የወሰነው አይመለስማ! ስንት አቅመ ደካሞች የረባ ሰበብ ሳያደርሱ ፈተናውን እያለፉ ነው። ምክንያቱ አላህ ስላልወሰነባቸው ብቻ ነው። ስለዚህ ጥንቃቄ አድርግ ማለት ተወኩልህን ያንተ ደካማ ሰበብ ላይ አንጠልጥል ማለት አይደለም። ይሄማ አይን ያወጣ ሺርክ’ኮ ነው። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም 
 لا عَدْوَى
ይላሉ። "የበሽታ መረማመድ የለም" ማለት ነው። [ቡኻሪና ሙስሊም]
"እንዴ? በሽታ ከአንዱ ወደሌላው አይተላለፍም ማለት ነው?" እንዳትል። ይህንን ጉዳይ እንኳን እሳቸው አንተም አውቀኸዋል። በበርካታ ሐዲሦቻቸውም ይህንን ሐቅ ግልፅ አድርገውታል። "ከአንበሳ እንደምትሸሸው ሽሽ!" ብለው እያስጠነቀቁ ይሄ ይሰወራቸዋል ብለህ ለአፍታ እንኳን እንዳትገምት። "እናስ ምን ማለታቸው ነው?" ከተባለ ሐዲሡን ያስተላለፈውም ሶሐብይ በሽተኛ ግመል ገብቶ ጤነኞችን የሚበክልበትን አጣቅሶ ጠይቋቸው ነበር። ምላሻቸው "እናስ የመጀመሪያዋን ማን አሳመማት?" የሚል ነበር። 
ምን ማለት ነው? የመጀመሪያዋን ግመል ማንም አስተላልፎባት ሳይሆን አላህ ወስኖ እንዳሳመማት በተጨባጭ የምታውቁት ነው። ስለዚህ ከሷ የተላለፈባቸውን ግመሎች እንዲታመሙ ያደረጋቸውም አላህ እንደሆነ እንዳይዘነጋ እያሉ ነው።
ባጭሩ ስለ ሰበቦች የሚኖረን ግንዛቤ ቀይ መስመር እንዳያልፍ ልንጠነቀቅ ይገባል ለማለት ነው። ያለበለዚያ በአላህ ላይ ካለን ተወኩል በበለጠ በሰበቦቻችን ላይ የምንጠለጠል ከሆነ ይሄ የዐቂዳ ክፍተት እንደሆነ ይሰመርበት።
በሌላ በኩል እንዲህ አይነት ወቅታዊ መከራዎችን ተከትለው ሺርክ እና ቢድዐ የሚያነፈንፉ ሰዎች ስላሉ ተገቢውን የማንቃት ስራ እንስራ። እውነት ለመናገር ሺርክና ቢድዐ ከኮሮና የከፋ አደገኛ ፊትና ነው። 

ስለሌላኛው የገመዱ ጫፍ በአላህ ፈቃድ እመለሳለሁ።


Post a Comment

0 Comments