Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የቫለንታይንስ ቀንን አስመልክቶ



Valentine's Day /ቫለንታይንስ ደይ 

የቫለንታይንስ የፍቅር ቀንን አስመልክቶ ከተሰጠ የዑለማዎች ፈትዋዎች!


بسم الله الرحمن الرحيم

إن الحمد لله نحمده ونستعينه و نستغفره، و نعوذ بالله من شرور أنفسنا ومن سيئات أعمالنا، من يهده الله فلا مضل له و أشهد أن لا اله إلا الله وحده لا شريك له وأشهد أن محمد عبده ورسوله .


ብዙዎቻችችን እንደምናውቀው (በፈረንጆቹ የጊዜ ቀመር 2ኛው ወር) February የፍቅር ወር በመባል መከበር ከጀመረ ረጅም ጊዜያትን አስቆጥሯል::

ይህም "የቅዱስ ቫለንታይን" ቀን በመባል ይታወቃል:: ዛሬ ላይም የምናየው (የበዓሉ ስርአት) የጥንት ሮማኖችን እና የክርስትያኖችን ባህል ቅሪት ይዞ እናገኛለን::በመሆኑም ከተለያዩ ምክንያቶች አንጻር ለሙስሊሞች ይህን በዓል ማክበር ክልክል ይሆናል።

1 በመጀመሪያ ይህ በሸሪዓ ምንም ዓይነት መሰረት የሌለው የፈጠራ ተግባር ነው:: በሸሪዓ መሰረት የሌለውን ተግባር መፈጸም ደግሞ የተወገዘ ክልክል ነው:: በመሆኑም ይህ ጉዳይ እናታችን ዓኢሻ (ረድየላሁ ዓንሀ) ካስተላለፈችው ሀዲስ ውስጥ ይካተታል የአላህ መልዕክተኛ (صلى الله عليه وسلم) ተከታዩን ተናግረዋል

📔‹‹በዚህ በዲናችን ላይ ከርሱ ያልሆንን ያመጣ (ሰው) ስራው ተመላሽ ነው፡፡ (ተቀባይነት አይኖረውም)››

📚[ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል]

ማለትም ውድቅ ተግባር በመሆኑ ወደ ሰሪው አካል ተመላሽ ይሆናል።

2 ይህ በዓል መሰረቱ ሙስሊም ካልሆኑ አካላት ነው። ስለዚህም በዚህ ተግባር መሳተፍ ለነርሱ እውቅና መስጠት በጉዳያቸው ላይ አድናቂ መሆን እንዲሁም በሚያደርጉት ተገባርም ላይ መተባበር እና ከነርሱ ጋር መመሳሰል ማለት ነው። ይህን ተገባር መፈጸም ደግሞ የመልዕክተኛው (صلى الله عليه وسلم) ትዕዛዝ ለመዳፈር ወደዛቱበት ቀይ መስመር ውስጥ ለመግባት ይዳረጋል ከከሃዲያን ጋር መመሳሰልን እንዲህ ሲሉ አስጠንቅቀዋል

📔‹‹ከህዝቦች የተመሳሰለ እረሱ ከነርሱ ነው፡፡››
📚 [አቡ ዳውድ ዘግበውታል]

3 በዚህ በዓል ላይ የተለያዩ ሸሪዓ የከለከላቸው ተግባራት ተፈጻሚ ይሆናሉ ከብዙ በጥቂቱ ፓርቲዎች ይዘጋጃሉ ፣ ሙዚቃዎች ፣ የተለያዩ የብልግና ተግባራት ፣ ስርአት አጥነት እንዲሁም ልቅ የሆነ የወንዶችና የሴቶች መቀላቀል በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው። እነዚህ ተግባራት ደግሞ ሸሪዓ አምርሮ የሚቃወማቸው መጥፎ ተግባራት ናቸው። በመሆኑም ስለ ራሱ የሚጨነቅ ማንኛውም ሰው ከነዚህ ስርአት አጥነት ከሚስተዋልባቸው ዋልጌነት ከተንሰራፋባቸው መጥፎ ተግባራት ራሱን ሊቆጥብ ይገባል።

4 ይህ ተግባር የሰዎችን አዕምሮና ልብ በውሸት ነገሮች ቢዚ እንዲሆን የሚያደርግ እንዲሁም ከነዛ ምርጥ እና ጻድቅ የነበረሩ አርአያ ትውልዶችን ፋናን የሚጻረር በመሆኑ ዛሬም ላይ ቢሆን ከዚህ በዓል ጋር ተያያዢነት ያላቸውን ልማዳዊ ተግባር መፈጸም ክልክል ይሆናል::

ማለትም ምግቦች፣ መጠጦች ፣ ልብሶች እንዲሁም የስጦታ ልውውጦችን እና መሰል ተገባራትን ያጠቃልላል።

ሙስሊሞች ሆይ! በሀይማኖታችን ልንኮራ ይገባል። ደካማዎችና የጮሃን ሁሉ ተከታይ መሆን የለብንም።

🚫ማሳሰቢያ

በዚህ በዓልም ይሁን በ ሌሎች ክልክል በሆኑ በዓላት ላይ በማንኛውም መንገድ እነርሱን መተባበር ለሙስሊሞች የተከለከለ ነው። ምግብ ና መጠጥ የስጦታ እቃዎች በመግዛት ፣በመሸጥ ፣በማዘጋጀት ፣ በማከፋፈል ፣ በማስተዋወቅ እንዲሁም በሌሎች ማንኛውም መንገዶች መርዳት ክልክል ነው። ምክንያቱም እንዚህ ሁሉ በመጥፎ ተግባራት አንዱ ለሌላው ደጋፊ እንደሆኑ ይቆጠራሉና ነው። የአላህና የመልዕክተኛውን ህግ ለመጣስና ለመተላለፍ ተባባሪ መሆን አይገባ አላህ እንዲህ ይላል፦


قال تعالى : ( وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَى وَلا تَعَاوَنُوا عَلَى الإثم وَالْعُدْوَانِ وَاتَّقُوا اللَّهَ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ ) المائدة من الآية2 



📖«በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡» አል ማዒዳ 2

በመሆኑ ራሳችንንም ሆነ ቤተሰቦቻችንን ከዚህና መሰል በሸሪዓ መሰረት ከሌላቸው ተግባራት በመቆጠብ የራሳችንንም ክብር እንዲሁም በዚህ ምድር ላይ ስንኖር ያለንን ብቸኛ አንጡራ ሀብታችን የሆነውን ዲናችንን ከብክለት ልንጠብቅ ይገባል።

የመዕልክተኛውን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሱናህ አጥብቀን በመከተል የከሃዲያንን መንገድ ልንርቅ ይገባናል፡፡

ሙስሊሞችን በጠቅላላ ከውጫዊም ሆነ ውስጣዊ ከሆኑ መጥፎ ተግባራት እንዲጠብቀንና በእምታችን ላይ ጽናት እና ብርታት እንዲሰጠን አላህን እማጸነዋለው። አላህ የተሻለ ያውቃል።

📝ማስታወሻ!

ይህን ጽሁፍ ያዘጋጀሁት የተለያዩ ዑለማዎች ስለዚህ በዓል ተጠይቀው የሰጡትን ፈትዋ መሰረት አድርጌ ሲሆን ። የመልእክት መደጋገም እንዳይኖርና ለንባብ አሰልቺ እንዳይሆን ፍሬ ነጥቦችን አሳጥሬ ለማውጣት ሞክርያለው።

ባለማወቅም ይሁን በመዘንጋት የተሳሳቱ ሙስሊም ወንድምና እህቶችን ማረሚያና መገሰጫ እንዲሆን ጌታዬን በመልካም ስሞቹና በሙሉባህሪዎቹ እማጸነዋለው።


وأسأل الله عز وجل أن يُوفقني وجَمِيعَ المسلمينَ لِما يحبه ويرضى.

والله تعالى أعلم وصلى الله وسلم على نبينا محمد!

📝ወንድማችሁ ሀይደር ኸድር




አድራሻዎቻችን ይቀላቀሉ


ፌስቡክ           ቴሌግራም         ዩቲዩብ