Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የፍቅረኞች ቀን (Valentines Day)


የፍቅረኞች ቀን (Valentines Day)
ﺑِﺴْﻢِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦِ ﺍﻟﺮَّﺣِﻴﻢِ
ቫለንታይንስ ማነው??? ለሚለው የተለያዩ ታሪኮች እና መላምቶች ቢኖሩም ከነሱ ውስጥ አንዱን እንመለከታለን በ አላህ ፍቃድ በሶስተኛው ክፈለዘመን በ ሮም ውስጥ በ ከላውዲዎስ ሁለተኛ
የንግስና ዘመን የኖረ ቅዱስ ቫለንታይንስ በመባል የሚታወቅ ታዋቂ ቄስ አገልጋይ ነበር በዛን ዘመን የነመረው ንጉስ ከላውዲዎስ ሁለተኛ ውሳኔን አስተላለፈ ውሳኔውም ምን ነበር ያላገቡ ወጣት ወንዶች ሚስት እና ቤተሰብ ካላቸው ይልቅ ጥሩ ወታደሮች መሆን ስለሚችሉ በ እነሱ ላይ ጋብቻን እንዳይፈፅሙ ውሳኔን አስተላለፈ ይህ የንጉሱ ፍትሃዊ ያልሆነ ውሳኔ ያልተወጠለት ቄስ ቫለንታይንስ ፍትሃዊ አይደለም ብሎ ያሰበውን የ ንጉሱን ውሳን ባለመቀበል በድብቅ ወጣት ፍቅረኞችን ማጋባቱን
ተያያዘው ነገር ግን ይህ ድርጊቱ በንጉስ ከላውድዎስ ሲደረስበት ንጉሱም ከላውዲዎስ እንዲገደል ትዛዝ አስተላለፈ ፡፡ ይህ እንግዲ ቫለንታይንስ ሰርቱዋችዋል በመባል ከሚሰጡ የተለያዩ መላምቶች ውስጥ አንዱ ነው አብዛሃኛዎቹ መላምቶች ቫለንተይንስ የተባለው ቄስ ለፍቅር ብዙ መስዋትነትን እንደከፈለ ያመላክታሉ፡፡ ታድያ በየአመቱ ቀን ተሰቶት የሚከበረው ይህ የፍቅረኞች ቀን ይህንን ቅዱስ ቫለንታይንን በመባል ይታወቅ የነበረውን ቄስ በማስመልከት ነው የሚያከብሩት፡፡
አጂጂጂጂብብብ !!!!!
አሁን ወደተፈለገበት ወደኛ ወደ ሙስሊሞቹ ስንመጣ ማንገኛውም ሸሪአን የሚፃረሩ ባእላት ሁሉ ቢድአ (ፈጠራ ) የሆኑ ባእላት (ኢዶች) ናቸው፡፡ እነዚህ በአላት በሰለፉነ ሳሊህም ዘመን ስለማይታወቁ ቢድአነታቸው አያጠራጥርም እነዚህ አብዛሃኛዎቹ በአላት ደግሞ የስጀመሩት ከ ኢስላም ውጭ ያሉ አካላት ሊሆኑ ስለሚችሉ እናም እነዚህን ባእላት ማክበር ከ አላህ እና ከ ነብዩ ጠላቶች መመሳሰል ሊሆን ይችላል፡፡ ሸሪአዊና በሙስሊሙ ዘንድ የታወቁ ባእላት ኢድል አልፈጥር እና ኢዱል አድሃ ናቸው ለነዚህም ማስረጃ ይሆን ዘንድ የሚከተለውን
ሃዲስ ዕንመልከት፡-
አነስ ኢብኑ ማሊክ እንዲህ ይላሉ<< የአላህ መልእከተኛ( ﷺ ) የመዲና ሰዎች በመሀይምነት ዘመን (ደስታቸውን የሚገልፁባቸው) የሚጫወቱባቸው ሁለት ክብረበዓላት እያሏቸው ወደ መዲና መጡ።ይህንን ባዩ ጊዜ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፦እናንተ በመሀይምነት ዘመን የምትጫወቱባቸው ሁለት ቀናት እያላችሁ ወደናንተ መጣሁ፡አላህ በእርግጥ ከእነርሱ የተሻለ ቀን
ለውጦላችሁዋል፡እነርሱም የፈጥር እና የእርድ(አደሀ) በዓላት
ናቸው>> (አቡዳውደ እና አህመድ ዘግበውታል አልባኒይ ሰሂህ ብለውታል)
ከነዚህ በእላት ውጭ የተፈጠሩ ባእላት ወደፈጣሪዎቹ ተመላሾች ይሆናል በሸሪአም ተቀባይነት አይኖራቸውም ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለመም ምን ብለዋል “ በዚህ ሃይማኖታችን ውስጥ ከሱ
ያልሆነን አዲስ ነገር የፈጠረ ያመጣ እሱ (ፈጠራው) ተመላሽ ይሆንበታል፡፡”ብለዋል( ቡኻሪ እና ሙስሊም ) ስራው ተመላሽ ይሆናል በ አላህ ዘንድ ተቀባይነት የለውም ማለት ነው በሌላ ገለፃ ደግሞ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂሂ ወሰለም ምን ብለዋል “ እኛ ያላዘዝነው ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ
ይሆንበታል “ ብለዋል (ሙስሊም)፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አንድ ሙስሊም በ አላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ ይህን በአል ማክበርም ፣ ምግብ ማዘጋጀትም በአሉን አስመልክቶ ፣ ስጦታ መሰጣጠትም አይፈቀድለትም ከምንም በላይ ደግሞ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችን ፋና መከተል የለበትም እራሱን በሀይማኖቱ ማነፅ ይኖርበታል በኸይር አስከታይ እንጂ በመጥፎ ነገር ተከታይ (ጅራት) ሊሆን አይገባም ለሱ ሰለፉነ ሳሊህን መከተል በቂው ነው እነሱን መከተል ከቆሙበት መቆም ያብቃቀዋል ጭማሪም ሳያስፈልገው የ እነሱ ፋና መከተል ወደ ኸይር እንጂ ወደ ሸር ይወስዳል ብለህ ታስባለህን ??
ኢስላም ከ ጋብቻ በፊት ያለን የ ተቃራኒ ፆታን ግንኙነትን ያወግዛል ይህ የፍቅረኞችን ቀን ደግሞ በስፋት የሚያከብሩት አፍላ እድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች እንደ መሆናቸው መጠን በአሉ ዚናን
በማስፋፋቱ ረገድ አስተዋፅኦ ስለሚያደርግ በ አሉን እጂግ የከፋና የተጠላ ደርገዋል አላህ ከ እንደዚህ አይነቱ ክስረተት ይጠብቀን ስለዚህ ሙስሊም ነኝ የሚል ሰው እነዚህን በእላት ማክበር
እንደማይፈድለት እና በእነዚህም መሰረት የሌላቸውን በዲን ውስጥ የሌሉ በአላት በማክበር ራሱን ማስጠመድ እንደሌለበት (ዑለሞች ተስማምተው አፅድቀውታል) ወላሁ አዕለም ፡፡



by Keriya Mohammed