Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሽርክ


#_ሽርክ ፡- በአምልኮ ከአላህ ጋር ሌላን እኩል ማድረግ ማለት ነዉ፡፡ አምልኮን ከአላህ ዉጪ ለማንም ማዋል የሽርክ ተግባር ነዉ፡፡ ተዉሂድ ፍትህ ነዉ፡፡ ሽርክ ግን የበደሎች ሁሉ በደል ነዉ፡፡ በመሆኑም አላህ የማይምረዉ ከባድ ወንጀል ነዉ፡፡ "አላህ በእርሱ ላይ ማጋራትን (ሽርክን) በፍፁም አይምርም! ከሽርክ በታች ያለን (ኃጢአት) ለሚሻው ሠው ይምራል" አል-ኒሳዕ 48 አንዳንድ ሰዎች ስለ ተውሂድ መስማት አይፈልጉም፡፡ የተለያዩ የኢባዳ አይነቶችን ለነብያት፣ ለመላዕክት እና ለሷሊሆች ያዉላሉ፡፡ ለምሳሌ፡- ጭንቅ በሚገጥማቸዉ ጊዜ በቀብር ዙሪያ ጠዋፍ ያደርጋሉ፣ ከአላህ ዉጪ ማንም መፈፀም
የማይችላቸዉን ጉዳዮች ለማስፈፀም ከምዕተ አመታት በፊት ለኖሩ ሰዎች የድረሱልን ጥሪ ያሰማሉ! ይማፀናሉ!! ልጅ ቢያጡ ለሚያመልኩት ሰዉ ስለት ይገባሉ፣ በስሙም ይምላሉ፡፡ በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች ይህ አይነቱ ቀብር አምልኮ ሰዎችን እየሸነገለ ይገኛል፡፡ ጁንዱብ ኢብኑ አብዲላህ ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ እንዲህ ብለዋል፡፡ (አደራችሁን! ቀብሮችን የአምልኮ ስፍራ አንዳታረጉ፡፡ እኔ ከዚህ አይነቱ
ተግባር እከለክላችለሁ፡፡) ሙስሊም ዘግበዉታል አዎ! ታላቁ ነብይ ይህንን የተናገሩት ህይወታችዉ ከማለፉ አምስት ቀናት ብቻ ቀደም ብለዉ ነበር፡፡ ደግመዉ ደጋግመዉ ተመሳሳይ መልዕክት አስተምረዋል፡፡ በዱንያ ቆይታቸዉ በመጨረሻዎቹ ሰዓታት ሳይቀር ከቀብር አምልኮ አስጠንቅቀዋል፡፡ አጅግ በጣም የሚያሳዝነዉ፤ ሸይጣን ይህ አይነቱን ባዕድ አምልኮ የሚያስፋፋበትን ስልት መቀየሩ ነዉ፡፡#_አንዳንድ ሰዎች ‹ቅርስን መንከባከብ› ፣ ‹ታሪክን ማቆየት› እና መሰል ምክኒያቶችን በማቅረብ የቀብር አምልኮ ቦታዎች በብዙ ወጪ እያሻሻሉና እየገነቡ ይገኛል፡፡ ይህ አይነቱ ተግባር ባዕድ አምልኮን ያበረታታል፡፡ በቁርአንና በሱና የተጠቀሱ መረጃዎች አጅግ በጣም ግልፅና በርካታ ከመሆናቸዉ ጋር የተለያዩ ጦሪቃዎን የሚከተሉ ሙሪዶች አንዲያዉቋቸዉ አልተደረገም፡፡ አንድ ዒባዳ(አምልኮ) ተቀባይነት
እንዲያገኝ ሁለት መስፈርቶች መሟላት አለባቸዉ፡፡ በኢኽላስ ለአላህ ብቻ ሊፈፀም እና በነብዩ የአምልኮ ፈለግ መሰረት ሊተገበር ይገባዋል፡፡ አላህ ቀጥተኛዉን መንገድ ይመራቸዉ ዘንድ እንማፀነዋለን!!

Post a Comment

0 Comments