Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ :- አንድ አደጋ ሲያገኘው የሚበሳጭ ሰው እንዴት ይታያል?

ጥያቄ :- አንድ አደጋ ሲያገኘው የሚበሳጭ ሰው እንዴት ይታያል?

-->መልስ :- ሰዎች አደጋ ሲያገኛቸው ፦ በአራት ደረጃዎች ይከፈላሉ

#አንደኛ_ደረጃ፦የሚበሳጭና የሚቆጣ፦ይህም የተለያየ አይነትአለው፦

1. መበሳጨቱ ከልቡ መሆኑ፦ አላህ በወሰነበት ነገር አላህ ላይ መበሳጨትና መቆጣት ።ይህ ሓራም ነው ወደ ኩፍርም ሊያመራ ይችላል። አላህ እንዲህ ይላል፦“ ከሰዎችም(ከሃይማኖት) በጫፍ ላይ ሆኖ አላህን የሚገዛ ሰው አለ፣ ታድያ መልካም ነገር ቢያገኘው በርሱ ይረጋል፣ መከራ ብታገኘው ግን ፊቱን ያዞራል፣ የቅርቢቱንም ሆነ የመጨረሻይቱን ዓለም ከሰረ፣....” (አል-ሐጅ 22፡11)

2.በምላስ የሆነ መበሳጨት፦ ዋይ ጥፋቴ፣ ወዮ፣ ወዮ፣ እያሉ ዋይታ ማሰማትና የመሳሰሉት፦ ይህምሓራምነው።

3.በአካላት የሚንፀባረቅ መበሳጨት፦ ጉንጭ ንእንደ መጠፍጠፍ፣ ልብስን መቅደድ፣ ፀጉርን መንጨትና የመሳሰሉት። እነዚህ ሁሉ ሓራም ናቸው። ግዴታ የሆነውን ሰብር ተቃራኒዎች ናቸው።

#ሁለተኛው_ደረጃ፦ሰብር (ትዕግስት) ማድረግነው፦ የደረሰበትን አደጋ ከባድመሆኑን ያውቃል ነገር ግንይችለዋል። መከሰቱን ቢጠላም ኢማኑ ከመቆጣትና ከመበሳጨት ይጠብቀዋል። ለዚህ ሰው አደጋው መከሰቱና አለመከሰቱ እኩል አይደሉም።ይህ ማለትም ሰብር ግዴታ (ዋጂብ) ነው። አላህ በሰብር አዞናልና፦ “ታገሱም፣ አላህ ከትዕግስተኖችጋር ነውና።”

#ሦስተኛውደረጃ፦መውደድ ነው፦ ሰውየው የሚደርስበትን አደጋ መውደድ ማለትነው። የአደጋው መከሰትም ሆነ አለ መከሰት ለሰውየው እኩልነው።እንደከባድ ሸክም አድርጎ አይመለከተውም። ይህ ሁኔታ የተወደደ (ሙስተሐብ) ነው። ግዴታ (ዋጅብ) ግን አይደለም ይበልጥ ተቀባይነት ባለው አተያይ።በዚህኛውና በሁለተኛው ደርጃ መካከል ያለው ልዩነት ግልፅ ነው።በዚህ ደረጃ ላለሰው የአደጋመከሰትም ሆነ አለ መከሰት እኩልነው። በሁለተኛው ደረጃ ላይ ላለሰው ግን አደጋ መከሰቱ ይከብደዋል ግንትዕግሥት ያደረጋል።

#አራተኛው_ደረጃ፦ማመስገን፦ ይህ ደሞ ከሁሉም የላቀ ደረጃ ነው። ሰውየው በደረሰበት አደጋ አላህን ማመስገን ማለትነው። ምክንያቱም የዚህአደጋ መከሰት ወንጀሎችን እንደሚያብስለት ወይም (ሐሰናቱን) እንደሚጨምርለት ያውቃልናነው። ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “አንዲትም አደጋ አንድን ሙስሊም አግኝታው አትቀርም አላህ በዚያች አደጋ የሰውየውን ወንጀል ቢያብስለት እንጂ፤እሾህ እንኳ ብትወጋው።”ብለዋል ።

ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን

Post a Comment

0 Comments