Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰላት የማይሰግድ ሰው ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው



ሰላት የማይሰግድ ሰው ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው

ጥያቄ፡- አንድ ሰው ቤተሰቦቹ ሶላት እንዲሰግዱ ተደጋጋሚ ምክር ቢመክርም ፈቃደኛ ሊሆኑለት አልቻሉም፡፡ ይህ ሰው ቤቱን ለቆ ይውጣ ወይንስ ከእነር ሱ ጋር ተቀላቅሎ ይኑር?

መልስ፡- ቤተሰቦቹ ፍጹም ሶላት የማይሰግዱ ከሆኑ ካፊሮች ወይም ከኢስላም ያፈነገጡ ናቸው፡፡(¹) በመሆኑም ከእነርሱ ጋር በፍጹም አብሮ ሊኖር አይገባም፡፡ ነገር ግን አላህ ወደቅኑ መንገድ ሊመራቸው ስለሚችል ተስፋ ሳይቆርጥ ዳዕዋ ሊያደርግላቸው ይገባል፡፡ 

ሶላትን ፍጹም የተወ ሰው ከሐዲ ለመሆኑ የሚከተሉት የቁርዓን፣ የሐዲስ፣ የሶሃቦች ንግግር እና የጤናማ አእምሮ ማስረጃዎች ይጠቁማሉ፡-

፠ የቁርዓን ማስረጃ
አላህ ስለሙሽሪኮች የሚከተለውን ቁርዓን ተናግሯል፡-
فَإِن تَابُوا وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَآتَوُا الزَّكَاةَ فَإِخْوَانُكُمْ فِي الدِّينِ ۗ وَنُفَصِّلُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ (11)
“ቢጸጸቱም፣ ሶላትንም ቢሰግዱ፣ ዘካንም ቢሰጡ የሃይማኖት ወንድሞቻችሁ ናቸው፡፡ ለሚያውቁ ሕዝቦችም አንቀጾችን እናብራራለን፡፡” (አት'ተውባህ፡ 11)
የዚህ አንቀጽ ግንዛቤ ከላይ አላህ የዘረዘራቸውን ነገሮች (ጸጸት፣ ሶላት እና ዘካን) ካልፈጸሙ ለእኛ ወንድሞች ሊሆኑ እንደማይችሉ ነው፡፡ የተፈጸመው ወንጀል ትልቅ እንኳ ቢሆን ከዲን ወንድማማችነት ሊያወጣ በፍጹም አይችልም፡፡ የዲን ወንድማማችነት የሚፈርሰው ከኢስላም የሚያስወጣ ተግባር ሲፈጽም ብቻ ነው፡፡ 

፠ ከሐዲስ ማስረጃ
የሚከተለው የነብዩ ﷺ ንግግር ነው፡- 
"إن بين الرجل وبين الشرك والكفر ترك الصلاة" رواه مسلم 
“በግለሰቡ እና በክህደት ወይም በሽርክ መካከል ያለው ልዩነት ሶላትን መተው ነው፡፡”
ቡረይዳ ባስተላለፈው ሐዲስ ደግሞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"العهد الذي بيننا وبينهم الصلاة فمن تركها فقد كفر"
“በእኛ እና በእነርሱ መካከል ያለው ልዩነት ሶላት ነው፡፡ ሶላትን የተወ በእርግጥ ካደ፡፡”

፠ ከሶሃቦች ንግግር
የሙዕሚኖች አሚር ኡመር رضي الله عنه የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"لا حظ في الإسلام لمن ترك الصلاة"
“ሶላትን ለተወ ሰው በኢስላም ምንም ዓይነት ዕድል የለውም፡፡”
ዓብደሏህ ብን ሸቂቅ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
(كان أصحاب النبي صلى الله عليه وسلم لا يرون شيْا من الأعمال تركه كفر غير الصلاة) (الترمذي : ٢٧٥٧)
“የነብዩ ሶሃቦች ከሶላት ውጭ አንድን ተግባር በመተው ክህደት ውስጥ ያስገባል ብለው አይመለከቱም ነበር፡፡” (አት`ቲርሚዚ : 2757) (²)

፠ የጤናማ አእምሮ ማስረጃ
በልቡ ውስጥ የብናኝ ክብደት ኢማን ያለው ሰው ከፈጣሪው ጋር የሚያገናኘውን ትልቁን የኢባዳ ዘርፍ ሶላትን ይተዋል ተብሎ አይታሰብም፡፡
መረጃዎች ሲፈተሹ ሶላትን የተው ሰዎች ከሀዲ እንደሚሆኑ እና የሙርተድነት አህካሞች እንደሚረጋገጥባቸው የሚገልጹ እንጅ ሙእሚኖች እንደሆኑና ከእሳት ነጻ ሆነው ጀነትን እንደሚወርሱ የሚያረጋግጡ አይደሉም፡፡ በመሆኑም ሶላትን የተው ሰዎች ከሐዲ እንደሚሆኑ የሚያስረዱ መረጃዎችን ጸጋን መካድ ወይም ከክህደት በታች ያለ ክህደት በማለት የተለየ ትርጉም መስጠት ትክክል አይሆንም፡፡

⚖️ አንድ ሰው ሶላቱን በመተው ምክንያት የሚከተሉት የሙርተድነት አህካሞች (ህግጋቶች) ይረጋገጡበታል፡-

አንደኛ፡- ሙስሊም ሴት ማግባት አይችልም፡፡ ሙስሊም ሴት ኒካህ አድርጎ ከሆነ ኒካሁ ባጢል ይሆናል፡፡ እርሷም ለእርሱ ሀላል (የተፈቀደች) ልትሆን አትችልም፡፡ 
በዲናቸው ምክንያት የተሰደዱ ሴቶችን አስመልክቶ አላህ ሲናገር፡-
فَإِنْ عَلِمْتُمُوهُنَّ مُؤْمِنَاتٍ فَلَا تَرْجِعُوهُنَّ إِلَى الْكُفَّارِ ۖ لَا هُنَّ حِلٌّ لَهُمْ وَلَا هُمْ يَحِلُّونَ لَهُنَّ ۖ 
“አማኞችም መሆናቸውን ብታውቁ ወደከሃዲዎች አትመልሷቸው፡፡ እነርሱ (ሴቶች) ለእነርሱ የተፈቀዱ አይደሉምና፡፡ እነርሱም (ወንዶቹ) ለእነርሱ አይፈቀዱምና፡፡” ( ሙምተሀሂና፡ 10)

ሁለተኛ፡- ግንኙነት ቢያደርግም ባያደርግም ጋብቻ ከፈጸመ በኋላ ሶላቱን ከተወ ባሳለፍነው የቁርዓን ማስረጃ መሰረት ጋብቻው ይፈርሳል፡፡ ሚስቱ ለእርሱ የተፈቀደች አትሆንም፡፡ 

ሶስተኛ፡- ሶላት የማይሰግድ ሰው ቢያርድ እርዱ በክት ይሆናል፡፡

አራተኛ፡- ሶላት የማይሰግድ ሰው መካ ወይም በሀረም ክልል መግባት አይችልም፡፡ (³)
አላህ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّمَا الْمُشْرِكُونَ نَجَسٌ فَلَا يَقْرَبُوا الْمَسْجِدَ الْحَرَامَ بَعْدَ عَامِهِمْ هَٰذَا ۚ وَإِنْ خِفْتُمْ عَيْلَةً فَسَوْفَ يُغْنِيكُمُ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ إِن شَاءَ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ حَكِيمٌ (28)
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አጋሪዎች እርኩሶች ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህም አመታቸው በኋላ የተከበረውን መስጊድ አይቅረቡ፡፡ ድህነትንም ብትፈሩ አላህ ቢሻ ከችሮታው በእርግጥ ያከብራችኋል፡፡ አላህ አዋቂ ጥበበኛ ነውና፡፡” (ተውባህ ፡ 28)

አምስተኛ፡- ዘመዱ ቢሞት ከውርሱ መካፈል አይችልም፡፡ ለምሳሌ አባት ይሰግዳል ልጅ ግን አይሰግድም ድንገት አባት ቢሞት ሶላት የሚሰግድ የአጎት ልጅ ይወርሳል እንጅ ልጅ በፍጹም ሊወርስ አይችልም፡፡
ኡሳማ ባስተላለፈው ሐዲስ ረሱል صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"لا يرث المسلم الكافر ولا الكافر المسلم" متفق عليه
“ሙስሊም ካፊርን አይወርስም ካፊርም ሙስሊምን አይወርስም፡፡”

ስድስተኛ፡- ሶላት የማይሰግድ ሰው ቢሞት አይታጠብም አይከፈንም አይሰገድበትም ከሙስሊሞች መቃብርም አይቀበርም ፡፡ ስለዚህ ምን እናድርግ? ክብር ሊኖረው ባለመቻሉ ከከተማ ውጭ ወስደን መሬቱን ቆፈር ቆፈር አድርገን እስከልብሱ አዳፍነን መመለስ ብቻ ነው፡፡
ሶላት አለመስገዱ እየታወቀ ሙስሊሞች ሶላተል ጀናዛ እንዲሰግዱበት ለማድረግ ከአንዳንድ ሰዎች የሚደረገው ጥረት ትክክል አይደለም፡፡

ሰባተኛ፡- የትንሳኤ ቀን ከፊርአውን፣ ከሃማን፣ ከቃሩን እና ኡበይ ብን ኸለፍ ከተባሉ ከሀዲዎች ጋር ይቀሰቀሳል፡፡(⁴)
©≈ ሶላት ለማይሰግድ ሰው እዝነትና ምህረት ከአላህ መለመን በፍጹም የተከለከለ ነው፡፡ 
አላህ እንዲህ ብሏል፡-
مَا كَانَ لِلنَّبِيِّ وَالَّذِينَ آمَنُوا أَن يَسْتَغْفِرُوا لِلْمُشْرِكِينَ وَلَوْ كَانُوا أُولِي قُرْبَىٰ مِن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمْ أَنَّهُمْ أَصْحَابُ الْجَحِيمِ (113)
“ለነብዩና ለነዚያ ላመኑት ለአጋሪዎቹ የዝምድና ባለቤቶች ቢሆኑም እንኳ እነሱ (ከሀዲዎቹ) የእሳት ጓዶች መሆናቸው ከተገለጸላቸው በኋላ ምህረትን ሊለምኑ የሚገባ አልነበረም፡፡” (ተውባ፡ 113)

الله أعلم وصلى الله على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين
الشيخ ابن عثيمين – رسالة صلاة النبي . ص (29-30) ومجموع فتاو

================================

(¹). ስንት ሶላቶችን የተወ ሰው ነው ካፊር የሚሆነው? 
ሸይኽ ብን ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) የሚከተለውን ተናግረዋል:–
ሰላትን ሙሉ በሙሉ የተወ ነው ወይስ በሌላ በሚለው ዑለሞች አንድ ሰላት በመተው፣ ሁለት ሰላት በመተውና አንዳንዶቹ ደግሞ ሁለት ሰላቶችን አሰባስቦ መስገድ ሚቻል ከሆነ የሁለተኛው ወቅት በመውጣቱ ይከፍራል ይላሉ። 
ነገር ግን ከማስረጃዎች ግልፅ የሆነው ካፊር የሚሆነው ሰላትን ሙሉ በሙሉ የተወ ጊዜ ነው። ማለትም ሰላትን በመተው ነፍሱን አዘወተራት ዙሁርንም፣ ዓሱርንም፣ መግሪብንም፣ ዒሻንም፣ ሱብሂንም አይሰግድም ይህ ነው ካፊር የሚሆነው። (ሸርሁል ሙምቲዕ‐1/307)
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያም (ዓለይሂ ረህመቱላህ) የሄዱበት በዚሁ ነው። (መጅሙዑል ፈታዋ‐22/49) 

(²). ሃፊዝ ዓብዱልሐቅ አልኢሽበይሊይ (ረሂመሁላህ) በኪታባቸው ላይ በሰላት ውስጥ የሚከተለውን ብለዋል:–
"ሰአተ ገደቡ እስኪወጣ መተውን አውቆ ሰላትን የማይሰግድን ሰው በማክፈር ሁሉም ሰሐቦችም ሆነ ከነሱ በኋላ ያሉት ተጉዘውበታል ከነዚህ መካከል ዑመር ብን አልኸጣብ ፣ ሙዓዝ ብን ጀበል ፣ ዓብደላህ ብን መስዑድ ፣ እብን ዓባስ ፣ ጃብር ፣ አቡ ደርዳእ ፣ ልክ እንደዚሁ ከዓልይ ብን አቡ ጣሊብም ተዘግቧል። እነዚህ ከሰሐቦች ናቸው። ከነርሱ ውጭ ደግሞ አህመድ ብን ሃንበል ፣ ኢስሐቅ ብን ራህዊያህ ፣ ዓብደላህ ብን ሙባረክ ፣ ኢብራሒም አንነኸዒይ ፣ ሐኪም ብን ዑየይናህ ፣ አዩብ አስሰኽቲያኒይ ፣ አቡ ዳውድ አጥጠያሊሲይ ፣ አቡበክር ብን አቢ ሸይባህ ፣ አቡ ኺስመተ ዙሐይር ብን ሃርብ" ይገኙበታል (ኪታቡ ሰላት ሊብኒል ቀይም አልጀውዚ ገፅ/36)

(³). ይህ ለሁሉም ካሃዲያን ቋሚ ህግ ሲሆን ሰላትን የተወ ሰው ግን የሙርተድ (ከእምነት ያፈነገጠ ሰው) ፍርድ ነው ተፈፃሚ ሚሆንበት። ሰላትን የማይሰግድ ግለሰብ እንዲቶብት ተጠይቆ ሰላት በመተው ከዘወተረ ይገደላል ሌሎቹም በሙርተድ ላይ ተግባራው የሚሆኑ ሸርዓዊ ህጎች ተፈፃሚ ይሆኑበታል። ምክንያቱም የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:-
((من بدّل دينه فاقتلوه)) (البخاري: ٣٠١٧)
"እምነቱን የቀየረን ግደሉት" (ቡኻሪ/3017) 

©≈ ይህ ከመሆኑ ጋር ግን እንዴት ነው ሚገደለው?፣ ማን ነው የሚገድለው?፣ ሲገደል ባሳለፈው ሰላት ነው ወይስ ለወደፊት አልሰግድም በማለቱ?፣ ሲገደል ካፊር ተብሎ ነው ወይስ ነፍስ እንዳጠፋ ወይም አግብቶ የሚያቅ ዝሙት እንደፈፀመ ሰው እስልምናው እንዳለ?፣ የነበረው መልካም ስራ ይታበስበታል ወይስ አይታበሱበትም? የሚሉትና ሌሎች ጉዳዬችን ኢማም ኢብኑል ቀይም (ዓለይሂ ረህመቱላህ) በዑለሞች መካከል ስላለው ልዩነት ቁርአንና ሐዲስን ድጋፍ በማድረግ "አስሰላት" በተሰኘው ኪታባቸው በሰፊው አብራርተውታል የፈለገ ቢመለከታቸው መልካም ነው።

(⁴). ዓምር ብን አልዓስ (ረዲየላሁ ዓንሁ) እንዳወሩት አንዴ ነብዩ ﷺ ዘንድ ሰላት ተወሳና እንዲህ አሉ "እርሷን [ሰላትን] ለተጠባበቃት የትንሳኤ እለት ብርሃን፣ ማስረጃና ነፃ መውጫ ትሆንለታለች, እርሷን ላልተጠባበቃት ግን ብርሃንም ማስረጃም ነፃ መውጫም አትሆንለትም, ግለሰቡም የትንሳኤ እለት ከቃሩን፣ ከፊርዓውን፣ ከሐማንና ከኡበይ ብን ኸለፍ ጋር ይሆናል" (አህመድ/6576 ሱነን አድዳሪሚ/2763 አልባኒ መሸካቱል መሳቢህ ላይ ሶሂህ ብለውታል) 

እነዚህ አራቶቹ በተለየ የተወሱት የክህደት ቁንጮ በመሆናቸው ነው። ሰላትን ከመጠባበቅ የሚተው ገንዘቡ፣ ንግስናው፣ ሹመቱ፣ ወይም ደግሞ ንግዱ ባተሌ አድርጎት ነው። ሰላትን ከመጠባበቅ:– ገንዘቡ ባተሌ ያደረገው ከቃሩን ጋር ይሆናል, ንግስናው ባተሌ ያደረገው ከፊርዓውን ጋር ይሆናል, ሹመቱ ወይም ስልጣኑ ባተሌ ያደረገው ከሐማን ጋር ይሆናል, ንግዱ ባተሌ ያደረገው ደግሞ ከኡበይ ብን ኸለፍ ጋር ይሆናል። (ኪታብ አስሰላት ሊብኒል ቀይም ገፅ/32)

መልእክት:– ሰላት የማይሰግድ ሰው አይከፍርም የሚሉት የሚያቀርቧቸው ማስረጃዎች አብዛኞቹ በራሳቸው ላይ ማስረጃ ሲሆኑ, ሌሎቹ ደግሞ ጭራሹኑ ማስረጃ የማይሆኑ፣ ሰላት መተው በሚቻልበት የችግር ግዜ ብቻ የተገደቡ፣ ከጥቅል ፍርድ ነጥሎ በማውጣት እና መሰል በቂ ካልሆኑ መረጃዎች የተነሱ ናቸው። ይህን ሸይኽ ብን ዑሰይሚን ሸርሁል ሙምቲዕ 1/312 እና ኢማም ኢብኑል ቀይም ኪታቡ አስሰላት ላይ ማስረጃዎችን በዘረዘሩበት ግልፅ አድርገዋል። (ረሂመሁሙሏህ)

የባህር ዳር አህሉ ሱና መሻይኾች ገፅ
https://t.me/alateriqilhaq


Post a Comment

1 Comments

  1. ፁሁፊን እዳለ በዋሳብና ኢሞ ሺሪ ለማረግ አይሄድም ከተቻለ አንዳንድ ፁሁፎችን ሺሪ ለማርግ እድ መች ብታርጉልን ።ጀዛኩም አላህ ኸይርን ጀዛ አላህ ይጠብቅልን ።እኔ ብዙ ትምህርት አግኚቸበት አለሁ ከልብ ነው ምስጋናይ

    ReplyDelete