Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሡሉ ሠላሣ.፦ ክፍል አስራ ሁለት

‎ሡሉ ሠላሣ.፦ ክፍል አስራ ሁለት

የኪታቡ ፀሀፊ እንዲህ አሉ

★ የሀሺያ ( ፍራቻ ) መረጃ አላህ እንዲህ ይላል ¹
« እነሡን አትፍሯቸው እኔን ፍሩኝ » (አልበቀራ 150)

★ የኢናባ. (መመለስ) መረጃ አላህ እንዲህ. ይላል ²

«ወደ ጌታችሁ ተመለሡ ለሡም እጅ ስጡ » ዙመር

★የኢስቲአና (እርዳታ መፈለግ) መረጃ አላህ እንዲህ ይላል
³
«አንተን ብቻ እንገዛለን በአንተ ብቻ እርዳታ እንለምናለን» አል ፋቲሀ

★ የኢስቲአዛ (መጠበቅ ) መረጃ⁴
አላህ እንዲህ ይላል « በተፍለቅላቂዋ ጎህ ጌታ በሆነው
እጠበቃለው በል» አል ፈለቅ
★ የእስቲጋሣ. ( የ ይድረሡልኝ ጥሪ) መረጃ
አላህ እንዲህ ይላል «ጌታችሁን እርዳታ በጠየቃችሁ ግዜ
ተቀበላችሁ» Ⅰ
★ የዘብህ (እርድ) መረጃ Ⅱ
አላህ እንዲህ ይላል «ስግደቴም ፣ እርዴም ፣ ህይወቴም ፣
ሞቴም ለአለማቱ ጌታ ለአላህ ነው በል። (163)
«ለእርሡም ተጋሪ. የለውም በዚህ (በማጥራት) ታዘዝኩ ።
እኔም የሙስሊሞች መጀመርያ ነኝ» በል።» አል አንአም
ከሀዲስ « ከአላህ ውጪ ላለ አካል ያረደ አላህ ከራህመቱ
አባሮታል»
★ የነዝር (ስለት) መረጃ
አላህ እንዲህ ይላል « ስለታቸውን ይሞላሉ ከፋቷ
የተንሠራፋ የሆነን ቀን ይፈራሉ »
_________
አጭር ማብራሪያ
_____
¹ ★ ሀሺያ
☞ ሀሽያ ማለት በእውቀት ላይ የተደገፈ ፍራቻ ነው. ስለ
አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ሀያልነት እና ብርቱነት ጠንቅቀው
የሚያውቁ ሠዎች የሚፈሩት የፍራቻ አይነት ነው አላህ
እንዲህ ይላል
« ከባርያው አላህን የሚፈሩትማ የሚያውቁት ናቸው»
² ★ኢናባ
☞ ኢናባ ማለት.የአላህ ትእዛዛት በመተግበር ክልክላቶቹን
በመራቅ ወደ አላህ መመለስ ማለት ነው
★ የሠው ልጅ ሢፈጠርም ተሣሣች ነው!!! አወቀነውም ሆነ
ሣናውቀው በተለያየ መልኩ ጌታችን አላህን እናምፀዋለን
መሀሪ የሆነው አዛኙ ጌታችን ግን የኛ ወንጀል ምንም ያክል
የበዛ ቢሆንም አዛኝነቱ ከቁጣው በላይ ነውና የሠራነውን
ወንጀል በአጠቃላይ የሚምምርበትን ተውበት የተሠኘን በር
ከፈተልን ይህ በር ጥቁሩን ፣ቀዩን ፣ደሀውን ፣ ሀብታሙን.
ሁሉንም ሣይለይ ከመቀርቀሩ በፊት ያንኳኳኳውን ሁላ
ያስገባል። ከተቀረቀረ ቡሀላ የመጡትን ግን ማስተናገጃ ቦታ
የለውም
~ መቼ ነው ይሔ በር የሚዘጋው ????
ይህ በር
1ኛ በግለሠብ ደረጃ ፦ አንድ ሠው ለመሞት ጫፍ ሢደርስ
ሁሉን ነገር ስለሚገለፅለት ቢፀፀት እና ቢመለስ ዋጋ
አይኖረውም
2ኛ ከትላልቅ የቂያማ ምልክቶች መካከል አንዷ የሆነችው
የፀሀይ በመግቢዋ መውጣት ናቸው
♂ አንድ ሠው ገርገራ ላይ ሆኖ እና ፀሀይ ከመግቢያዋ
ከወጣች ቡሀላ ተውበት ተቀባይነት የላትም
∴ ተውበት የሚያደርግ ሠው
① ተውበት ሊያደርግ ያሠበውን ወንጀል ማቆም አለበት
② ተውበት ወዳደረገው ወንጀል ላይመለስ ቁርጥ ውሣኔ
መውሠድ አለበት
③ በሠራው ወንጀል መፀፀት አለበት
④ ከሠው ልጅ ጋር በተያያዘ መልኩ ከሆነ የበደለውን
አውፍ ማስባል የወሠደውን ንብረት መመለስ አለበት
ከአራቱ አንዱ ከጎደለ ተውበቱ ተቀባይነት አይኖረውም!!
³ ★ኢስቲአና
☞ ኢስቲአና ማለት ፦ እገዛን መፈለግ ማለት ሢሆን
በተለያየ መልኩ ሊታይ ይችላል
① በአላህ መታገዝ ፡ በአላህ የሚታገዘው አካል ለአላህ
የተናነሠ እና የተዋረደ ሠው ነው, ጉዳዩንም ወደ አላህ
ያስጠጋ ሠው ነው, ከአላህ ውጪ ባለ አካል በዚህ መልኩ
መታገዝ ሽርክ ነው, አላህ ብቻ ነው የዚህ ኢባዳ ባልተቤት!
መረጃው ላይ እንደተመለከትነው አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ
ሒክማ በተሞላ ንግግሩ እንዲህ ይላል
( ﺇِﻳَّﺎﻙَ ﻧَﻌْﺒُﺪُ ﻭَﺇِﻳَّﺎﻙَ ﻧَﺴْﺘَﻌِﻴﻦُ )
« አንተን ብቻ ነው ምንገዛው. በአንተ ብቻ ነው እገዛ
ምንፈልገው»
እንደ አረበኛ የአነባብ ህግ ከስራው በፊት ሠራተኛው
ከተጠቀሠ ስራው ለዛ አካል ብቻ የተገደበ ነገር መሆኑን
ያጣቅማል
ለምሣሌ. (( ﻭَﺇِﻳَّﺎﻙَ )) የሚለው ባለቤት ሢሆን ስራው ደግሞ
((( ﻧَﺴْﺘَﻌِﻴﻦ )) ነው ስለዚህ ኢስቲአና በሀሊቃችን ላይ የተገደበ
ነው
②ፍጡራኖች የሚችሉት ነገር እርዳታ መፈለግ ፦ አላህን
ማመፅ ካልሆነ እና መልካም ነገር ከሆነ መረዳዳቱም
እርዳታም መጠየቁ የተፈቀደ ነገር ነው
አላህ እንዲህ ይላል « በመልካም ነገር እና አላህን
በመፍራት ተረዳዱ»
∞ ነገር ግን በወንጀል እና አላህን በማመፅ ላይ መተባበር
አይፈቀድም
አላህ እንዲህ ይላል ፦ «በወንጀል እና ድንበር በማለፍ ላይ
አትረዳዱ»
③ አጠገቡ በሌሉ ፣ ሙት በሆኑ እና እሡ የሚፈልገውን
እርዳታ መርዳት የማይችሉ አካላትን መማፀን ይህ ሽርክ
ነው
⁴ ★ ኢስቲአዛ
☞ ኢስቲአዛ ማለት ፦ ከሚጠላው ነገር በአላህ መጠበቅ
ይህም በስቲአና ላይ ያለፋት ሦስት አይነታዎች
ይመለከቱታል
Ⅰ ኢስቲጋሣ
☞ ኢስቲጋሣ ልክ እንደ ኢስቲአና እገዛ መፈለግ ሢሆን
ከስቲአና የሚለየው
በከባባድ ጉዳይ እገዛ የምንፈልግ ከሆኘ ለምሣሌ በጦርነት
ሠአት የምንፈልገው የእርዳታ አይነት ኢስቲጋሣ በመባል
ይታወቃል ቀለል ላሉ ጉዳዬች ደግሞ ኢስቲአና በመባል
ይታወቃል ማብራርያው ከእስቲአና ጋር ተመሣሣይ ነው
Ⅱ ★ ዘብህ
☞ ዘብህ ማለት ፦ የእንስሣት ደምን ማፍሠስ ማለት ነው
✔ በተለያየ መልኩ ሊታይ ይችላል
① የአላህ ፊት ተፈልጎበት የሚታረድ እርድ፥ የሚታረደው
አላህ እንዲታረድ ያልከለከለበት ቦታ (ከእሡ ውጪ ያለ
አካል የማይመለክበት ቦታ) ፣ የአላህ ስም ተጠርቶ እና
ለአላህ ብቻ ታስቦ እሡ ባዘዘው ሠአት የሚታረድ የእርድ
አይነት ነው ።
② አላህ ባልፈቀደው ቦታ ፣ ከአላህ ውጫ ያለ አካል ስም
ተጠርቶ ፣ከአላህ ውጪ ላለ አካል ታስቦ የሚታረድ የእርድ
አይነት ሽርክ ነው
③ አላህ ባልከለከለው ቦታ ፣ የሡ ፊት ተፈልጎበት ፣ የሡ
ስም ተነስቶበት ፣ ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም
ባልደነገጉት ወቅት የሚታረድ የእርድ አይነት ቢድአ ነው
④ እንግዳን ለማክበር ታስቦ የአላህ ስም ተነስቶበት የታረደ
የእርድ አይነት ይህ የተፈቀደ ነው
Ⅲ ★ ነዝር
☞ አላህ ግዴታ ያላደረገውን ነገር በራስ ላይ ግዴታ
ማድረግ ( ጥቅምን ከማግኘት ጋር)
~አላህ የሡን መልካም ባርያዎች ነዝር በመሙላታቸው
አወድሦ መናገሩ ኢባዳ ለመሆኑ ግልፅ ማሣያ ነው
∴ አላህ ለማመፅ የተሣለ ነዝር መሙላት አይቻልም
በሀላል ነገር ላይ የተሣለ ነዝር መሙላቱ የግድ ነው!!
በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል!!
share ማድረጎን እንዳይረሡ‎
ሡሉ ሠላሣ.፦ ክፍል አስራ ሁለት
የኪታቡ ፀሀፊ እንዲህ አሉ
★ የሀሺያ ( ፍራቻ ) መረጃ አላህ እንዲህ ይላል ¹ « እነሡን አትፍሯቸው እኔን ፍሩኝ » (አልበቀራ 150)
★ የኢናባ. (መመለስ) መረጃ አላህ እንዲህ. ይላል ² «ወደ ጌታችሁ ተመለሡ ለሡም እጅ ስጡ » ዙመር
★የኢስቲአና (እርዳታ መፈለግ) መረጃ አላህ እንዲህ ይላል³ «አንተን ብቻ እንገዛለን በአንተ ብቻ እርዳታ እንለምናለን» አል ፋቲሀ
★ የኢስቲአዛ (መጠበቅ ) መረጃ⁴ አላህ እንዲህ ይላል « በተፍለቅላቂዋ ጎህ ጌታ በሆነው እጠበቃለው በል» አል ፈለቅ
★ የእስቲጋሣ. ( የ ይድረሡልኝ ጥሪ) መረጃ አላህ እንዲህ ይላል «ጌታችሁን እርዳታ በጠየቃችሁ ግዜ
ተቀበላችሁ» Ⅰ
★ የዘብህ (እርድ) መረጃ Ⅱ አላህ እንዲህ ይላል «ስግደቴም ፣ እርዴም ፣ ህይወቴም ፣
ሞቴም ለአለማቱ ጌታ ለአላህ ነው በል። (163) «ለእርሡም ተጋሪ. የለውም በዚህ (በማጥራት) ታዘዝኩ ። እኔም የሙስሊሞች መጀመርያ ነኝ» በል።» አል አንአም ከሀዲስ « ከአላህ ውጪ ላለ አካል ያረደ አላህ ከራህመቱ አባሮታል»
★ የነዝር (ስለት) መረጃ አላህ እንዲህ ይላል « ስለታቸውን ይሞላሉ ከፋቷ የተንሠራፋ የሆነን ቀን ይፈራሉ »
_________
አጭር ማብራሪያ
_____
¹ ★ ሀሺያ
☞ ሀሽያ ማለት በእውቀት ላይ የተደገፈ ፍራቻ ነው. ስለአላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ሀያልነት እና ብርቱነት ጠንቅቀው የሚያውቁ ሠዎች የሚፈሩት የፍራቻ አይነት ነው አላህ እንዲህ ይላል
« ከባርያው አላህን የሚፈሩትማ የሚያውቁት ናቸው»²
★ኢናባ
☞ ኢናባ ማለት.የአላህ ትእዛዛት በመተግበር ክልክላቶቹን በመራቅ ወደ አላህ መመለስ ማለት ነው
★ የሠው ልጅ ሢፈጠርም ተሣሣች ነው!!! አወቀነውም ሆነ ሣናውቀው በተለያየ መልኩ ጌታችን አላህን እናምፀዋለን መሀሪ የሆነው አዛኙ ጌታችን ግን የኛ ወንጀል ምንም ያክል የበዛ ቢሆንም አዛኝነቱ ከቁጣው በላይ ነውና የሠራነውን ወንጀል በአጠቃላይ የሚምምርበትን ተውበት የተሠኘን በር ከፈተልን ይህ በር ጥቁሩን ፣ቀዩን ፣ደሀውን ፣ ሀብታሙን. ሁሉንም ሣይለይ ከመቀርቀሩ በፊት ያንኳኳኳውን ሁላ ያስገባል። ከተቀረቀረ ቡሀላ የመጡትን ግን ማስተናገጃ ቦታ
የለውም ~ መቼ ነው ይሔ በር የሚዘጋው ???? ይህ በር
1ኛ በግለሠብ ደረጃ ፦ አንድ ሠው ለመሞት ጫፍ ሢደርስ ሁሉን ነገር ስለሚገለፅለት ቢፀፀት እና ቢመለስ ዋጋ አይኖረውም
2ኛ ከትላልቅ የቂያማ ምልክቶች መካከል አንዷ የሆነችውየፀሀይ በመግቢዋ መውጣት ናቸው
♂ አንድ ሠው ገርገራ ላይ ሆኖ እና ፀሀይ ከመግቢያዋ ከወጣች ቡሀላ ተውበት ተቀባይነት የላትም
∴ ተውበት የሚያደርግ ሠው
① ተውበት ሊያደርግ ያሠበውን ወንጀል ማቆም አለበት
② ተውበት ወዳደረገው ወንጀል ላይመለስ ቁርጥ ውሣኔ መውሠድ አለበት
③ በሠራው ወንጀል መፀፀት አለበት
④ ከሠው ልጅ ጋር በተያያዘ መልኩ ከሆነ የበደለውን አውፍ ማስባል የወሠደውን ንብረት መመለስ አለበት ከአራቱ አንዱ ከጎደለ ተውበቱ ተቀባይነት አይኖረውም!!
³ ★ኢስቲአና
☞ ኢስቲአና ማለት ፦ እገዛን መፈለግ ማለት ሢሆን በተለያየ መልኩ ሊታይ ይችላል
① በአላህ መታገዝ ፡ በአላህ የሚታገዘው አካል ለአላህ የተናነሠ እና የተዋረደ ሠው ነው, ጉዳዩንም ወደ አላህ ያስጠጋ ሠው ነው, ከአላህ ውጪ ባለ አካል በዚህ መልኩ መታገዝ ሽርክ ነው, አላህ ብቻ ነው የዚህ ኢባዳ ባልተቤት! መረጃው ላይ እንደተመለከትነው አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ሒክማ በተሞላ ንግግሩ እንዲህ ይላል ( ﺇِﻳَّﺎﻙَ ﻧَﻌْﺒُﺪُ ﻭَﺇِﻳَّﺎﻙَ ﻧَﺴْﺘَﻌِﻴﻦُ )
« አንተን ብቻ ነው ምንገዛው. በአንተ ብቻ ነው እገዛ ምንፈልገው»
እንደ አረበኛ የአነባብ ህግ ከስራው በፊት ሠራተኛው ከተጠቀሠ ስራው ለዛ አካል ብቻ የተገደበ ነገር መሆኑን ያጣቅማል ለምሣሌ. (( ﻭَﺇِﻳَّﺎﻙَ )) የሚለው ባለቤት ሢሆን ስራው ደግሞ ((( ﻧَﺴْﺘَﻌِﻴﻦ )) ነው ስለዚህ ኢስቲአና በሀሊቃችን ላይ የተገደበ ነው
②ፍጡራኖች የሚችሉት ነገር እርዳታ መፈለግ ፦ አላህን ማመፅ ካልሆነ እና መልካም ነገር ከሆነ መረዳዳቱም እርዳታም መጠየቁ የተፈቀደ ነገር ነው አላህ እንዲህ ይላል « በመልካም ነገር እና አላህን በመፍራት ተረዳዱ» ∞ ነገር ግን በወንጀል እና አላህን በማመፅ ላይ መተባበር አይፈቀድም አላህ እንዲህ ይላል ፦ «በወንጀል እና ድንበር በማለፍ ላይ አትረዳዱ»
③ አጠገቡ በሌሉ ፣ ሙት በሆኑ እና እሡ የሚፈልገውን እርዳታ መርዳት የማይችሉ አካላትን መማፀን ይህ ሽርክ ነው
⁴ ★ ኢስቲአዛ
☞ ኢስቲአዛ ማለት ፦ ከሚጠላው ነገር በአላህ መጠበቅ ይህም በስቲአና ላይ ያለፋት ሦስት  አይነታዎች ይመለከቱታል
Ⅰ ኢስቲጋሣ
☞ ኢስቲጋሣ ልክ እንደ ኢስቲአና እገዛ መፈለግ ሢሆን ከስቲአና የሚለየው በከባባድ ጉዳይ እገዛ የምንፈልግ ከሆኘ ለምሣሌ በጦርነት ሠአት የምንፈልገው የእርዳታ አይነት ኢስቲጋሣ በመባል
ይታወቃል ቀለል ላሉ ጉዳዬች ደግሞ ኢስቲአና በመባልይታወቃል ማብራርያው ከእስቲአና ጋር ተመሣሣይ ነው
Ⅱ ★ ዘብህ
☞ ዘብህ ማለት ፦ የእንስሣት ደምን ማፍሠስ ማለት ነው
✔ በተለያየ መልኩ ሊታይ ይችላል
① የአላህ ፊት ተፈልጎበት የሚታረድ እርድ፥ የሚታረደው አላህ እንዲታረድ ያልከለከለበት ቦታ (ከእሡ ውጪ ያለ አካል የማይመለክበት ቦታ) ፣ የአላህ ስም ተጠርቶ እና ለአላህ ብቻ ታስቦ እሡ ባዘዘው ሠአት የሚታረድ የእርድ አይነት ነው ።
② አላህ ባልፈቀደው ቦታ ፣ ከአላህ ውጫ ያለ አካል ስም ተጠርቶ ፣ከአላህ ውጪ ላለ አካል ታስቦ የሚታረድ የእርድ አይነት ሽርክ ነው
③ አላህ ባልከለከለው ቦታ ፣ የሡ ፊት ተፈልጎበት ፣ የሡ ስም ተነስቶበት ፣ ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ባልደነገጉት ወቅት የሚታረድ የእርድ አይነት ቢድአ ነው
④ እንግዳን ለማክበር ታስቦ የአላህ ስም ተነስቶበት የታረደ የእርድ አይነት ይህ የተፈቀደ ነው
Ⅲ ★ ነዝር
☞ አላህ ግዴታ ያላደረገውን ነገር በራስ ላይ ግዴታ ማድረግ ( ጥቅምን ከማግኘት ጋር)
~አላህ የሡን መልካም ባርያዎች ነዝር በመሙላታቸው አወድሦ መናገሩ ኢባዳ ለመሆኑ ግልፅ ማሣያ ነው
∴ አላህ ለማመፅ የተሣለ ነዝር መሙላት አይቻልም በሀላል ነገር ላይ የተሣለ ነዝር መሙላቱ የግድ ነው!! በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል!!  share ማድረጎን እንዳይረሡ